ምን ይወራል ? News

AFRICAN BIBLICAL LEADERSHIPINTIATIVE (ABLI) ፎረምን የእኔ ምልከታ

ከሦስቱ ቤተ እምነቶች የተውጣጡ እና  ከተለያዩ ዓለማት በተለይም ከአፍሪካ የተውጣጡ ግለሰቦች በተካፈሉበት ሶስተኛው የአብሊ ኮንፍራንስ ላይ ሁለቱን ቀን ታድሜ ነበር። እጅግ በተዋበው እና ቃሊቲ ግርጌ በሚገኘው የCCRDA የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ ወደ 350 (በግምት!) የሚሆኑ ሰዎች ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማሕበር  ዋና ፀሐፊ ንግግር የተጀመረው ስብሰባ  በቡድን ፀሎት እሰከተጠናቀቀበት ድረስ የተለያዩ ትዕይንቶችን አስተናግዷል። ጭማቂው እነሆ !

“የሥላሴ አማኝ ቤተክርስቲያናት መድረክ”

ድንቅ ሓሳብ ! ሶስቱ ቤተክርስቲያናት (አርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ወንጌላውያን) “በልዩነት አንድነት” ብለው አብረው መነሳታቸው ይበል የሚያስብል ነው። ነገር ግን ነገር አንድ ነገር ቅር ብሎኛል። ምን መሰላችሁ ? ሕብረታቸው ግጭትን በመፍታት ረገድ ያስቀመጠው ነገር ትንሽ “ጎምዘዝ” ብሎኛል። ምክንያቱም ግጭት ማሰወገዱ ሁሉም ቤተ ክርስቲያናት በሥራቸው ያሉትን ምዕመናን መቆጣጥር ይችላሉ በሚል ሂሳብ ላይ የተመሰረተ ስለ መሰለኝ ነው። ነገር ግን ይህ ነገር ተጨባጭ አይመስለኝም! ምክንያቱም የወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያናት ሕብረት በቁጥጥሩ ስራ ያሉት አብዛኛዎቹ እንጂ ሁሉም ወንጌላውያን ቤተ እምነቶች አይደሉም! በኦርቶዶክስ በኩል ደግሞ ማህበረ ቅዱሳንን ለየት አድርጎ የማየት አካሄድ ያለ ይመስለኛል!

መጽሐፍ ቅዱስ እና …

መጽሐፍ ቅዱስ እና ግጭት አፈታት፣ መፅሐፍ ቅዱስ እና ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ መፅሐፍ ቅዱስ እና መልካም አስተዳደር  የሚሉ ሶስት ወርክ ሾፖች በጋራ ውይይት ታጅበው ቀርበዋል። በግጭት አፈታት ዙሪያ የተናገሩት ሰው “ከውጪ በተጫኑብን፣ ወይም ከውስጥ በመነጩ ግጭቶች አፍሪካዊ ማንነታችንን ለማጥፋት በሚገዳደሩባት አህጉር ውስጥ እንኖራለን” በማለት የጀመሩት እና ግጭትን መቼ እና እንዴት እንፈታለን የሚለውን ያስተነተኑት ቻርለስ ቪላ ቪቺንሲዮ የመጀመሪያው ተናጋሪ ነበሩ። ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካ የተለያዩ ቦታዎች የሚታዩትን ግጭቶች ለመፍታት ግዴታ አለባት ነገር ግን ይህን ነገር እንዲሆን ፍቃደኝነቱ እና መሰጠቱ አላት ወይ ሲሉ ጠይቀዋል? (እስቲ እናንተ መልሱት!)

ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ ድንቅ ኢኮኖሚስት!

የCCRDA ዋና Pላፊ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ ድንቅ የኢኮኖሚ ዕወቀታቸውን ያስመሰከረ ትንታኔ አቅርበው። ከእግዚአብሔር ሉዐላዊነት ውጪ የሆኑ መላምቶችን  እና ውጤቶቻቸውን “እግዚአብሔር አልባ ዕድገት” ሲሉ መዝለፋቸው እና ለዚህም የአሜሪካንን እና የሩሲያን የምዕራብ አውሮፓን ጉዳይ ማንሳታቸው አንጀት አርስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን ግን ለኢኮኖሚያዊ ሓሳባቸው ማጠናከሪያ መጠቀማቸው ትንሽ  አስቀይሞኛል። አንድ የኢኮኖሚ ሊቅን ጠቅሰው “ እግዚአብሔርን በመላምቶቻችን (በኢኮኖሚያዊ) ላይ እናንግሰው!” ሲሉ ያቀረቡት ጥሪ አጀብ አሰኝቶኛል።

አፍሪካ ያለባት “Leadership Tsunami” ነው!

የናይጄሪያው የPeople Democratic Party አባል የሆኑት ኢማኑኤል ኢሺቢ አንድ መፅሓፍ አፍሪካ የተፈጥሮ አደጋ የለባትም መባሉን ጠቅሰው። “አዎ እሱ የለባትም! አፍሪካ ያለባት የአመራር ሱናሚ ነው “ ብለዋል። እኔ ግን በዚህ አልስማማም። ምክንያቱም አሜሪካ ብንል፣አወሮፓ ፣ ሩቅ ምስራቅ፣ መካከለኛው ምስራቅ ወዘተ ዓለም ያለባት ችግር “የአመራር ሱናሚ” ነው። አሁን በሞቴ የእንግሊዝን በሙስና መተራመስ የሰማ በእርግጥ ያለኩትን ነገር እውነትነት ይሞግት ይሆን?

ወይኔ መጽሐፍ ቅዱስ!!

እናንተይ ማንኛውንም  ሙያ አውርታችሁ …መHል ላይ  ከመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በተን ካደረጋችሁበት መፅሓፍ ቅዱሳዊ ይሆናል። “እግዚአብሔር እንዳሎሎ ይወርውራች`ል !” የሚለውን ጠቅሶ እስፖርት ያስተማረን የስፖርት መምህራችንን አልረሳው። ከአብሊም የነቀፍኩት ይህንን ነው። መፅሓፍ ቅዱስን ሐሳባችንን ለመደገፍ አንጥቀሰው።

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s