Uncategorized

የሰንበት ህብረት ፣ የጸጋ ሥጦታዎች አጠቃቀም ችግር፣ እና የእኔ ምልከታ

በአብዛኛው ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል በጣም ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ነገሮች አንዱ “የጸጋ  ሥጦታዎች ናቸው” ብል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ማስረጃው  አገልጋይ በሚጋበዝበት ጊዜ  የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ናቸው። “እንዴት ነው ይሄ ሰውዬ የሚያገልግለው በጸጋ ነው?” “አንዴት ነው ይህች ሴትዮ ‘ትጸልያለች’?” “እንዴት ነው ይሄ ሰውዬ ጣል ጣል ያደርጋል?” ወዘተ። ሁለተኛው ደግሞ  አብያተ ክርስቲያናት የሚከፈሉበት መንገድ ነው። አንዳንዶች ‘እርጥብ’ ሲባሉ፤ ይህም ማለት ትንቢት ፣ልሳን እና ‘ሰሜት ኮርካሪ’ አምልኮ እንዳላቸው መገለጡ ነው። ‘ደረቅ’ ማለት ደግሞ ምን ማለት እንድሆን ለእናንት መናገር አያስፈልግም። ስለዚህ አብዛኞቹ ወንጌላውያን ለጸጋ ስጦታዎች በ “እምነት ከመዳን” በታች እና “ከመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣናዊነት” በላይ ስፍራ ይሰጡታል ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም።

ከዚህም አመለካከታቸው ጋር ተያይዞ የአጠቃም ችግር ሊኖር እንደሚችል መገመት አያቅትም። ወደ እነዚህ አቢአተ ክርስቲያናት ጎራ ቢሉ በትንቢት የተጋባ ፣ በትንቢት የተፋታ፣ በትንቢት ሥራ ያገኘ ፣ በትንቢት ስራ ያጣ ማግኘት ብዙም አይከብድም። አንዳንዶች ጌታ ፈውሷችሃል ተብሎ ከተነገራቸው በሃላ ከነደዌያቸው ዛሬም ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ጥሰው እንደሚወጡ ተነገሯቸው ዛሬም እያዳከሩ እንዳሉ ግልጥ ነው። ዛሬም ትንቢት ሳይሰሙ ከአልጋቸው የማይወርዱ ሰዎች በመካከላችን ያሉ ሲሆን ፤ ከዚያ ውጪም የ‘ግል ነቢያት’ ያላቸውም በርከት ያሉ እንደሆኑ እሙን ነው።

በብርቱ ወጣቶች የተደራጀው እና ዕለተ ሰንበትን ተንተርሶ የተለያዩ ሃሳቦችን ይዞ “ክርስቲያኖች አዕምሯቸውን መጠቀም አለባቸው” በሚል መርህ የሚመክረው የሰንበት ቡድን  ደፈር ብሎ ይህንን ጉዳያችንን ይዞ አደባባይ ወጥቶ ነበር። ዕለተ ውዳሜ የካቲት 21 ቀን 2003ዓ.ም ከማደው ሦሰት ሰዓት ተኩል በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች ውስጥ ፕሮግራሙም ወደ 150 የሚጠጉ ተማሪዎችን፣ መጋቢዎችን እና የሥነ መለኮት አዋቂዎችን አካትቶ ነበር። በእለቱ የቤዛ ባፕቲስት ቤተ ክርስትያን መጋቢ የሆኑት መጋቢ ስሜ ታደሰ እና በተለያዩ የሥነ መለኮት ትምህርት ቤቶች በማስተማር የሚያገለግለው ወንድምማችን እንዳሻው ወረቀቶችን  አቀርበው ነበር። በእነዚህ ወረቀቶችም ዙሪያ ጥሩ የሚባል ጥያቄ እና መልስ የነበረ ሲሆን፤ በአጣቃላይ ፕሮግራሙ የተዋጣ ነበር ማለት ይቻላል።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው አስተያየታቸውን ከሰጡኝ በርካታ ግለሰቦች የተረዳሁትም ይህንኑ ነበር። በኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ትምህርት ቤት የሆነ አንድ ተማሪ “ፕሮግራሙ እስከዛሬ ድረስ ካየ`ቸው ትምህርት ነክ ፕሮግራሞች ሁሉ የተዋጣለት ነበር። አንዳንድ ሰዎች ‘ሲጀምሩ አርፍደዋል’ ፣ ‘የስብሰባውን አዳራሽ አላመላከቱም’ ከሚለው ቅሬታ በስተቀር ድንቅ ነው ብሎናል።” ሌላኛው የድህረ ምረቃ ትምህርቱን ለመከታተል በዝግጅት ላይ የሚገኝ ወንድም የፕሮግራሙ ጥሩነት አምኖ ተቀበሎ በመጋቢ ስሜ የቀረባውን ወረቀት ትንሽ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ትኩረት ያንሰዋል ሲል፤ የወንድም እንዳሻውን ወረቀት ደግሞ ትንሽ ተግባር ተኮርነት እና ቅንጅት ላይ አቕም ያንሰዋል” ብሎኛል። በርካቶችም “ጌታ ይባርካቸው ድንቅ ነው” ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል።

እኔ በግሌ ያሰተዋልካቸው ነገሮች ከላይ ከተገለጡት ብዙም የራቁ አይደሉም። አንደኛ ሰዓት ተከብሮ አለመጀመሩ ትንሽ ቆጥቆጦኛል ምናልባት ‘ባህላችን  ነው’ ተብሎ ይሆን እንዴ ብዬ አንድጠይቅም አድርጎኛል። ጅምላ ፍረጃ ግን ከሰንበት ቡድን የራቀ እንደሆነ እገምታለሁ። ሁለተኛ ፤ ትንሽ ሁለት የተለያዩ “ጽንፈኛ” አመለካከቶች ቢስተናገዱበት ጥሩ ውይይት እና ሙግት ይፈጥር ነበር፤ ፍሬውም ልዩነትን ማወቅ እና ልዩነትን አቻችሎ መኖር ይሆን ነበር። ይህንንም ስል ምናልባት ‘የጸጋ ስጦታዎች የአጠቃቀም ችግር አለ’ እና ‘የጸጋ ስጦታዎች አጠቃቀም ችግር የለም’ የሚል አይነት አልያም ደግሞ ‘የጸጋ ስጦታዎች ቆመዋል’ እና ‘የፀጋ ስጦታዎች ቀጥለዋል’ በሚል አይነት። ሦስተኛ የጥያቄ እና መልስ ጊዜው ማነስ ግን የራስ ምታት ሆኖብኛል።( ምክንያቱም ወሳኝ ጥያቄዎች ነበሩኝ! ሌሎችም እንደዚያው)

በጥቅሉ ግን ለሰንበት ቡድን ጭብጨባ ይገባል። ከዚህ ቀደም ከተዘጋጀው ፕሮግራም እጅግ በጣም የተሻለ ጥልቀት እና ዝግጅት አይቼበታለሁ። ከሁሉ በላይ ያስደሰተኝ ግን የብዙ ታዳሚዎች መገኘት እና የወንድም ሚኪያስ በላይ የመድረክ አመራር ነው (ብራቮ ሚኪ)። እኔም በሚቀጠሉት ተከታታይ ጽሁፎቼ በዕለቱ የቀረቡ ሁለት ወረቀቶች ዙሪያ ያሉኝን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አነሳለሁ። ከፀሐፍቱ ጋር እና ከሰንበት ቡድን አስተባባሪዎች ጋርም እማከራለሁ።

Advertisements

One thought on “የሰንበት ህብረት ፣ የጸጋ ሥጦታዎች አጠቃቀም ችግር፣ እና የእኔ ምልከታ

  1. you ! young scholar really I am impressed in your thoughts and theological understandings. yes we have to know what the bible says about spiritual gifts and we have to use them in right way for the glory of God rather than misusing and taking credit for ourselves. by the way don’t you think that ,this is the right time to talk about spiritual gifts and their usages as evangelical churches especially focused on youths? I agree with you, Your comment about past is good but what is your opinion about present and future, the situation we are in and we are going through and we will be going? I need your concrete point!
    peace and grace
    Thom

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s