Uncategorized

የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ተግባራዊ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ሦስት መፍትሔዎች

ስለዚህ ዘመን የኑሮ ውድነት ለማወቅ መቼስ የግዴታ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ (ኢኮኖሚስት) መሆን አይጠይቅም። እኔ እንደምገምተው በአቅራቢያችን ወደሚገኝ ሱቅ ሄደን ትላንት የገዛነውን ዕቃ ዛሬ ደግመን ብንጠይቅ የዚያን ጊዜ አንድ ኢኮኖሚስት መጽሐፍ አገላብጦ ከሚያገኘው “ፅንሰ ሃሳብ” በላይ “ተግባራዊ” ዕውቀት ማግኘት የሚቻል ይመስለኛል። እንዲያውም በየታከሲው ውስጥ የሚጋገረው እና የሚቦካው እሱ ነው። በእርግጥ ቤተክርስቲያናቶቻችን በኑሮ ውድነት ዙሪያ ፀሎት እንጂ “የቃል መልዕክት” እንዳልተናገሩ ያነጋገርኳቸው ወዳጆቼ ጠቁመውኛል። ታዲያ ይህንን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም እንደ ክርስቲያን ምን ይጠበቅብናል።

እንፀልይ

ኤ.ሲ ዲክሰን እንዲህ ብለዋል ፦

በድርጅቶች ላይ ስንደገፍ  ድርጅቶች ሊያደርጉት የሚችሉትን ነገር ብቻ እናገኛለን። በትምህርታችን ላይ ስንደገፍ  ትምህርት ሊሰጠውን የሚችለውን ብቻ እናገኛለን። በሰው ስንመካ ሰው ሊሰጠው የሚችለውን ብቻ እናገኛለን። ነገር ግን በፀሎት ላይ ስንደገፍ እግዚአብሔር ሊያደርገው የሚችለውን እናገኛለን።[i]

ምናልባት ቢፈቀድልኝ እኔም ይህንን እጨምር ነበር- በመንግስት ላይ ብንመካ መንግስት ሊያድርገው የሚችለውን ብቻ እናገኛለን። በአይ ኤም ኤፍ ላይ ብንመካ ፤አይኤም ኤፍ ሊያድርገው የሚችለውን ብቻ እናገኛለን፤ወዘተ… ታዲያ ፀሎት የአጽናፈ ዓለሙን ፈጣሪ ለድርጊት የሚያንቀሳቅሰው ከሆነ ስለ ኑሮ ውድነት የማንፀልየው ለምንድን ነው?  ብዙዎቻችን የማንፀልየው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እግዚአብሔር ታሪክን የመለወጥ አቅም የለውም ብለን በልባችን ስለምናምን ይመስለኛል? ከዚያ ይልቅ የአረቦችን መረጋጋት ፣ የአሜሪካንን እና የአውሮፓውያንን እርጥባን፣ የመንግስት እርምጃ ለውጥ የሚያመጣ ይመስለናል። ምክንያቱም የዓለምን “ተግባራዊ” ችግር የሚፈቱት እነሱ ናቸው ብለን ስለምናስብ ነው። ነገር ግን በተግባር የምናየው ነገር ያ አይደለም አሁንም የዓለማችን የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ውስጥ ሆና እየተጨነቀች እንደሆነ የምናየው እውነት ነው ። እነዚህ የዘረዝርናቸው እሱ ፈቃዱን የሚያከናውንባቸው መሳሪያዎች ናቸው። ለዚህ የመጀመሪያው መፍትሔ የታሪክ ሁሉ ባለቤት ወደ ሆነው አምላካችን መጮህ ነው። እግዚአብሔር ዛሬ የምናየውን ኢ ፍትሐዊ ግብይት የመለወጥ አቅም አለው።  የእስራኤልን ታሪክ ተመልከቱ “እንደገና ለእስራኤል ቤት ልመና እሺ እላለሁ ይህንንም አደርግላቸዋለሁ፤ ሕዝባቸውንም እንደመንጋ አበዛዋለሁ” (ሕዝ.36፡37) ታዲያ እግዚአብሔርም ታሪክን መለወጥ ቢችልም እንኳን እኛ አንድንጠይቀው ይፈለጋል። ስለዚህ እንጠይቀው “አባት ሆይ…” እንበለው። ፀሎታችን ለየትኛውም ሥራ መንደርደሪያችን ነው። በመሆኑም እስቲ ምስባኮቻችን ሁሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ጌታ እንደ ፈቃዱ ጣልቃ እንዲገባ የምናውጅባቸው መድረኮች ይሁኑ።

ለኑሯችን ጣሪያ እናብጅለት

በአንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ የመጣ የውጭ ሃገር ዜጋ ኢትዮጵያውያን ውሃ መጠጣት ሲችሉ ኮካ ይጠጣሉ ማለቱን ማንበቤ ትዝ ይለኛል። ሁሉንም ባይወክልም እውነት ግን ይመስለኛል። ታዲያ በዚ የኑሮ ውድነት በተንሰራፋበት ዘመን የምንኖር ክርስቲያኖች  ለኑሯችን ጣሪያ ልናበጅለት አይገባም ትላላችሁ። መግዛት ስለምንችል ብቻ የገኘነውን ነገር ሁሉ መሸመት የለብንም። ምናልባት እግዚአብሔር የመስራት እና የማግኘት አቅም የሰጠን ፤ የገኘነውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በእኛ ላይ እንድናውለው ሳይሆን ቁራሽ ዳቦ ያጠሁ ወገኖቻችንን እንድናስብበት ይሆናል። መጋቢ ጆን ፓይፐር ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፦

ኢየሱስ አንዳለው ከሆነ ማገኘው ገንዘብ ሁሉ በምድር ላይ ያለ ሕይወቴን በምቾት የተሞላ ለማድረግ ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ሞኝ ነው። ጠቢብ ሰዎች ገንዘባቸው በሙሉ የእግዚአብሔር አንደሆነ ያውቃሉ ፤ ገንዘብንም ውዱ ሃብታቸው፣ ምቾታቸው ፣ደህንነታቸው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ በሚያሳይ መልኩ ይጠቀሙበታል።[ii]

በእርግጥ ከመጋቢ ፓይፐር ጋር የምንስማማ ከሆነ ማድረግ የሚገባን የሚከተለው ይመስለኛል ፦ የምንችለውን ያህል ገንዘብ ማግኘት ፤ የሚያስፈልግንን ያህል መጠቀም ሌላውን ደግሞ “በሰማይ” ማስቀመጥ። የዚያን ጊዜ ዋስትናችን እግዚአብሔር እንጂ ገንዘባችን እንዳለሆነ  በማያሻማ ሁኔታ እናሳየለን። የኑሯችን ጣሪያም  ያ ይመስለኛል። ኮካ መጠጣት ብንፈልግ ሻይ ተጥተን ፤ ዳቦ ለሌላቸው ሰዎች መስጠት እንደማለት ነው።

በፀሎት አለመታዘዝ

ሦስተኛ ከተመን ውጪ የሚሸጡ ነጋዴዎችን  “እምቢ” ማለት። ይሄ ከባድ፣ ፀሎት እና ድፍረት የሚጠይቅ ነው። ዛሬ መንግስት ካወጣው ታሪፍ በላይ እቃዎችን የሚነግዱ ነጋዴዎች ሥራቸውን እንደ ጀብዱ እያዩት መጥተዋል።   አንዱ ወዳጄ ትላነት ሲያጫውተኝ በሰፈር ውስጥ ዘይት ፈልጌ በ32 ብር አገኘሁ ና ሌላ ዕቃ ልገዛ ወደ አንድ ሱቅ ሄድኩ አለኝ። እዚያም ባለሱቁ ምን ያህል ገዛሀው ብሉ ጠየቀኝና ዋገውን ነገርኩት ። እሱም እንዲህ አለኝ አለ “አንተዬ ሕዝቡ ለካ ለምዷል አሁንስ ዘይት ባመጣ ይሻለኛል።” አልለመድንም! እያንዳንዳችን ክርስቲያኖች በዚህ ምድር ላይ ያለን ስርዓተ አልበኝነት የምንከላከለው በፀሎት ብቻ ሳይሆን በፀሎት አለመታዘዝም ጭምር ነው። ይህም ማለት እነዚህን “ስግብግብ” ነጋዴዎች  “እምቢ” ልንላቸው ይገባናል! እምቢታችን ግን ምንጩ እራስ ወዳድነት ብቻ ሳይሆን ኢፍትሀዊነትን ለመቃወም ነው። አንድ ነጋዴ ከእግዚአብሔር ፍትህ፣ ከህሊና ፍርድ፣ ከመንግስት ፍቃድ ውጪ በሆነ ሁኔታ ሲሰራ አንገዛህም ለማለት የመጀመሪያዎቹ እኗ ክርስቲያኖች መሆን አለብን።


[i] John Piper , Brothers we are not professionals: A plea to pastors for Radical Ministry (NAshvill: Tennesse: Brodman &Holman Publishers) p.176

[ii] ዝኒ ከማሁ ፤ ገጽ 76

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s