መጣጥፍ Articles

“የኢትዮጵያ ሕዝብ አያስብም።”

ዛሬ ነው ። ከቶታል ወደ መከኒሳ የሚሄድ ታክሲ ጋቢና ውስጥ ቁጭ ብያለሁ። ከጋቢናው በስተቀር  ሌላው ቦታ በሙሉ በሰው ተሞልቷል። ባዶ ቦታ ቢታይ ትራፊክ የሚይዛቸው ይመስል ክፍት ቦታዎችን በሙሉ በሰው እና በዕቃ ችምችም አድርገዋቸዋል። ጉዞ ጀመርን ። በገብርኤል ቁል ቁል ወደ አቦ ማዞሪያ እስክንደርስ ድረስ፤ ከአንዳንድ ተቸምቻሚዎች ቅሬታ በስተቀር ሁሉም በሃሳብ ተውጧል። እንዲህ አይነት ፀጥታ የሚመነጨው ከኑሮ ውድነት ብቻ ይመስለኛል። ድንገት እንዱ  “ወራጅ አለ!” ሲል ተቆጣ። ዞር ብሎ ያየውም ሰው አልነበረም። ምናልባት በደህና ጊዜ ቢሆን ኖሮ የሽሙጥ ሳቅ እንኳን አያጣም ነበር። ዛሬ ግን  ማንም ቁብ ሳይሰጠው ሃሳቡን ያዳውራል።

እኔ ራሴ ቁጡው ሰውዬ ከአጠገቤ እንዳላ ያወቅኩት ሲወርድ ገፋ ሲያደርገኝ ነው። የታክሲው ሹፌር በአጥንት ላይ ስጋ የተጣፈባቸው የሚመስሉ ረጅም ሰውዬ ናቸው። ሰፋ ያለው ፊታችው ላይ የሚንቧቸሩ አይኖቻቸው በቁጣ እንደ እሳት የንቦገቦጋሉ። ፀጉራቸው ገብስማ ከሆነ ብዙ እንዳልቆየ ያስታውቃል። ምናልባት የታክሲ ተራው፣ የዋጋ ተመኑ መቸመር እና መነሳት ሳይሆን አይቀርም እንዲህ አደረጋቸው።

መንገዳችን ቀጥለናል የአቦን ማዞሪያ አልፈን ቁልቁል ወደ መከኒሳ እያዘገምን ነው። ሰውየው ነዳጅ ለመጨረስ ሳይሆን አይቀርም ቀስ እያሉ ነው የሚነዱት። “በዚህ የኑሮ ውድነት በተከፈለ  ገንዘብ እንዲህ የሚቀልዱት እንዴት ነው ጃል!” አልኩ በውስጤ። ዞር ብዬ ስመለከታቸው ፊታቸው አቧራ የተገበ አሮጌ  አሸዋ ግርፍ ይመስላል። ምናልባት የልጆቻቸው ብዛት፣ የዛሬ እራት፣ የሃገሪቷ ፍጻሜ ወይም የአባይ መገደብ ሳያበሳጨቸው አይቀርም አልኩ። ወይም ደግሞ የዋጋ ተመኑ ሊነሳ ነው የሚለውን ወሬ ሲሰሙ በሬዎች በሙሉ ወደ ከተማ መሰደዳቸውን ሰምተው ፤ የመግዣ 80 ብር ስለሌላቸውም ሊሆን ይችላል።

ረዳቱ “አንተ እስቲ አስር ብር ዘርዝር “ አላቸው። ለወትሮው ቢሆን “ደፋር አንቱ አይባልም አባትህ አይሆኑም!” እለው ነበር። ወይም አንድ በስነ ምግባር የታነጸ ድምጽ ያላት ሴት ስትል እሰማ ነበር። ነገር ግን እንዲህ አይነት ነገር  ቀርቶ ኮሽታም አይሰማም፡፤  ሬሳ የተሰከምን እነጂታክሲ የተሳፈርን አይመስልም። ሰውየው በተጠንቀቅ አሉ ይመስል ፊታቸውን ዞር አድርገው የተጠቀለለ ዝርዝር አስር ብር ሰጡት። የሰውየውን ሙሉ ፊት ስመለከተው   ደምስሮቻቸው ከፈታቸው ላይ አፈንግጠው ሊወጡ ደርሰዋል። ምን ይሆን እንዲህ ያስቆጣቸው!

ድንገት ያቺ ቀርፋፋ መኪና ሲጢጢጥ ብላ ቆመች። ቁል ቁል ወደ አስፋልቱ ስመለከት አንድ ወጣት ልጅ ሳንቲም ከመሬት ፈልቅቆ ሊያነሳ ሲሞክር። መኪናዋ ተንሸራታ አጠገቡ ስትደርስ ቆመች ልጁ ብዙም ሳይደናገጥ ሳንቲሟን ከመሬት ፈልቅቆ ተሻገረ።

የመጀመሪያው ጫሂ እኔ ነበርኩ “እንዴ!!”

ሹፌሩ ተከተሉ “ሆዳም!”

አንድ ሴትዬ “የኢትዮጵያ ሕዝብ እኮ አያስብም!” አለች ጮክ ብላ ከንፈሯን በመምጠጥ እያዳነቀች። ታከሲው ውስጥ ያለው ሰው ግን ትንፍሽ አላለም።

ውስጤ ሃሳብ ተዘራ። ሹፌሩ ለምን “ሆዳም!” አሉ? እንዲያው ሌላ የተሻለ፣ ስልጡን ስድብ ጠፍቶ ነው። ማለቴ ከተለመዱት የታክሲ ሹፌር ስድቦች አንዱ። ምናልባት እኮ ልጁ ሳንቲሟን ቆፍሮ ላመውጣት የሞከረው ስለራበው ነው ብለው ይሆን? አይ ወይስ ሃሳባቸውን ሰንጎ የያዘው በልባቸው የሞላው “የሆድ ነገር ስለሆነ ነው!”

ደግሞ የሴትየዋ “የኢትዮጵያ ሕዝብ አያስብም” ማለቷ ከምን የመነጨ ነው?  ስለ ኑሮ ውደነቱ ነው የማያስበው! ወይስ ደግሞ አንድ ወጣት የኢትዮጵያ ሕዝብን ይወክላል ብላ ነው። አላውቅም! ነው ወይ አንድ ወጣት በአንድ ሳንቲም እና በሕይወት መካከል ያለውን ልዩነት አልተረዳም ለማለት ነው

! እኔ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስባል ባይ ነኝ! አንዲያውም ይህ ወጣት እራሱ ያስባል ባይ ነኝ። እርግጥ ነው አንድ ሳንቲም ከሕይወት አትበልጥም!  ሕይወትን ለማቆየት ዳቦ ያስፈልጋል፤ ያለሳንቲም ዳቦ አይገኝም፤ ስለዚህ ሳነቲምን ለማዳን ሕይወትን አደጋ ላይ መጣል የማሰብ ምልክት አይደል።

ሁላችንስ የምናስበው ነገ ነግቶ ዳቦ መብላታችንን አይደል። ዳቦ ለመብላት ደግሞ ሳንቲም ያስፈልገን የለ፣ ሳንቲምን ለማግኘት ደግሞ እስከ ሕይወት መስወዕትነት እንከፍል የለ።

አንድ  የፖለቲካ ሰው “የተራበ ሕዝብ መንግስቱን ይበላል ያሉት!”

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s