ምን ይወራል ? News

የናይሮቢ የጉዞ ማስታወሻዎቼ “FIRST IMPRESSION”

ዛሬ እሁድ ነው።

ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ በወዳጅ ጓደኞቼ ተቀባይነት ስገባ ግቢው ጭር ብሏል። በር ላይ የሚገኘው ጥበቃ የያዝኳትን ‘ላፕ ቶፕ’ እንዳስመዘግብ ጠየቀኝ። ፈገግ ብሎም አዲስ ተማሪ ነህ አይደል። አንድ የማውቀውን ተማሪ ጠርቱ ቁጭ እኮ እሱን ነው የምትመስለው አለኝ። ለራሴ “ለምንድ ነው ሁሉም ኢትዮጵያውያን እከሌን ይመስሉኛል” የሚሉት አልኩ።

ብቻ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ገባን።

“ካሪቡ” (እንኳን ደህና መጣችሁ!)

“አሳንቴ!” (እንኳን ደህና ቆዩን!)

“ሃበሪያኮ” (እንዴት ናችሁ!)

“ሙዙሪ!” (ደህና ነኝ)

በኪሲዋህሊኛ እያልኩ እየተባባልኩ ወደ ገባሁ ቅጥር ግቢው። (እነዚህን ልጆች ግን አማርኛ ማስተማር የተልዕኮዬ አካል መሆን አለበት።

ግቢው የገነትን “ቁራጭ” ይመስላል። ግቢው ውስጥ በርካታ የሚያማምሩ አበባዎች ይፍለቀለቁበታል። ወደ አስተዳደር ብንሄድም አንድም ሰው አላገኘንም። ከፍተኛ አቀባበል ያደረገልኝ ወዳጄ ወደ ራሱ ‘ዶርም’ ወሰደና ዶርሙን እንድጋራው ጋበዘኝ። ክፍሉ ሁለት ተደራራቢ አልጋና አንድ አልጋ ወደ ግድግዳው ተጠግቶ ተቀምጦበታል። ክፍሉ ልክ እንደማንኛውም ተማሪ ክፍል ዝብርቅርቅ ያለ ነው። ወዳጄ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገሮች ወደዚህ “ክርስቲያን” ዩኒቨርስቲ የመጡ ተማሪዎችን አስተዋወቀኝ። ከኮንጎ፣ ከብሩንዲ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳን የመጡ በርካታ ተማሪዎች አሉ።

ከሱዳን የመጣ አንድ ወዳጄ  የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ገነትን ለማስመሰል እየተዘጋጁ እንደሆነ መሰከረልኝ። በልቤ “ጌታ ይርዳችሁ!” አልኩና። በአንደበቴ ግን “የሄ ፔትሮ ዶላር እንዳያጣለችሁ!” አልኩት ፈገግ ብሉ ዝም አለኝ። እንዲያው እኮ የሄ የፔትሮ ዶላር ገንዘብ ፍቅር የጦርነት ሁሉ ስር ሆነኮ።

ወደ ‘ካፍቴርያው” ስንገባ ሰፊ እና የሚያስፈራ አዳራሽ ነው። ዙሪያዬን ስመለከት በዚህ “ክርስቲያን” ዩንቨርስቲ ውስጥ የማያቸው ወጣቶች ግር የሚያሰኙ ናቸው። አንዱ ድርም ውስጥ ቁጭ ብሎ በታላቅ ጩሀት የማርያ ኬሪን ዘፈን ያቀነቅናል። ሴት ተማሪዎች ጥግ ይዘው ወደ እኔ እና ወዳጄ አቅጣጫ እየተጠቋቆሙ ይንሾካሾካሉ። ወደ ምግብ አብሳዮቹ ጠጋ አልን እና እኔ እና ወዳጄ እጃችንን የተለመደውን ሰላምታ አስቀድመን ዘረጋን።

ሩዝ በትልልቁ ተከትፎ ከበሰለ ሥጋ ጋር እና በሚያስጠላ የላሰቲክ ኩባያ ውሃ ተሰጠን። እንጀርዬ ደህና ሰንበች አልተገናኝተን አልኩ በሆዴ። ጓደኛዬ እንጀራውን ለኮፍ ለኮፍ ሳደርግ ፣ ዙሪያዬን ደጋግሜ ስገላመጥ አየኝ እና  ከት ብሎ ሳቀብኝ። ሳቁ ውስጤ ጥያቄዎችን ፈጠረ። ምንድን ነው የሚያስቀው ገና ብዙ ነገር አለ ለማለት ነው። ወይስ ሌላ ሚስጢር አለው። እኔንጃ እሱ ከት ብሎ በሚስቅበት ጊዜ ዙሪያችን ቁመተ ረጃጅም  ኮረዶች ፈገግ ብለው ሲመለከቱን ነበር። ትንሽ ፍርሃት ቢጤ ውስጤን ወረር አደረገው። ነገም ሌላ ቀን ነው።

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s