ምን ይወራል ? News

መጋቢ ሮብ ቤል፦ “ሲዖል የለም “!!!!!

ወዳጆቼ ማርሰ ሂል ቤተክርስቲያንን የሚያቀርባቸው ግሩም ስብከቶቹ ይመስጡኛል። ሮብ ቤል በእርግጥም ለዚህ ዶት ኮም ትውልድ የተመቸ ነው። ስብከቱን ብታዩ ወደፊት የቤተክርስቲያን  ገጽታ ቁልጭ ብሎ ታዩታላችሁ። ይህች ቤተክርስትያንም ከዚህ የአርባ አመት ጎልማሳ ፈጠራ እና “በእግዚአብሄር ፀጋ” እያደገች መሄዷን ትቀጥላለች። ታዲያ ከሰሞኑ ግን መጋቢ የጻፋት እንድ መጽሐፍ ሰዖል የለም የሚል አስተምህሮ አላት በሚል ያነበቡ ሰዎች እየተወዛገቡባት ነው።

ወግ አጥባቂ ወንጌላውያን የሚባሉት  ይሄ ሰውዬ “ገበያ” ለማግኘት ነው እንጂ ፤ አኢነዲያው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሲዖል የሚያስተምረውን ቁልጭ ያለ ትምህርት አጥቶት ነው ሲሉ። ለዘብተኞች ደግሞ አትከፉበት አዳምጡት ይላሉ። እስቲ አንድ ነገር እናስቀድም እና ግራ ቀኙን እናዳምጥ።

ታይም

በተይም መጽሄት ላይ “ሰዖል የለምን?” በሚል ርዕስ የጻፈው  ሰው ሮብ ቤልን ባሞካሸበት ጽሑፍ እንዲህ ሲል ገልጦታል ። “የማህበራዊ ድረ ገጽ ን በመጠቀም ረገድ የሚተካከለው የሌለ” በተጨማሪም “ብዙ ወጣት ተከታዮችን ያፈራ የወንጌላውያን መጋቢ” ብሎታል። ታይም መጽሔት በዓለማችን ላይ ተጽዕኖ ከፈጠሩ 100 ሰዎች መካከል አንዱ በማድረግ  በ2011 መርጦታል። ከተመረጡት መካከል ብቸኛው የወንጌላውያን ተወካይ እንደሆነ ልብ ይበሉ። ቀሪውን ከእዚህ ያንብቡ።

ኒውስ ዊክ 

የመጋቢ ሮብ ቤል አዲስ መጽሐፍ LOVE WINS: A Book About Heaven, Hell, and the Fate of Every Person Who Ever Lived  ፡የተሰኘው እና በብዙሃን ሲዖልን ይክዳል ተብሎ የሚታሰበው መጽሐፍ  በኒውስ ዊክ የመጽሐፍት ሽጭ ሰንጠረዥ ውስጥ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።እዚህ ይጫኑ።

ተዋቂው ክርስቲያን ብሎገር  ፔሪ ኖቤል

ከሮብ ቤል ጋር እንደሚቀራረቡ  ነገር ግን በሰዖል ዙሪያ ያስተማረውን ትምህርት “ስህተት” ሲል ይገልጠዋል። ከዚሁም ጋር አያይዞ መጽሐፉን ለማስተዋወቅ በጉዞ ላይ የሚገኘው ሮብ ቤል፤ እባካችሁ በነገሩ ላይ በጥሞና እንነጋገርበት ሲል ጥሪ ማቅረቡን አያይዞ ይገልጣል።

ጆን ማካርተር

ከሁሉ በላይ በሮብ ቤል መጽሐፍ  ክፉኛ የተበሳጨ የሚመስለው ታወቂው ሰባኪ እና የመ{ኢሃፍ ቅዱስ ምሁር ጆን ማካርተር ነው ። ጆን ማከርተር በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ  ሰፋ ያለ ሀተታን “የቤል ሲዖል” አውጥቷል።  እሰቲ ከሮቤ ቤል አዲስ መጽሐፍ ውስጥ የጠቃቀሳቸውን  ነገሮች ላስነብባችሁ፦

“ሰዎች ሰዖል የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ ምን ማለታቸው ነው? ቦታ ፣ሁነት ፣ ሁኔታ  ፤ እግዚአብሄር ቢፈለገው መንገድ ሳይሆኑ ሲቀሩ ለማለት ፈልገው ነው። ረሃብ፣ ዕዳ ፣ ጭቆና ፣ ብቸኝነት፣ ተስፋ መቁረጥ ፣ ሞት እና ጭፍጨፋ .. ሲዖል በምድር ላይ ማለት ናቸው። ኢየሱስ ለተከታዮቹ የሚመክረው ደግሞ በአኗኗራቸው ገነትን በምድር ላይ እንዲያመጧት ነው።”

“ በኢየሱስ አስተምሮ ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ቢሆን እንኳን  እራሳችንን እንደ ሃጢያተኛ እንድንቆጥር የሚያደርገንን ቦታ አላየሁም።”

እባክዎ ቀሪውን  ከራሱ ከጆን ማከርተር ያንብቡት።

የሮብ ቤል ደጋፊዎችም ትችቱ በዝቷል ይላሉ?

ሪቻርድ ጄ ሞው

የፉለር ቲዮሎጂካል ሴሚናሪ መምህር እነዲህ ይላሉ ፦

“ብዙ ሰዎች እንዲገቡ መነግድ ጠርጓል ብለው ሮብን የሚወነጅሉት ሰዎች ለምንድን ነው ብዙ ሰዎች እንዳይገቡ የሚከለክሉት ? ለምንድን ነው ሁላችንም “በተትረፈረፈ መዳን” እና  “በቆንቋና መዳን” ላይ እርር ያልነው።”

ብሬያን ማክሌረን

“ ሮብ ቤል ይህንን መጽሐፉን ሲያሳትም በእኔ ላይ እንደ ፀሐፊ የደረሰው  ነገር በአዲሱ መጽሐፉ ሊደርስበት  እንደሚችል ገምቼ ነበር። አባቶች  ከጣላት ጥቃት ይልቅ የወዳጆች ዝምታ ያቆስላል እንደሚሉት ለሮብ ለመናገር እድሉን ስጠብቅ ነበር” በማለት ዶክተር አልበርት ሞህለርን በመጣጥፋቸው ይተቻሉ።

“ እሱ ሊሳሳት ይችላል፤ ነገር ግን ከተሳሳትን ስህተት የሚሆነው ከዘመኑ ጋር ለማስማማት ስለፈለግን ነው  ተብሎ መታሰብ የለብትም።”

አስደናቂውን እሰጥ አገባ በሰፊው እዚህ  በመጫን ያንብቡ

ግራ ቀኝ ሙግቱ  አሁንም እንደቀጠለ ነው ።

ከሁሉ በላይ  ያስደነቀኝ ምልከታ ግን የታይም መጽሔት አርታኢ የሰጠው አስተያየት ነው። ማክሄይም እንዲህ ይላል፦

“ክርስቲያን መሆን ማለት ምን ማለት ነው ለሚለው ጥያቄ የመሰጠው መልስ እየተለወጠ ሳይመጣ አልቀረም?”

የእኔም ፍርሃት እና ስጋት ይሄ ነው። ለመሆኑ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?

Advertisements

2 thoughts on “መጋቢ ሮብ ቤል፦ “ሲዖል የለም “!!!!!

  1. አብነት
    ይህንን የዩኒቨርሳሊዝምን ትምህርት ሮብ ቤል እንድ አዲስ ቢያቀርበው አይደንቀኝም። ነቀፋን ከጠላን አለምንንም ከወደድን የክርስቶስን ትምህርት ማስተማር እጅግ ከባድ ነው።ለዚሁ ምሳሌ የሚሆኑንተቀባይነትንና ተሰሚነትን ለማትረፍ ክርስቶስን ከመስበክ ፈቀቅ ያሉ አያሌ መጋቢዎቻችን ናቸው። ምናልባት ኢየሱስም ሆነ ሌሎች ሀዋርያት የአሁኗን ቤተክርስትያን አስትምህሮ ቢያዩ ልክ እንዳልከው ክርስትያንነታችንን በጥያቄ ያስገቡታል ብዬ እገምታለሁ። ስለዚህ የማንነት ጥያቄ ማንሳትህ እጅግ ተገቢ ነው። ለነገሩ የክርስቶስን ትምህርት ብቻ ሳይሆን ማንነቱን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ትምህርት የሚሰጥበት አብያተ ክርስትያናት ሞልተውን የለ? መጨረሻችን ምን ይሆን?

  2. ጆኒ አመሰግናለሁ። እንዳልከው የዚህ የስህተት ትምህርተ ምንጭ፣ ነቀፋን መጥላት እና አለምን መውደድ እንደሆነ እስማማለሁ። ከዚያ ባሻገር ግን አሁንም የሚያስገርመኝ ነገር፤ በተለይ ከዚህ ከድህረ ዘመናዊነት በተለይም “ሥልጣንን” ከመጥላት ለሚመነጩ ለእነዲህ አይነት ትምህርቶች ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ተዘጋጅታለቸ ወይ የሚለው ነው። እኛ ጉያ ስር የተሸሰጉትንስ “መምህራን” እነዴት ነው መንጥረን በመጽሓፍ ቅዱስ ሚዛን ላይ መፈተሽ የምንችለው የሚለው ነው ትልቁ ጥያቄ?

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s