ምን ይወራል ? News

የናይሮቢ ጉዞ ማስታወሻዎቼ

“ውሃ ውሃ..ያ…ያያ ወይኔ…. ውሃ ”

ኳስ አልወድም። ከስፖርት ውድድሮች መካከል ምናልባት ቅርጫት ኳስ የሚስበኝ ይመስለኛል። በተለይ ደጋፊ ልሆን ቀርቶ ሰው ሲደግፍም በትዝብት የማይ አይነት ነኝ። አስታውሳለሁ የዓለም ዋንጫ በሚካሄድበት ጊዜ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝቼ “ጎል” ተብሎ ሲጮህ ተነስቼ ዳግም ሲያሳዩ ነበር የማየው። ዛሬ ምሽት የደረሰብኝ ግን የሚያስገርም ነው።

ዶርም ውስጥ ቁጭ ብለን ነበር ስልክ የተደወለው የኢትዮጵያ ልጆች እኛ ያለንበት ዩኒቨርስቲ ድረስ መጥተው ሊጫወቱ ነው። እየሮጥን..ወደ ጨዋታው ሜዳ ስንሄድ በእርግጥም እየተሟማቁ ነበር። የኢትዮጵያ ልጆች ..የእጅ ኳስ ጨዋታ ሊያደርጉ ወደ ዩኒቨርስቲያችን ድረስ መጥተዋል ሲባል ነበር እየበረርን ወደ አዳራሽ የሄድነው ። ገና ሳያቸው ነበር አንጀቴ የተንሰፈሰፈው። ቀይ አጭር ቁምጣቸውን አድርገው ውሃ ሰማያዊ ማልያቸውን አጥልቀው ሜዳ ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲሉ “አገሬ ናፈቀችኝ”። ከተመልካቾችም መካከል የኢትዮጵያን ባንዲራ እንቅ አድርገው አቅፈው በደስታ ስሜት የሚቁነጠነጡ ኢትዮጵያውያንን አየሁ። አንተዋወቅም ግን ተቃቀፍን! (ምነው ባገራችን እንዲህ ብንዋደድ)

ጨዋታው ተጀመረ። ከኬንያ ብሄራዊ ባንክ ቡድን ጋር ሊገጥሙ የመጡት የ “ውሃ ስራዎች” የእጅ ኳስ ቡድን አባላት እንደሆኑ አወቅኩ። ጨዋታው ተጀመረ የኬንያ ደጋፊዎች ግን የዩኒቨርሰቲያችን ተማሪዎች።ጭፈራውን አቀለጡት። እኛም አብረውን ካሉት ኢትዮጵያውያን ጋር እንደቀልድ የጀመርነው ድገፋ ወደ ምር ተቀየረ እና ማሊያቸው ላይ ባለው ስማቸው መጣራት ጀመርን።

ሊሊ፣ዮዳ፣ሪታ፣እሙ፣….

የሃገራችንን ባንዲራ እያውለበለብን ጩሀቱን ተያያዝነው። ጩሀታችንም ሆነ ፍቅራችን ግን ብዙም አለቆየም በኬኒያውያን ድል እና በደጋፊዎቻቸው ጩሀት ተዋጠ።

የመጀሪያውን ዙር ስንሸነፍ ኢትዮጵያን ይደግፉ የነበሩት በርካታ ሰዎች ሄደው እኔ፣ጓደኛዬ አንድ ከቡድኑ በአካል ጉዳት የተለየች ወጣት እና በኪሲዋህሊ የሚለፈልፍ ወጣት  ብቻ ቀረን።

ሁለተኛው ዙር ላይ እንደምንም እኩል ወጡ። የእኛም ፣የኬንያውያን ደጋፊዎችም ድምጽ ቀነሰ። ሶስተኛውን ዙር የእኛ ልጆች ወጥረው ይዘው አሸነፉ። ከዚያ በሃላ ያለውን እንኳን መናገር አልችልም። የጩሀቱ ዋነኛ አካል ሆንኩ። ባንዲራ ተውለበለበ። እልልታ፣ፉጨት ቀለጠ።

ባልታሰበ ሁኔታ ከሃላ የተነሱት ኢትዮጵያውያን ጨዋታውን በድል ደመደሙት። ከዚያማ ምን ልባበላችሁ በምድረ ጊቢው ውስጥ የምንገኝ ሁለት ኢትዮጵያውያን ከወገኖቻችን ጋር ተቃቀፍን ተሳሳምን፣ተላቀስን። “ውሃም” ለሩብ ፍጻሜ አለፈ። የሚያስደንቅ ምሽት በትምህርት ቤቱ ውስጥ የምንገኝ ሁለት ኢትዮጵያውያን የተሰማንን ኩራት ግን ልነግራችሁ አልችልም። ኬኒያውያን ወንድሞቻችን ግን ኩምሽሽ እንዳሉ እንዴት ላሳያችሁ። እኛም ተጫዋቾቻንን “እግዚአብሔር ይመስገን” የሚለውን በጋራ መዝሙር ተለየናቸው።

ሁለት ጥያቄዎች ግን አዕምሮዬ ውስጥ አሉ። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ውጭ ሃገር ስንገናኝ የምንዋደደው ለምንድን ነው? እናንተስ እንዲህ አይነት አጋጥሟችሁ ይሆን?

ነገ ዛሬ ያገኘሃቸውን አሉባልታዎች በማስረጃ አስደግፍ ደግሞ አወራቸሃለሁ።

ማክሰኞ ደግሞ የውሃ ስራዎችን መጨረሻ አወጋችሃለሁ።

አመሰግናለሁ (ሳዋ!)

Advertisements

One thought on “የናይሮቢ ጉዞ ማስታወሻዎቼ

  1. I really impressed today and proud of being Ethiopian. I have been in Africa Nazarene University since 2009 alone without any friend, but I got my only best friend from Ethiopia today and we were talking in our language and enjoying together and I was not aware of that our basket ball team is coming to our university, but thanks to my Congolese friends , they called me and told me that our team is already here and preparing to play with Kenyans. Immediately I and my friend rushed to the field to watch the game and the first session was really very bad and we felt bad and many of my Kenyan friends of mine started sending messages and discouraging me, but our Ethiopian team which has the real story of freedom came soon to show our history in a foreign country and I and my friend were very glad many of my international students joined my group and we started shouting loudly and finally thanks to God our team succeed and we sung the victorious song together and we gave glory to God, and really this kind of unity shows our concern to each other, therefore , before my conclusion I would like to urge all of us to love each other even in the country as we do in a foreign country, everywhere and to live in harmony. May God bless Ethiopia.

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s