ምን ይወራል ? News

ኬንያ ዶት ኮም ፦ የኬንያ ፍንዳታዎች

ኬኒያ ዶት ኮሞች ዕድሜያቸው በግምት ከ15-25 የሚደርስ ወጣቶች ናቸው።  ብዙዎቹ በሚያስገርም ሁኔታ የጥቁር አሜሪካውያንን አለባበስ አነጋገር አስገራሚ በሆነ ሁኔታ የተላበስ ናቸው ።  ብዙዎቹ ተግባቢዎች ናቸው። ከኬንያውያን መካከል እነደ ኬኒያ ዶት ኮሞች የሳበኝ የለም። ሁሉም “ሃይ ሜን” ሳይሉኝ አልፈው አያውቁም (ከሴቶቹ በስተቀር )።

ሁልጊዜ  ለአምለኮ ወደ አዳራሽ ሲገቡ እንኳን ከጆሯቸው ላይ ኢር ፎን አይለይም። የሚያስገርመው ነገር ለሙዚቃ ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው። ልክ እንደኛ አገር እንሱ ጋር ሙዚቃ ሃጢያት አይደለም። ዶርም ውስጥ እ ሉ እንኳን ሙዚቃ ዝቅ አድርጎ መስማት ይከብዳቸዋል። ብዙ ጊዜ ከእንቅልፌ የሚቀሰቅሰኝ የእነሱ ሙዚቃ ነው። በኢር ፎን እነኳን ሲያዳምጡ ይሰማል።

የኬኒያ አምለኮ ትንሽ ከብዶኛል። እናንተዬ እንዴት ነው “ዳሌ የሚያወዛውዝ” የአፍረካ ዳንስ የአምልኮ ሙዚቃ ሊሆን የሚችለው። በዚህ አጋጣሚ በአዘማመራቸው የነቀፍኳቸውን አንዳንድ ወዳጆቼ ይቅር ማለት እፈልጋለሁ። በሃገሬ ያለች ውዝዋዜ ፣ዝማሜ እና ዝላይ ማሪኝ ብያለሁ።  በኬንያ ዶት ኮሞች ዘንድ ግን አምለኮ እና ጭፈራ ተመሳሳይ ናቸው። አንዳንዴ ስቅጥጥ ይለኝና ሃጠያት እየሰራሁ ይሆን ስል ራሴን እጠይቃለሁ። ብቻ አምልኮ ላይ ጭፈራው ይቀልጣል። ኬኒያ ዶት ኮም!

ኬኒያ ዶት ኮሞች ትንሽ ወግ አጥባቂ የሆነ ቤተክርስቲያን አይወዱም። በተለይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እያስተነተነ የሚሰብክ ሰው ከጋጠማቸው ሞባይሎቻቸውን ከፍተው እየተሳሳቁ የጽሁፍ መልዕክት ይቀያየራሉ። አንዲያው ምነው መጋቢ እከሌን በዛዘባቸው እላለሁ።

ኬኒያ ዶት ኮሞች ውበትን ማድነቅ ያውቁበታል። አደናነቃቸው ግን ግራ የሚያጋባ ከየት እንደመጣ እገዜር ይወቅ። “ቅርጿ የላፕ ቶፕ ይመስላል!” ካሉ ያቺ ኮረዳ ውበቷ ዳርም ይለው ማለት ነው። አልፎ አልፎ ሲባል የምንሰማውን “ስምንት ቁጥር” ማለት ነው።

የእነዚህ ፍንታዎች ቋንቋ ሼንግ ይባላል። ሼንግ ማለት እኛ የአራዳ ቋንቋ እንደምንለው ነው። ለምሳሌ በኪስዋህሊ ሽማግሌ ሽማግሌ ማለት “ሙዜ” ነው። በሼንግ ግን “ቡዳ” ወይም “ምቢዩ” ይሉታል።

በእነዚህ ወጣቶች ዘንድ የግበር ሥጋ ግንኙነት ማደረግ ማለት በዕምነት የሚገደብ አይደለም። አንዳንድ ያወራሃቸው ወጣቶች ሃጢያት መሆኑን እንኳን አያውቁም ብለውኛል። አንዳንዶቹ ከነማን እንማር አገልጋዮቹም እንደዚያ ው ናቸው ሲሉ ይሟገታሉ። ኬኒያ ዶት ኮሞች ሲጋራ እና ዕጽ ላይም የሚተካከላቸው እንደሌለ ሹክ ያሉኝ አሉ። ብቻ ግራ የተጋቡ እና በምዕራባውያን ቁሳዊነት የተሞሉ ወጣቶች ናቸው።

ተስፋቸው ምንድን ነው? የአንግሊካን ቄስ የሆኑት ቼሶሲ እንዲህ ይላሉ ። “ምንም !” ። ቢሾፕ ጄፈረሰን ግን በዚህ አይስማሙም። ” ተስፋ አለ ግን እነዚህን ወጣቶች ልናዳምጣቸው ይገባል ” ይላሉ።

ወዳጆቼ ኢትዮጵያ ዶትኮሞችስ? እነሱን ማን ያዳምጣቸው?

ብቻ የኬንያ ክርስትና አንደ ገጽታ ይሄ ነው?

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s