Uncategorized

የሃዊ ማስታወሻዎች

ክፍል ዘጠኝ
አዲስ ዓመት ሲያልቅ ልክ ማሚ ቤት ሳትኖር የሚሰማኝን አይነት ስሜት እንዲሰማኝ ያደርገኛል። እንዲያው ደርሶ ክፍት ይለኛል። ዳዲ የሰው ልጅ ዓመት ሲለዋወጥ የማያስታውሰው ነገር ቢኖር ወደ ሞት ምን ያህል እየቀረበ እንደሚመጣ ነው ይላል። ልክ እኮ ነው! ወዳጆቼ እያንዳንዷ ጀንበር እየጠለቀች በሄደች ቁጠር ወደ ህይወት ሳይሆን ወደ ሞት እየቀረብን ነው። ለነገሩ ማሚ እንደምትለው ሰው እኖራለሁ እንጂ እሞታለሁ አይል።
(የሞትን ደጃፍ ጎብኝቼ) ቋንቋ ትምህርት ቤት ተመልሻለሁ። የስፖክን ኢንጊሊሽ መምህራችን በአዲሱ ዓመት ያለንን ዕቅድ እንድንጽፍ ጠይቀውናል። ብዙ ተማሪዎች ዕቅድ እና ቃል መግባት የተካኑ ነው የሚመስሉት አብዛኛዎቹ የተሰጣቸውን የክፍል ሥራ ጨርሰው በታለቅ ተመስጦ ያወራሉ። አንዳንድ ወንዶቹ በቅርቡ ስለ ወጡ አዳዲስ ፊልሞች ተግባራዊ ሲለዋወጡ፣ ሌሎቹ ደግሞ የማንችስተርን እና የአርሴናልን ያረጀ ያፈጀ እና የተቀጨ ጨዋታ አንስተው ይዘበዝባሉ። ሴቶቹ ከንፈር ለከንፈር ለመነካካት ትንሽ እኪቀራቸው ተቀራርበው ስለቦይ ፍሬንዶቻቸው አስደማሚ ትንተና ይሰጣሉ። ኪኪ አይኖቿ ከጉድጓዳቸው ለወጡ ደጃፍ ላይ ደርሰው አፏን ገርበብ አድርጋ ከፍታ ጄሪ የምታንቆረቁረውን ተግባር ተኮር የጭፈራ ቤት አመሻሽ ትኮመኩማለች።
ይሄ ሁሉ የሚሆነው…የአመቱ እቀድ በአምስት ሰክንድ ውስጥ ተጠናቆ መሆኑ ነው። እኔ እና ባለመስመሩ ወረቀት ግን እንደተፈጠጥን ነው። ልክ ሊጽፍ እንደተዘጋጀ ሰው እኪብርቶዬን በእጄ ወደ ወረቀቱ አስጠግቼ ይዣለሁ። የሚያስቅው ነገር ከተወለድኩ ጀምሮ ሰዎች እቅድ ሲያወጡ እንጂ ሲፈጽሙ ላላየ ሰው “እቅድ አወጪ!” ከሚል ሃሳብ በላይ ምን መርዶ አለ።
አንዳንድ ጓደኞቼ በአዲሱ ዓመት ውስጥ ወደ ቤተ ክርስቲየን ለመሄድ እና መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ቃል እገባለሁ ይሉና። አራት ሳምንት ሳይሞላው እቅዳቸው ይተናል። ዳዲ ለምሳሌ በየአዲስ ዓመቱ ቡናን እርግፍ አድርጎ ለመተው እንደማለ ነው ። ዕቅዱ ታዲያ የሚሰራው ለአመት በአል ቀን ብቻ ነው። ዳዲ ሲያጠፋፋ “መንግሥት እንኳን ዕቅዱን መቶ በመቶ አያሳካም!” ይላል። ታዲያ እኔን የማልፈጽመውን እቅድ አውጪ ብሎ ጭቅጭቅ ነው።
“አኮ ዚስ ኢዝ ኢኖፍ” ትልቅ የጭብጨባ ፍንዳታ ሲያሰሙ። እንደንብ ተሰብስቦ የነበረው ተማሪ ወደ መቀመጫው ተመለሰ።
“ኦኬ ኢቭሪ ቦዲ ዊል ፐርዘንት ሂዝ ፕላን” በአጭሩ የቀረቡ “አሰቃቂ እቅዶች ይህን ይመሰላሉ፡-
ሳሚ
በሚቀጥለው አመት ሁሉንም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ለማየት አቅጃለሁ።
ሊና
በሚቀጥለው ዓመት ከቦይፍሬንዴ ጋር ወደ አዋሳ ለመሄድ አስቤያለሁ። ግን …. ቤተሰብ እንዴት እንደምሸውድ አላውቅም…
(ጭብጨባ ፉጨት ..ጭብጨባ ፉጨት)
ዳዳ
ይህን ሲጋራ እንዴት እንደማቆም ጭንቅ ብሎኛል ለማንኛውም … ቢ ንስ በቀን ከሁለት በላይ ላለማጨስ አቅጃለሁ
(ሃሃሃሃሃሃ)
ጄሪ
(…..) ክልብ መጨፈር እንዴት መሰላችሁ ያማረኝ..እርግጠኛ ነኝ .. እንግሊዛዊው ቦይ ፍሬንዴ ሲመጣ…እሄዳለሁ
(ታላቅ ጭብጨባ እና ፉጨት)
ደሬ
በሚቀጥለው ዓመት የበለጠ ውጤቴን ለማሻሻል አቅጃለሁ (ውኡኡኡኡአኡ!!!!!)
ኪኪ
እ እእ… በቃ አንድ የማፈቅረው ሰው አለ…እእእእእ… እሱን
(መጠየቅ!!!!! መጠየቅ !!)
ሐዊ
ከመቀመጫዬ ተነሳሁ።
ተማሪዎቹ በሙሉ “ሐዊ ሓዊ ሐዊ!” ማለት ጀመሩ።
ከመሐላቸው አንዱ “በናትስ እኔን በሚቀጥለው ዓመት አጀንዳስ ውስጥ አስገቢኝ… (ሳቀ ጭብጨባ)
ፊት ለፊታቸው ቆምኩ
ባደ ወረቀቴ ላይ አፈጠጥኩ። አሁንም አፈጠጥኩ ።
“ካም ኦን ሃዊ ቴል አስ!”
ክፍሉ ብሎ ሁሉም ሰው እኔን መመልከት ጀመረ። እግሬ መብረክረኩን መደበቅ አልችልም። እጄ ላይ ያለው ወረቀት በንፋስ እንደሚንገዋለል መርገብገብ ጀመረ።
“እእ..እ..” ጎሮረየ ተሳሰረ
“የእኔ የአዲስ ዓመት እቅድ “ምንም አለማቀድ ነው”…” ክፍሉ የበለጠ ጸጥ አለ እጆቼና እግሮቼ በጸጥታው በረቱ
“ከልጅነቴ ጀምሮ እናት አባቴ፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ሲያቅዱ እንጂ ሲፈጽሙ አላየሁም፤ እኔም እራሴ ብሆን፤ ስለዚህ የ 2004 ዕቅዴ “አለማቀድ ነው”… የማልፈጽመውን ነገር በማቀድ እራሴን እና እናተን በተለይም ደግሞ እገዚአብሔርን ማታለል አልፈልግም!”
ጭብጨባ፣ ሳቅ ፣ ሽሙጥ፣ ማላገጥ እና የመሳሰሉት የት እንደገቡ አይታወቅም።
ምንም አለማቀድ እንዲህ ጠቃሚ ነው እንዴ?
እፎይ !!!

Hawwiii

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s