ምን ይወራል ? News

ጋሼ በቄ፦ ‘የእኛ ሠፈር ሰው!’

008እግዚብሔር በሚያውቀን መልኩ ሰዎች ቢያውቁን ምን ይሉ ይኾን ? (በሞቴ እሰቲ ለጥቂት ደቂቃ አስቡት!)
አንዳንዶቻቸን ሕይወታችን “ጉድፉ” በዝቶብን የእግዚአብሔርን ቸርነት እየተጠራጠርን ነው። ሌሎቻችን ደግሞ የምንፈልገውን ማገኘት ተስኖን እየቆዘምን ነው። ሌሎቻችን ደግሞ የምናወራው እና የምንኖረው የማይገናኝ ሆኖብን የሰቀቀን ኑሩ እየገፋን ነው። እንዲያው ሰዎች ይህንን “ጉዳችንን” ቢያውቁት አግልግሎታችን ፣ ሥራችን፣ ኑሯችን ፣ ትዳራችን፣ወዳጅነታችን እንደ ጉም ሲተን ይታየናል። ለዚህም ይመስኛል አንዳንድ ጊዜ ከምንኖረው በላይ የምንጮኸው። ሕይወታችን እየደከመ በሄደ ቁጠር ጮኸታችን እየበረታ የሚመጣ ይመስለኛል። (የሥነ ልቦና ሊቃውንት Preversion እንዲሉ ! ማስቀየሻ እንበለው!)
ታዲያ በዚህ ‘በእኛ ሰፈር’ የሚኖር አንድ ሰው ይህንን ጩኸታችንን “ኡ ኡ ኡ…” ብሎ ሲጮኽልንስ? መንፈሳዊ ብርታቱን አግኝቶ እኛ ለራሳችን እንኳን ጮክ ብለን ልንናገረው የማንደፍረው ነገር ሲነግረንስ። ይህንን ድብቅ ማንነታችንን ፊት ለፊት ፍንትው አድርጎ በማሳየት ‘ቀልብን እንደንገዛ’ እና ልባችንን ወደ አንድዬ እንድንመልስ ሲሞግተንስ።
በጋሽ በቄ “ጣልቃ እየገባ ፦ ትንግርት ያ’ረገለት ሰው ታሪክ’ መጽሐፍ ውስጥ የሰማሁት ጩኸት ይኸው ነው። አንድ ጊዜ ታዋቂው ምሁር ሲ ኤስ ሊዊስ እንዲህ ብሎ ነበር፦

“ ክርስትናችን ስራሳችን በጎነት እንድናዜም ሲያደርገን፤ በተለይም ከሌሎች መብለጣችንን ሲሰብከን ፤ በርግጠኝነት በኛ ላይ እየሰራ ያለ ይል እንዳለ ግልጽ ነው። እሱም እግዚብሔር ሳይሆን ሰይጣን ነው። በእግዚአብሔር ፊት የመገኘታችን አይነተኛ ምልክት ራሳችንን ፈጽመን መርሳታችን ወይም ደግሞ ራሳችንን እዚህ ግባ የማይባል እና ኮሳሳ ድርገን ማየታችን ነው።”

እኛ ሰፈር ይሄ የለም! እኛ ሰፈር የራሳችንን አስቀያሚ ማንነት መጋፈጥ ሲያቅተን ስለ ራሳችን ‘ማስታወቂያ’ እንሰራለን። “በዘህ ወጥቼ ..በዚህ ወርጄ..እንዲህ አድርጌ ..ደግሞም እንዲያም አድርጌ” እያልን ከእውነታው እንሸሻለን።
ጋሽ በቄ ግን ይህንን ውስጣዊ ትግል በ358 ገጾች ጠርዞ አሳይቶናል። በ”ጣልቃ እየገባ” ውስጥ እግዚአብሔር በሰው ሕይወት ውስጥ ሲሰራ እናየዋለን። ደግሞም እንገረማለን። ብላሽ ፣ ጉድፍ፣ የማይጠቅም ፣ የሚያሳፍር፣ የማይገባን የምንላቸውን ሁኔታዎች አንስቶ እንደ ሃር ሲያደውራቸው እናያለን። The Grand Weaver ‘ታላቁ ሸማኔ’!
ይሄ መጽሐፍ ምንም ነገር ባይሰጣችሁ። እነዛ አሳፋሪ የምትሏቸው የምትቆጩባቸውን ኹኔታዎች ፊት ለፊት ተጋፍጣችሁ የምታሸነፉበት ጉልበት የሚያሰጣቃችሁን ታዩታለችሁ። እኔ ያንን አግኝቻለሁ። በሕይወቴ በሰረዃቸው ስህተቶች ፍርስራሽ ውስጥ የእግዚአብሔርን ዱካ እንዳይ አድርጎኛል።

“በጋሽ በቀለ “ጣልቃ እየገባ” መጀመሪያ ሰው የሆነውን ጋሽ በቀለን አየሁ።…ዝቅ ብሎ ምድጃ ዳር ትረካ ሲያዋየኝ ግን ከትቢያ የሚያነሳውን ሰባራ ጠጋኙን ፍርስራሽ (መቃብር) ቆፋሪውን ፣ የመደዴዎች ወዳጅ የሆነውን የጌታ አምላኬን የምህረቱን ባጠግነት አሳየኝ ይኼ ነው ባዶነት ከቶስ ደኸ ልሸሸግ ቢልስ ከምኑ ይሸሸጋል (ወንድዬ አሊ- ስለ መጽሐፉ ከተሰጠ አስተያየት የተወሰደ)

ስለዚህ ጋሽ በቄ ሰው ሰው ይሸታል! እኔን እኔን ይሸታል እናንተን እናንተንም ይሸታል!
(መጽሐፉ ውስጥ ባገኘቸው ሌሎች ሐሳቦች ዙሪያ ያለኝን አመለካከት አበክሬ አወጋለሁ።)  Read PDF  ጋሽ በቄ

Advertisements

One thought on “ጋሼ በቄ፦ ‘የእኛ ሠፈር ሰው!’

  1. Isn’t this what is eating the evangelical community from the inside. Eventhough it is not articulated as such, most Ethiopian evangelicals believe they are free from sin and do not transgress in any way since their conversion. Because of this to the outside observer they come across as hypocrites in fact they are. One gets the depth of their hypocracy and shallow understanding of sin when one considers what is considered sin by the evangelical community in Ethiopia. The list consists of trivial issues – Listening to secular music, drinking alcohol, smoking. If you stay away from these they say your life is holy and clean. By this definition one does not need to be a christian to live a holy and clean life. There are millions of people who have such a life style. Their concept of love is even more amazing – it is attachment that they develop when people engage in common activity such as being a choir members or going to the same church etc. What they mean love is their attachment to people they associate with. This too is common among unbelievers. They trivialize sin and set the bar very low. But they are very extreme in talking and observing these trivial issues. Because of this as it is plain to see they have no fruit. More than any time in Ethiopian history the size of the evangelical community is the highest nearly 18% of the population but their impact on society is nil. The moral standard of the Ethiopian society is falling as the size of the evangelical community is rising. In real terms an average evangelical does not show any more integrity than a none evangelical person. Yet they seem to be very happy in their state of affairs .

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s