Uncategorized

የሐዊ ማስታወሻዎች ( ክፍል ሰባት)

የሐዊ ማስታወሻዎች ( ክፍል ሰባት)

የካቲት 28 ቀን 2003 ዓ.ም

እናንተዬ ሰው ጥፍት ሲልም አትጠይቁም ? እኔ ግን እንዲያው በወሬ ከመሞላቴ ይተነሳ አንድ ቀን ጦስ ብዬ እፈነዳለሁ ብዬ ሳስብ፤ ጌታ ረዳኝ እና ብዕሬን እንደገና አነሳሁ? ለመሆኑ እንዴት ናችሁ? ብዙ ላወራችሁ ይምፈልገው ነገር አለኝ ግን ከየት ልጀምር?

እስቲ ሰበብ በመስጠት ልጀምር ። እንዲያው ምናልባት ምናልባት አንዳንዶቻችሁ “ይህን ያህል ጊዜ ሳትፅፊ የከረምሽው ለምንድን ነው?”  ልትሉኝ ትችላላችሁ። ሁለት ምክንያት ነው ያለኝ ከወራት በፊት ማስታወሻዬን ስመለከት ለመጨረሻ ጊዜ የፃፍኩት  ስለዛ ቀፋፊ ቀን ነበር። ማለቴ ታስታውሱ የለ መPል ፈረንሳይ ላይ ጠብ የጫርኩ ጊዜ ማለት ነው። የዛን ቀን የተፈጠረውን ሳልነግራችሁማ ሌላ Pተታ ማብዛት የለብኝም።

ያው ባለፈው ወሬዬን የቋረጥኩት መሬት ላይ በጀርባዬ መውደቄን እና እራሴን መሳቴን ተናግሬ አይደል? ከዚያላችሁ ልክ እንደወድቅኩ ቤዛ ሆዬ በሁለት እጆች አንከብክቦኝ፣ ከጭንቅላቴ ላይ የሚፈሰው ደም ቁብም ሳይሰጠው እያንደረደረ ታክሲ ውስጥ አስገባኝ። የገባበት ታክሲ ሹፌር ደግሞ ከእሱ ጓደኞች ጋር ሲጣላ ስላየው  አላሳፍርም ብሎ ግግም አይል መሳላችሁ ። እንዴት ያሳፍራል እኔ በ`ላ ላይ ሲነግሩኝ እንኳን ‘ፌንት’ የሰራሁ ነው ያለኩት። ስለ ‘ፌንት’ ሳነሳ ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ አንዲት ሴትዬ? ስሟን አላስታውሰውም ብቻ ወደ ሲዖል ሄዳ እንኳን ሲዖል ምን እንደሚመስል ያየችው! አላውቅም ሲዖል ግን እሷ እንዳለችው ሰዎች የሚቀጠሉበት ስፍራ ይሆን ? አላውቅም 1 ጌታ ግን ጨክኖ….አይመስለኝም። ለምንድነው ሰዎች ስለ መንገስተ ሰማያት ውበት ከማውራት ይልቅ ስለ ሲዖል “እሳት” የሚያወሩት?

ወሬ አበዛሁ አይደል ንፍቅ ብሎኝ እኮ ነው። ከዛላችሁ ኪኪ ሆዬ የቻለችውን ያህል ቦጫጭራ፣ የቻለችውን ያህል ተሳድባ ከጨረሰች በሃላ ! ገንዘቧን ላጥ አድርጋ ‘ላዳ’ ‘ኮንትራት’ ይዛ ‘ሆሰፒታል’ ሄድኩላችሁ። ገና ‘ሆስፒታል’ እንደረስኩ ነበር፤ ልክ ቁስሌን በአልኮል መጠራረግ ሲጀምሩ የነቃሁት። አይዟችሁ አትፍሩ እኔ ሲዖልንም ገነትንም አላየሁም። እንዳልዋሽ ግን ድቅድቅ ያለ ጨለማ አይቻለሁ።

ፀጥ ያለው እና ነጭ የተቀባው የክሊኒኩ ድንገተኛ ክፍል ከእኔ መኝታ ቤት እንኳን ይጠባል። እኔ የተኛሁበት አልጋ እና ሁለት ግዙፍ ነርሶችን ይዟል። ዶክተሩ ብቻውን እያጉተመተመ እቃ ያንኮሻኩሻል። ያለኝን ሃይል ተጠቀሜ አይኖቼን ገርበብ አድርጌ ስመለከተው። አንድ ሰው እና አንድ ትልቅ ቦርጭ በትንሽ ስልቻ ተያይዘው ይመስላል። ሳቄ አፈነኝ ድንገት ግን አናቴን የሚያዞር ህመም ተሰማኝ። ለካ ነርሷ የምወደውን ጸጉሬን  ያለርህራሄ በምላጭ እየላጨችው ነው።

በሹክሹክታ አጠገቧ ላለችው ጠና ላለችው ነርስ እንዲህ አለቻት “ለምን ለሳምፕል አትወስጂም!” አለቻች።

ጠና ያለቸውም ነርስ “አንቺ ነሽ የሚያስፈልግሽ ? ያ ከርፋፋ ጓደኛሽ ይህንን “ሽቦ” ጸጉርሽን አይቶ አይደል የተወሽ? ”

ወይ ጉዴ አረ ሥራችሁን ስሩ ወሬ አታብዙ ልል አሰብኩና አቅም አነሰኝ።

ወጣቷ ነርስ “አንቺ እኮ ከጨዋታ ውጪ ስለሆንሽ ነው!” ከት ከት ብላ አስቀያሚ ሳቅ ሳቀች። ስትስቅ የሰራ አካሏ ይንዘፈዘፋል። በዚህን ጊዜ ቁስሌን አሰመመችኝ የተሰማኝን ህመም ልንግራችሁ አልችልም። አቅም ቢኖረኝ በጥፊ ብላት ደስ ይለኝ ነበር።

“አንቺ ከርፋፋ… አረ ልጅቷን !”  አለቻት። ሳቋን ስላቆመች እኔም ተንፈስ አልኩ። “ከጨዋታ ውጪ”  ማለት ግን ምን ማለት ነው ? መልሱን ለማግኘት ስመራመር ከውጪ በኩል ጩzት ተሰማ። ጩzቱ እየቀረበ ሲመጣ የማን እንደሆነ አወቅኩ።

ማሚ ነበረች። በጩzት ግቢውን እያናወጠችው ገባች! በእድሜ የገፉትን የጥበቃ ሰራተኛ ምንም ሳትቆጥር ተንድርድራ ወዳለሁበት ክፍል ስትገባ… ሁለት “ቀጫጫ” ነርሶች፣ አንድ “ቦርጫም” ዶክተር እና ቤዘ ነበሩ ይዘው ያቆሟት።  ተኛሁበት ክፍል ውስጥ ሆኜ

“ልጅ ሞታለች!ያ ሁላ ደም ፈሷ አትተርፍም ..ወይኔ ልጄ ወይኔ ልጄ አንድ ልጄ ..የእኔ ሐዊ” እያለች ስታለቅስ ተሰማኝ እና ትንፋሼን ዋጥ አድርጌ እምባዬን ተቆጣጠርኩ። ትንሽ ቆየት ብሎ የቤቢ ድምጽ ይሰማኛል “እህ ምን ትሆናለች..በጥይት አልተመታች አታካብጂ” ሲላት ይሰማኛል። ትንሽ ቆይቶ የታለ የታለ የሚል ድምጽ ተሰማኝ። የዳዲ የቁጣ ድምጽ እንደሆነ በምን አጥቼው።

“እነዚህ ሁለቱ ናቸው ጠቡን የቀሰቀሱት ያዙልኝ!”

ኪኪ “ኡኡኡአኡ..” ብላ ስትጮህ ከአላጋዬ ለመነሳት ያደረግኩት ጥረት ጭንቅላቴ ላይ በሚሰማኝ ህመም የማይቻል ሆንብኝ። ድምጼን ለማውጣት ብሞክር… ድምጼን “የቀማኝን” ነገር ያለ ይመስል ለራሴ እንኳን አይሰማኝም ነበር።

“ፋዘር ..”

“አንተ ዝም በል ..ይቺንም ያዙልኝ እሱንም ያዙልኝ “

ማሚ “ለዚያውም ተርፋ ከሆነ እኮ ነው…አማረ” ማሚ የዳዲን ስም እንደዚህ የምትጠራው በጣም ስትቆጣ ብቻ ነው። እጄ፣ እግሬ፣አንደበቴ አልታዘዝ አለኝ። አይኖቼን አንስቼ በቀዳዳ ውስጥ እንኳን እንዳልመለከት። አይኖቼ ማጠፊያው እንደዘጋ በር ተንጋታግተው ተከፈተው ተዘጉ።

ፖሊሲቹ ቀትል እዚያው ሄደህ መልስ ትስጣለህ

ኪኪ “ወይኔ ማሚ” ብላ ጮሀች ፖሊሱ “ዝም በይና ቀጥይ”

“እሺ እሺ በናትህ እንዳትመታኝ!” አለች።

“ዳዳ ማሚ እነሱ ምንም አላጠፉም። እኔም ምንም  አል…” አረፍተ ነገሩን መጨረስ አልቻልኩም ።አይኖቼ ላይ ክብ ክብ የሆኑና የተለያዩ ቀለማት ያለቻው ብርሃናት ታዩኝ። የልብ ምቴ እየወረደ ስመጣ ይታወቀኛል። የተኛውሁበት አልጋ እየተስከረከረ ቁለቁል ወደ መሬት ገባ።

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s