Uncategorized

የናይሮቢ የጉዞ ማስታወሻዎቼ

“ጉቦ”  ለቤተክርስቲያን፣አደቬንቲስት እህታችን፣  “የመሞካከር ጥግ”፣ የኢትዮጵያ “ውሃ”

Blogging
ዶርም ውስጥ

ኬንያውያን ገንዘብ ይወዳሉ።(ኦሆ ሁሉም ማለቴ አይደለም) በተለይ እኛ ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ደግሞ ያለ ገንዘብ ፈገግ እንኳን የማይሉ ናቸው። አንዳች ነገር ያለ ገንዘብ ማደረግ አይቻልም? በትብብር ማበደር የሚባል ነገር በዚያ ጊቢ ውስጥ አይታወቅም። ልክ ናቸው ወይም ክርስቲ ኖች አይደሉ እንዴ አንተን መተባበር አለባቸው ልትሉ ትችላላችሁ። እውነት ነው! ግን ገንዘብ ይወዳሉ!  እስቲ ገንዘብ የሚጠላ እጁን ያውጣ!

“ጉቦ ለቤተክርስቲያን”

ዛሬ በመማሪያ ክፍልችን ውስጥ ትልቅ የሙግት አጀንዳ የነበረው ቤተክርስቲያን ደክማለች ወይስ አልደከመችም የሚል ነበር። አንድ የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አባል የሆነ ወዳጄ እና አንድ የጴንጤቆስጣል  ቤተክርስቲያን ተማሪ የሆኑ ወዳጆቼ ዱላ ሊነሳሱ እስኪደርስ ተሟገቱ። ለካ ሰሞኑን መንግስ ለቤተክርስቲያን አባለት “ጉረሻ ” እየሰጠ ሰሞኑን  ሰልፍ እንዲወጡ እያደረገ ነው።  ይህ ነበር አንግሊካን ወዳጄን ያስቆጣው ” እሰከመቼ ነው የራሳችን ድምጽ የማይኖረን 85% ክርሰቲያን ባቀፈችው ኬንያ ለምን ቤተክርስቲያን ተጽዕኖ መፍጠር ተሳናት ሲል  እንዲጠይቅ የተገደደው። ትክክለኛ ጥያ ቄ ይመስለኛል። በጅማው ጭፍጨፋ ጊዜ ድመፃቸውን ያጠፉ የእኛ መሪዎችስ ምን ሊባሉ ይሆን? ለማንኟውም እዚህ ኬኒያ ውስጥ ቤተክርስቲያን በበላችበት የምትጮህ ስለመሆኗ ከራሳቸው አንደበት ሰማሁላችሁ።

“አድቬንቲስት”

በእኛ ክፍል ውስጥ በግምት ወደ ሃያ የምንሆን ተማሪዎች የምንማር ሲሆን ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል አንድ ሱዳናዊ ፣እኔ እና አንድ ላይቤርያዊ ብቻ ስንገኝ ሌሎቹ በሙሉ ኬኒያውያን ናቸው። በክፍላችን ውስጥ ሁለት  የአንግሊካን እና ሁለት የናዛሪን ቤተክርስቲያን ሰዎች ሲገኙ ሌሎቹ በሙሉ ከተለያየ  ቤተ እምነት የመጡ ናቸው። ያስገረመኝ ነገር ግን ውስጥ ውስጡን በነገር ቢወጋጉም በመካከላቸው ግን የሚያስገርም “መቻቻል” አይቻለሁ። የመቻቻላቸውን ጥግ ግን ያየሁት የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አባል የሆነችን እህት ትምህርት ቤቱ ውስጥ መቀበላቸው ብቻ ሳይሆን “እህት” ብለው መጥራታቸው ነው። በሺዎች የሚቆጠር ቤተ ዕምነት (ዲኖሚኔሽን) በለባት አገር “ከለመቻቻል ” እንዴት ይኖራል ብላችሁ ነው።

“የመሞካከር ጥግ”

አንድ ወጣት ልጃገረድ እና አንድ ወጣት ጎረምሳ አንድ ቤት አብረው መኖራቸው በኬኒያውያን  ክርስቲያኖች ዘንድ ብዙ አጀብ የሚያስብል አይደለም። በግርድፉ እንደተነገረኛ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ከመጋባታቸው በፊት አንድ ላይ በመኖር ይሞካከራሉ። ለዚህ ደግሞ ፍንጭ  እንዲሰጠን  እማኝ ፍለጋ የትም መሄድ አያስፈልገንም።  ነፋስ ለመቀበል በወጣሁ ጊዜ ያየሃቸው ተማሪዎች ያለምንም ሃፍረት በፊት ለፊቴ ከንፈር ገጥመው ሲተሻሹ ማየቱ በቂ ነው።  የምዕራባውያን ሸቀጥ ማራገፊያ መሆናችንን በቸልታ ለሚመለከቱ ሰዎች እንዲህ እላቸዋለሁ፦

“በኬንያ ወንድ እና ወንድ ተያይዞ መሄድ ነውር  ነው..ምክንያቱም ግብረ ሰዶማዊ ያስብላል”

የኢትዮጵያ “ውሃ”

"አይታመንም!"

እኔ እየተማርኩ የኢትዮጵያ ውሃ ሥራዎች ቡድን ከኬንያ ማረሚያ ቤት ተጫውቶ ሶስት ለዜሮ  ተሸነፈ። እሁድ እንዳላኮሩን ዛሬ የኬኒ ዎች መዘባበቻ ሆንን። ወዳጄማ ጭራውን ቆልፎ ከአካባቢው እንደተሰወረ ነገረኝ። እኔ ግን ኮርቼባቸዋለሁ ! እስከ ሩብ ፍጻሜ ተጉዘዋል። 3-0 ቢሸነፉም ምንም አይደል ። ኬኒያውያን የስድብ መዓት በኪስዋህሊ እንዳወረዱባቸው ነገሮኛል። እረ እንኳን አልሰሙት!

ነገ ስለስኬታማ መጋቢዎች፣ “ኬኒያ ዶት ኮም” ስለሚባሉ ወጣቶች፣ “የተባረከ” ውሃ እና ዘይት ንግድ እንጨዋወታለን።

እናነተስ ከእኛ አገር ክርስትና ጋር ስታነፃፅሩት ምን ትላላችሁ?

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s