ምን ይወራል ? News · Uncategorized

የናይሮቢ የጉዞ ማስታወሻዎች ፦ “ያ ቻይ”፣ “የስልጣን ውል”

“ያ ቻይ”

መንገድ ላይ ነው። ሰውየው የምታምር መኪናውን በፍጥነት ያሽከረክራል። ፍጥነት ቢያስደስተውም የናይሮቢን ከተማ የመኪና አደጋ በመፍራት በጥንቃቄ ያስከረክራል። ብዙም አልቆየም አንድ ትራፊክ አስቆመው።
“አባሪያኮ” አለው ትኩር ብሎ እየተመለከተው።
ባለመኪናው የመኪናውን መስታወት ዝቅ አድርጎ “ሙዙሪሳና” ብሎ መለሰለት።
“ጌታዬ መንጃ ፍቃድዎትን የስጡኝ በሰዓት ከ120ኪሜ በላይ እያሽከረከሩ ነው።” አለው ትራፊኩ ፈርጠም ብሎ።
“እረ በፍጹም የእኔ መኪና ፍጥነቷ መቶ አስር ነው!”
ትራፊኩ ከስተር ብሎ “ጌታዬ እኔ ትራፊክ እነጂ መኪና ጠጋበኝ አይደለሁም…መንጃ ፈቃድዎትን የስጡኝ? ” ብሎ አፈጠጠበት።
ሰውየው በቁጣ ገነፈለ። የመኪናውን በር ከፍቶ ወጥቶ፤
“ባልከው ፍጥነት አልነዳሁም አልኩህ አልነዳሁም! አሁን እቸኩላለሁ” ብሎ ጮሀበት።
ትረፊኩ ፈገግ አለ ፣ጸጉሩን በመዳፉ አከክ አከክ እያደረገ “ሙኩ ኢኒፔሄ ፔሳ ያ ቻይ?(ጌታይ ለሻይ ገንዘብ ይስጡኝ)” አለው።
ባለመኪናው ፈርጠም ብሎ “አልሰጥም ..ምን አጠፋሁ እና ነው የምሰጥህ?” አለው።
“ጌታዬ ይችላሉ! እኔ ብቀጣዎት አየር ማቀዝቀዣ ባለው ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሎ የሚውለው አለቃዬ ብዙ ቀን ካመላለሰዎት በሃላ በእጥፍ ይቀበልዎታል። እስቲ አስቡት ጌታዬ እኔ ሶስት ልጆች አሉኝ ባለቤቴ ምንም ስራ የላትም። እሱ ጋር ሄደው ከሚጉላሉ ለእኔ ቢሰጡኝ ይቀልዎታል።… እኛ ጸሐይ ተመተን በምናመጣው ገንዘብ እነሱ ይሞላቀቁበታል።”
የቀረውን ጨርሱት …
ይህንን ያጫወተኝ አንድ ወዳጄ ነው።
“የስልጣን ውል”

Rev. Kimutai B. Chesosi

አለም አቀፋዊቷ የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን በየጊዜው አዳዲስ ካህናትን ትሾማለች። በተለይ በኬንያ ውስጥ የምትገኘው የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ግን በአብዛኘው ኬኒያውያን ዘንድ የታወቀች ነች። በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያየሁትን እና በቤተክርስቲያን በፖለቲካውም ሊለመድ ይገባዋል የምለውን ነገር ላካፍላችሁ። የሚያስገርመው ነገር በኬኒያዋ የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ቢሾፕ ሲሾም ውል ይፈርማል አሉ። የምን ውል አትሉኝም። እኔ እከሌ እከሌ የተባልኩት በዚህ ቀን ከሌሊቱ ከዚህ ሰዓት ስለጣኔን ለቅቄ ለሚተካኝ ሰው እንደማስረክብ በመሃላ እና በፊርማዬ አረጋግጣለሁ ይላል። ታዲያ ሥልጣን ላይ ወጥተው በአመጽ ካልሆነ አንነሳም ለሚሉ በርካታ መሪዎች አያስፈልግም ትላላችሁ።
ሁለተኛውም ቢሆን የዋዛ አይደለም! ምን መሰላችሁ በዚች ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚመረጡ ቢሾፖች በየጊዜው ከተለያየ ጎሳ ነው የሚመረጡት። አሁን ኩኪዩ ፣ በሚቀጥለው ሉዎ፣ በሚቀጥላው ካልነጂ እያለ ይቀጥላል። ታዲያ በብሄር ተቧድነው ለሚናቆሩ አንዳንድ መሪዎቻችን ጥሩ መድሃኒት አይሆንም ትላላችሁ! እኔ ግን ሁለቱም መልካም ናቸው እላለሁ። ምን ይመስላችሃል?
ስለ ሌጂዮ ማርያ እና ስለጥቁሩ መሲህ ደግሞ እንጫወታለን…

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s