ለመምህር ዘበነ ለማ ‘የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ’ ቪሲዲ ምላሽ የሰጠው መፅሐፍ ተወደሰ።

ትላንት ሰኔ 11 ቀን 2002 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡30 ላይ አምስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ መካነ የሱስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ  ገብረ መሲህ በተባሉ ግለሰብ “ የመምህሩ ምርቅ እና መረቅ” በሚል ርዕስ የተፃፈው መፅሐፍ ተገመገመ። ይህ መፅሐፍ መምህር ዘበነ ለማ የቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ላይ (እንደ እኔ አመላካከት በአጠቃላይ ወንጌላውያን) ትችት የሰነዘሩበት እና “የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ” በሚል ርዕስ በዚህ ዓመት ለተሰራጨው ቪሲዲ የተሰጠ መልስ  ነው። በዚህ በማቴቴስ መፅሄት ዝግጅት ክፍል በተሰናዳ እና 100 የሚሆኑ ሰዎች የተካፈሉበትን ውይይት በንግግር የከፈቱት አቶ ሚኪያስ በላይ የመፅሔቱ ዋና አዘጋጅ ናቸው። ውይይት ላይ የመፅሐፉን መደበኛ ግምገማ ያቀረቡት በማቴቴስ መፅሄት ላይ መፅሐፍትን በመገምገም ስራቸው የሚታወቁት ወንድም ነብዩ ዓለሙ፤ የውይይቱን ፕሮግራም በማሰተባበር ያገለጉት ወንድም ንጉሴ ቡልቻ ሲሆኑ ፣ መፅሐፉን በማንበብ ምን እናድርግ ለሚለው ጉዳይ ደግሞ ምላሽ የሰጡት መጋቢ ስሜ ታደሰ ናቸው።

አቶ ነብዩ መፅሐፉን “ምላሽ ከመስጠት” ዓላማው አንፃር የገመገሙት ሲሆን የፅሁፉን መረጃ አጣቃሽነት አመክንዮ እና  ይዘት አወድሰዋል። በማጠቃለያቸው የሰጡት አጠቃላይ ግምገማ ግን ጠለቅ ያለ ነበር። በተለይ መፅሐፉ “ከተሰነዘረው ትችት ይልቅ በግለሰቡ ላይ አተኮረ” የሚለው የመደምደሚያ ሐሳባቸው ከታዳሚዎች ጥቂት ተቃውሞ ቢገጥመውም እውነትነቱ ግን በመፅሐፉ ውስጥ ይንፀባረቃል። መፅሐፉን ባነበብኩበት ወቅት ገብረ መሲህ ከመምህር ዘበነ ጋር ጥብቅ እውቅና ያላቸው መሆናቸውን ተመልክቻለሁ። (ይሄ ነገር መልስ ለመስጠት ተገቢ ሰው ያደርጋቸው ይሆን?)

በተጨማሪም እኚሁ ሰው የመፅሐፉን የቋንቋ አጠቃቀሙን በተለይም የቀላት ክብደት በተመለከተም መሰተካከል እንዳለበት የሰነዘሩት አስተያየት እኔም የምጋራው ነው። እንደዚህ አንገብጋቢ በሆነ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሚሰጡ መፅሐፍት የቋንቋ አጠቃቀም መዝገበ ቃላት ፍለጋ የሚያስሮጠን  ባይሆን፣ ማንኛውም ሰው ሊረዳው በሚችለው የእለት ከእለት የመግባቢያ ቋንቋ ቢፃፍ ድንቅ ነው እላለሁ። በዚህ አጋጣሚ ከመድረክ ላይም ሆነ ከታዳሚዎች የተሰነዘረው ተግባቦትን ከመፍጠር ይልቅ የቋንቋን ውበት እንጠብቅ የሚለው ሐሳብ የማልጋራው ነው። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቴ ውብትን በተላበሰ ቋንቋ የተፃፈና ለተሰጠው ትችት አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ መፅሐፍ ሆኖ ፣ አንባቢያን አንብበው የማይረዱት ከሆነ ዓላማውን መትቷል ብዬ ስለማላምን ነው። በተጨማሪም መፅሐፉ “ሰፊውን ነገር አጥብቧል” በሚለው ጉዳይ ላይ የተሰጠው  የአቶ ነብዩ አስተያየት በእርግጥም እውነትነት ያለው ነው። መምህር ዘበነ ስለቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል የሚያወሩ ይምሰሉ እንጂ ትችቱን የሰነዘሩት በሁሉም ወንጌላውያን ላይ መሆኑን ቪሲዲውን በመመልከት መፍረድ ይቻላል። የገብረ መሲህ መልስ ግን በአብዛኛው በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል በተጨማሪም በግለሰቡ ማንነት እና ሐሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው።


(ይሄ ቪዲዮ “የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ” ከሚለው የተወሰደ ነው ሙሉውን ከዩ ቲዩብ ማግኘት ትችላላችሁ።)

በመቀጠል መፅሃፉን ተንተርሰን ምን እናድርግ በሚለው ዙሪያ “ጣፋጭ” ትንተና የሰጡት መጋቢ ስሜ ታደሰ ናቸው። መጋቢ ስሜ የተለያዩ ጥልቅ ሐሳቦች የሰነዘሩ ቢሆንም ከነዚህ መካከል “እራሳችን የስራው ባለቤት አድርገን አንይ” ይህም ማለት የስራው ባለቤት እሱ ጌታ ሆኖ እኛ የስራው ባለቤት ሆነን ለመቅረብ አንሞክር ማለታቸው መሰለኝ። እንዲሁም ደግሞ የእግዚአብሄርን ቃል እንወቅ የሚሉት ሐሳቦች ሚዛን የሚደፉ ናቸው። በተለይም ሁለተኛው ሐሳብ በወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያናቶቻችን ውስጥ ለምናያቸው ግልፅ ግድፈቶች መንስኤው ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ለልምምዳችን ከፍተኛ ትኩረት መስጠት መሆኑን የምናስተውለው ነው። ይህንንም ሁኔታ አንዳንድ የቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል በለቀቀችው ቪሲዲ ላይ የታየ አንድ ድርጊት በመጥቀስ መፅሐፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ከታዳሚዎች በስተመጨረሻ በተሰነዘረው አስተያየት የመፅሐፉን “ሚዛናዊነት”፣ ስነፅሁፋዊ ጥልቀት፣ መረጃ አጠቃቀም፣ ፈር ቀዳጅነት፣ ታሪካዊ ስነመለኮታዊ እና አመክንዮ ተወድሷል። አንዳንድ ሰዎችም በእርግጥ ከእኛም መካከል “ያልተገባ” ትችት ሲሰነዘር ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ መልስ መስጠት የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ የሚያሳይ ነው ብለው ገልጠውታል። እራሳችንን ለትችት አጋልጠናል የሚሉ ሰዎች ደግሞ እራሳችንን እናስተካክል ሲሉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ፣ በግል ያናገርኳቸው ሰዎች ደግሞ  “የራስን ድክመት ለመሸፈን ሌሎችን ማጠልሸት” ከክርስቶስ የተሰጠንን የወንጌል  አደራ ከመወጣት አንፃር የሚያበረክተው አስተዋፅኦ እንደሌለ  በምሬት ተናግረዋል።

እንዲያው በጥቅሉ የመምሀር ዘበነን ቪሲዲ ተመልክቶ እሰይ አበጁ በዚሁ ይቀጥሉ ያለ “በሳል” ሰው ከኦርቶዶክሳውያንም ከወንጌላውያንም ይገኛል ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል። ይህንን ስል ታዲያ ቪሲዲው ካነሳቸው ግድፈቶች መካከል አንዳንዶቹ በአቢያተ ክርስቲያናቶቻችን አልተንፀባረቁም ለማለት አይደለም በእርግጥ ተንፀባርቀዋል። ለዚህ ሁሉ ችግር ዋና መሰረቱ  “መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሀይምነት” በእኛ በወንጌላውያን መካከል እየተከሰተ መምጣቱ ይመስለኛል። የመድረክ ላይ ድርጊቶቻችን በአብዛኛው መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረታቸው “የሳሳ” ናቸው። ይሄ ደግሞ ለትችት አጋልጦናል! ይገባናልም። መምህር ዘበነም የሰጡት ትችት “መረቅ” (እውነተኛ የሆነ ነገር ቢኖረውም) “ምርቁ” (ድብልቁ) በዝቶበታል ባይ ነኝ። ስለዚህ እባካችሁ ከዚህ “ከመፅሐፍ ቅዱሳዊ መሐይምነት” ለመውጣት እንስራ እሱን እናስተምር እሱን እናገር በእሱ እንኑር ፣ ፀሐፍትም እባካችሁ የቋንቋ ውበትን ከቃላት ትልቀት ጋር ሳይሆን ከተግባቦት ስምረት ጋር  አቆራኙት፤ በተጨማሪም እንዲህ በብስለት እና በጨዋነት የሚመካከር ፣የሚገሳሰፅ ትውልድ ጌታ ከኦርቶዶክሳውያንም ከወንጌላውያንም ያስነሳልን።

ለማንኛውም ብራቮ ማቴቴስ!!

Published by Abinet

I am a graduate of Evangelical Theological College (ETC) of Addis Ababa ( Bible Translation and Literacy Major) (2011). I am a Graduate of Masters of Art in Religion from Africa Nazarene University (ANU), Nairobi, Kenya(2015). A student in Counseling Psychology at Addis Ababa University. A husband with three Children living in Addis Ababa, Ethiopia. I love writing and discussing issues pertaining to faith and life. My area of interest youth, culture, art, Secular Vs Sacred, religious Philosophy and Apologetics.

4 thoughts on “ለመምህር ዘበነ ለማ ‘የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ’ ቪሲዲ ምላሽ የሰጠው መፅሐፍ ተወደሰ።

  1. it is really a wonderful observation. i was one of the attendants and what i noticed was there is a need to criticize eachother but only with love and upright spirit. the other thing is there is no need of defending our leaders or pastors when they do wrong. May the Lord Keep the Church from the evil one.

    1. Mamoye,
      you are right we need to have ahumble spirit and a right mind to handle critisim. Indeed bro may the Lord help us raise up some of those people who have the wits and the guts. I am gonna get some of them here on my blog very soon. Keep on searching!

  2. ጥሩ ምልከታ ነው! በጣም ወድጄዋለሁ። በጉባኤው የተገኘው ሰው ቁጥር ግን መቶ ነበር።

    በርታ!

    1. Thank you bro. I am also proud of you guys…you, micky,GebreMesih and all other mathethes guys.Hope you keep on dropping by and comment. I would be thrilled if you guys would “guest blog”.

ምን ሐሳብ አለዎት?