መጣጥፍ Articles

የስኬታማ አገልግሎት መለኪያ፡ – ውጫዊ መገለጥ ወይስ ውስጣዊ ማንነት?

በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎችን አንድ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው ብላችሁ ብትጠይቁኝ በርካታ መልስ ልሰጣችሁ እችላለሁ። ከመልሶቼ መካከል በጣም በእርግጠኝነት ልናገረው የምችለው ግን ስኬት ነው። ስኬት ማለት በሆነ  ልንሰራው ባሳብነው ነገር ዙሪያ የምንፈልገውን ውጤት ማግኘት ማለት ነው። ስኬታማ መሆን በዚህ ዘመን በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል ዋነኛ ለመሆኑ ማስረጃ የሚሆነን አካባቢያችንን መመልከት እና ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር መጠየቅ ብቻ ይመስለኛል ።ከእያንዳንዱ ለጥያቄያችን ከሚሰጥ መልስ ጀርባ በምንም ነገር ስኬታማ ለመሆን መፈለግ ዋነኛው ነው። ተማሪው በትምህርቱ  ስኬታማ ሆኖ ኢነጂነር ፣ዶክትር ለመሆን ይፈልጋል ። አስተማሪው በደንብ አስተምሮ ስኬታማ መምህር  መሆን ይፈልጋል። ነጋዴው ስኬታማ ነጋዴ ሆኖ ማትረፍ ይፈልጋል። ፖለቲከኛው በፖለቲካው ጥሩ ተሰሚነት አግኝቶ ስኬታማ መሆን ይፈልጋል። እኔም እንደፀሃፊ ስኬትን መፈለጌ የማይካድ ነው። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ስኬትን መፈለጋቸው በጣም ጠቃሚ ይሁን እንጂ የአገልጋይን ያህል  በአግልግሎቱ ውጤታማ መሆን ያለበት ሰው አለ ብዬ ለመናገር  ስፈራኛል። በዚህች አጭር ፅሁፌ ግን የአገልግሎት ስኬትን መፈለግ መልካም ቢሆንም መለኪያው ምን መሆን እንዳለበት ማሳየት እፈልጋለሁ። ለዚህም እንዲረዳኝ በመጀመሪያ የዘመኗን ቤተክርስቲያን የስኬት መለኪያ አሳያለሁ በመጨረሻም በመፅሃፍ ቅዱስ ሚዛን ላይ አሰቀምጬ የመፍትሄ አቀጣጫን በማሳየት አበቃለሁ።

በዚህ ዘመን በወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የአገልግሎት ስኬት የሚለካው በተለየዩ መንገዶች ቢሆንም አንድ ሶስቱን መጥቀስ ግን ግድ ይለኛል። የመጀመሪያው የአገልግሎት መለኪያ የአግልግሎታችን የአገልግሎት አድማስ መስፋት ነው። እንደ ቤተክርስቲያንም ሆነ እንደ የአልጋዮች ስኬት የሚለካው በሄዱባቸው የአገልግሎት ስፍራዎች እና የተገልጋኦች ብዛት ነው። ሐገር ውስጥ ብቻ የሚያገለግሉን ሰዎች በቁጥር ስንለካቸው ወደ ውጭ የሂዱትን ደግሞ በሄዱባቸው የሀገር ብዛት እንለካቸዋለን።

ሁለተኛው የአገልግሎት መለኪያ ደግሞ መልዕክት የማምጣት ብቃት ነው። አንድ አገልጋይ ምንም አይነት ጥቅል መልዕክትም ያምጣ (ምሳሌ፦ “እግዚአብሄር ይባርካችሓል”)፤ ወይም ደግሞ  ግለሰባዊ መልክእት ያምጣ (ለምሳሌ ፦ “ጌታ ቀንበርሽን ሰብሬያሁ ይላል።”) በአጠቃይ ለህዝቡ መልዕክት የሚያመጣ አገልጋይ ትንቢት የሚናገር “መገለጥ አለው”  እንላለን። ከዚህ ጋር የተያያዘው ሌላ መስፈርታችን ደግሞ አጋንንትን ማስወጣት ነው። አንድ በቅርብ የማውቀው አገልጋይ ቤተክርስቲያን ውስጥ የአገልግሎት ስፍራ ለማግኘት ወይ “አጋንንት መስወጣት አለብህ ወይም ትንቢት መናገር አለብህ” ያለኝ የቅርብ ጊዜ ትዝታዬ ነው።የመጨረሻው የአግልግሎት ስኬት ጣራ ላይ ለመድረሳችን ማረጋገጫው ፈውስ ነው። የፈውስስጦታ አለው አግልጋይ ያለበት ቤተክርስቲያን ምሳሌነቷ ለብዙ ነው።

ከእነዚህ ከላይ ከዘረዘርኳቸው እና ካልዘረዘርኳቸው ነገሮች በመነሳት የአገልግሎት ስኬት መለኪያችንን ማስቀመጥ ይምችል ይመስለኟል። በመሆኑም በአብዛኛው በወንጌለውያን አቢያተክርስቲአናት ምእመናን መካከል የአገልግሎት ስኬት የሚለካው በውጭ በምናሳየው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መገልጥ ነው።የስኬታማ አገልግሎት መስፈርታችን የሚታይ (የተገለጠ) ውጤት ነው። ለመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ስኬታማ አገልግሎት የሚለው ምን አይነት አገልግሎት ነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ ኸማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ጀምሮ የታራራው ስብከት ብላን በምንጠራው ክፍል መጨረሻ ምዕራፍ 7 ስለ ሀሰተኛ ነቢያት የሚያወራበት ክፍል ይገኛል። በዚህ ክፍል መደምደሚያ ላይ (ቁ.21-23)የስህተት መምህራንን በፍሬያቸው የምንለይበትን መንገድ በግልፅ ካሳየ በሓላ በመጨረሻው ዘመን የአግልግሎት መስፈርታቸውን ይዘው ስለሚቀርቡ ሰዎች ይናገራል። ሰዎቹ “በዚያን ቀን” በዳግም ምፅዓቱ እና ፍርድ በሚሰጥበት ቀን እንዲህ ብለው መስፈርታቸውን ያቀርባሉ፤ “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህትንቢት አልተናገርንምን ፤በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን ፤ በስምህስ ብዙ ተዓምራትን አላዳረግንምን?”። እነዚህ ሰዎች ያሉት በአገልግሎታችን ስኬታማ ስለሆንን ወደ መንግስትህ ይገባናል።ምክንያቱም 1) በስምህ ትንቢት ተናግረናል። 2) በስምህ አጋንንትን አስወጥተናል። 3) በስምህ ብዙ ተዓምራትን አድርገናል። የኢየሱስ ክርስቶስ ምላሽ ግን ሁለት ገፅታ ያለው ግልፅ ነበር። አንደኛ  ወደ መንግስቴ ሊገባ የሚችለው ስሜን የሚጠራ ሳይሆን  የአባቴን ፍቃድ የሚያደርግ ነው። ለመሆኑ የአባቱ ፍቃድ ምንድን  ነው? (ማቴ .7፡19፣12፡50 ይመልከቱ)። ሁለተኛ ወደ መንግስቴ ሊገባ የሚችለው “ ዓመፀኛ”[1] ያልሆነ ነው ። ዓመፀኛ የሚለውን ቃል መፅሃፍ ቅዱስ በተፃፈበት ቋንቋ ስናጠነው ። “ ህግ እንደሌለ እያሰቡ መኖር የሚል ትርጉም” አለው።

በአጠቃላይ ስንመለከተው  ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህ “ስኬታማ ነን ሽልማት ይገባናል” የሚሉ አገልጋዮችን “ውጫዊ መስፈርት” ( ትንቢት ፣አጋንንት ማሰወጣት እና ተዓምራት ማድረግን) አልካደም ነገር ግን በጣም አስፈላጊው ነገር ምን እንደሆነ ግን ያስታውሳቸዋል ይውም የእግዚአብሄርን ፍቃድ መፈም ነው። የእግዚአብሄርም ፍቃድ የእግዚአብሄርን ህግ አክብረው እንዲኖሩ ነው ።ህግን የሚያከብሩት የብሉይ ኪዳንን ህግ በመጠበቅ ሳይሆን የህግ ሁሉ ፍፃሜ የሆነውን ፍቅር በህይወታቸው በመግለጥ ነው(ማቴ.22፡28-30)።

ስለዚህ የዚህ ዘመን መስፈርታችን በኢየሱስ ሚዛን ላይ ስናቆመው ቀሏል። ስለዚህ የግል አገልግሎታችን መለኪያ የመናሳየው “ውጫዊ መገለጫ” በቻ ሊሆን አይችልም።ይሄ “ውጫዊ የስኬት መገለጫ”ን በመንፈስ ቅዱስ እየተሞላን በምንኖረው ዕለታዊ ህይወት ካለተደገፈ የሰኬታችን ፍፃሜ የሚሆነው አላውቃችሁም ነው።[2] ይህን ፅሁፌን  አንድ አስተማሪ በሰጡን ማስታወሻ ላይ ባገኘሁት ጥቅስ ላጠቃል “የእግዚአብሄር ህልውና በመሀላችን መገኘት እና መስራት የእኟን መንፈሳዊነት(“ስኬታማነት” እንደሚያሳይ አድርገን መቁጠር አደገኛ ነው።”


[1] ይሄ የግሪክ ቃል በግሪክ አኖሚያ የሚል ሲሆን ትርገዋሜውም 1) ህግ እንደሌለ በማሰብ መኖር 2)ህግን ሙሉ በሙሉ አለመታዘዝ 3)ህግን ሁሉ እያንቋሸሹ መኖር

[2] የግሪኩን ቃል ስንመለከተው የሚያሳያው ላልተወሰነ ጊዜ ወደፊትም አለማወቅንም ጭምር ስለሆነ “አላወቅኳችሁም አላውቀችሁም” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ብዬ አስባለሁ።

Advertisements

One thought on “የስኬታማ አገልግሎት መለኪያ፡ – ውጫዊ መገለጥ ወይስ ውስጣዊ ማንነት?

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s