ምን ይወራል ? News

የናይሮቢ የጉዞ ማስታወሻዎቼ

አንዳንድ ጊዜ ከሃገር መውጣት የሚያስፈራ ነገር ነው። በተለይ “ብርቅዬ” ሆኖ በሃገር ውስጥ ለተቀመጠ ሰው። እኔ እንደዛ አይደለሁም ! ከዚህ በፊት በርከት ያሉ ቦታዎች የመሄድ ዕድል ገጥሞኛል።

በእርግጥ ዕድል ይሁኑ ግዴታዎች አላውቅም ለማንኛውም ግን አሁን ናይሮቢ እገኛለሁ። በከተማው ውስጥ ከሚገኙ በርካታ ዩኒቨርስቲዎች በአንዱ ውስጥ የድህረ ምረቃ ትምህርቴን ለመከታተል ተሰይሜ እገኛለሁ። ከምማረው ትምህርት በበለጠ አንድ ያጓጓኝ ነገር አለ። በአሁኑ ጊዜ በተለይ ክርስትና (የወንጌላውያን ክርስትና) በኢትዮጵያ “አክትሞለታል ተቀብሯል ተሃድሶ ያስፈልገዋል” የሚል ድምጽ አይሎ ይሰማል። “ታዲያስ እውነት ነው እንጂ ሥነ ምግባረዊ ውድቀት ነግሷል” የሚሉ ሰዎች በርካታዎች ናቸው።

 

እኔ ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው የማስበው ክርስትና በየትኛውም ዘመን እንዲህ አይነት ችግሮች ይገጥሙታል ነገር ግን ከእነዚህ ተሻግሮ ያበራል የሚል አመለካከት ነው ያለኝ። ለማንኛውም ይህንን አመለካከቴን ለእኔ ተውት! እንዲያው እስቲ ክርስትና በኬንያዋ ዋና ከተማ ናይሮቢ ምን ይመስላል? በተለይ በወጣት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዘንድ የሚለውን የሚበሉትን እየበላሁ፣የሚያድሩበት እያደርኩ “ፍትፍት” አድርጌ ላወራችሁ ወስኛለሁ። በየቀኑ የገጠሙኝን ነገሮች በሙሉ ብሎግ አደርጋለሁ ፍርዱን ለእናንተ።

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s