ምን ይወራል ? News

“ሙሽሮቹ ቀሩ” ፦ “የፖሊስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም” ፣የእኛ መንደር ሰዎች እና ሪፖርተር ጋዜጣ

ሰሞኑን የፖሊስ ፕሮግራም በቴሌቪዥን በቴሌቪዥን “የውሃ ሽታ የቀረው” ሙሽራ ጉዳይ በከተማችን ውስጥ በየጥጋጥጉ መወያያና፣ ቡና መጣጫ፣ወሬ ማጣፈጫ ሆኗል። ሁሉም ሰው የመሰለውን አስተያየት ይሰጣል። ሁሉም በየራሱ “መረጃ” ላይ ተመስርቶ ፍርድ ይሰጣል። ሁሉም የተለያዩ አካላትን “የምሰክር ወንበር” ላይ እያስቀመጠ ይፈርድባቸዋል።

ወንዶች ሰብሰብ ብለው ፤                   

“ባክህ ተወኝ ጥፋተኛ  እሷ ነች !”

“ይህን ያህል ዓመት አብረው ሲቆዩ አንድ ቀን እንኳን ባለትዳር እንደሆነ አታውቅም። ማለቴ ወንድ ልጅ እኮ ሌላ ጉዳይ ሲኖረው ያስታውቃል…በቀላሉ ሞባይሉን ‘ሳይለንት’ ሲያደርግ…ሰዋራ ቦታዎች ሲቀጥር ምናምን ..መጠርጠር ይቻላል።”

“ቤተሰቦቿ ዕኮ ሲያነቡ ብታይ  ምን በወጣቸው! እሷ ናት ጥፋተኛ!”

“ባክህ ተወኝ! እኔ እኮ የሚገርመኝ እነሱ ተበድረው ለመደገስ እንዴት ደፈሩ!”

“በዚህ የኑሮ ውድነት … ይገርመሃል ከዚህ በፊት  አንዱ ምን ሆነ መሰለህ …”

“ወይ ጉድ .. “አዲስ ሙሽራ” የሚለውን ፊልም አይቼ ስደነቅ እኮ ነው ! ይህንን የሰማሁት!”

በንዴት የተቀጣጠሉ ሴቶች ፤

“እሱ ነው እንጂ ጥፋተኛ …ድሮውንም ወንዶች …የወደዱ አስመስለው ማታለል ልምዳቸው ነው! ሁሉም አንድ ናቸው።”

“ፈርዶባት ነው እንጂ! ምን ታድርግ ጠንቋይ አትቀልብ”

“ከዚህ በፊት አንዷ ሙሽራ ምን እንደሆነች ታውቂያለሽ…..”

ብቻ ሁሉም ሰው ፤ይገምታል፣ ይፈርዳል ፤ይሟገታል።

ሪፖርተር ጋዜጣ “የቀረውን ሙሽራ በተመለከተ” ያቀረባቸው ሁለት ወንጌላውያን ወጣቶች እና የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችም ይሟገታሉ።

አቶ ታምሩ

“እኔና ሲሳይ የተዋወቅነው በ1996 ዓ.ም. በአንድ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያህል በእጮኝነት ከቆየን በኋላ በባህሪ ስላልተግባባን በሰላም ተለያይተናል፤ ላለፉት አምስት ዓመታት ትደውልልኛለች እደውልላታለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ሰላምታ ውጭ ምንም ነገር ተነጋግረን አናውቅም፡፡ ተገናኝተንም አናውቅም፤”

ባለትዳር መሆኑንና በቤተክርስቲያን ሥርዓት ካገባ አንድ ዓመት ከሁለት ወራት እንደሆነው፣ የቤተክርስቲያን አገልጋይ መሆኑንና ከዚህ ውጭ ምንም እንደማያውቅ የሚገልፀው አቶ ታምሩ፣ ከሲሳይ ቤተሰቦችም ሆነ ጓደኞች አንድም ሰው እንደማያውቅ፣ የላከውም ሽማግሌ እንደሌለና ድርጊቱን ሁሉ የፈጸመችው በራሷ ተነሳሽነት ራሷ (ሲሳይ)  መሆኗን አበክሮ ይናገራል፡፡

ቄስ ከበደ

እንደ ቄስ ከበደ ገለጻ፤ የእምነቱ ተከታዮች ለመጋባት ሲፈልጉ፣ ሁለቱም ከአንድ ቤተክርስቲያን ከሆኑ ተፈራርመው ለቤተክርስቲያኒቷ ደብዳቤ ያስገባሉ፡፡ አንዳቸው ብቻ የአካባቢው አጥቢያ አባል ከሆኑ የሚፈልጉትን ተጣማሪ አጠቃላይ ነገር የሚገልጽና ለጋብቻ እንደሚፈላለጉ የሚገልፅ ደብዳቤ ያስገባሉ፡፡

ቤተክርስቲያኗም ለጋብቻ የደረሳትን ደብዳቤ በዝርዝር አይታና ጥያቄ አቅርባ፤ ተጋቢዎቹ የጋብቻ መሠረታቸው ምን እንደሆነና ለመጋባት ፈቃደኛ መሆናቸው ተጣርቶ ይጠየቃሉ፡፡ ስለ ተጋቢዎቹ መግለጫ እንድትሰጥ ወደሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ደብዳቤ ይፃፍና (አባል መሆናቸውን ቀደም ባሉት ጊዜያት ጋብቻ መፈጸም አለመፈጸማቸውን. . “. ቤተክርስቲያናቱ ደብዳቤ ከተለዋወጡ በኋላ፣ ለእሱ ወይም ለእሷ ከሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ሸኝ ደብዳቤ ይጻፋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ከመጋባታቸው ስድስት ወራቶች በፊት ነው፡፡ ከቄስ ከበደ ለመረዳት እንደቻልነው፣ ከዚያ በኋላ ለአራት ወራት ጋብቻን በሚመለከት ትምህርት እንደሚሰጥና በጉባኤ ፊት ቀርበው ትውውቅ ይደረጋል፡፡

ወ/ሪት ሲሳይ

ሚያዝያ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ድንገት ደውሎ የዘመድ ለቅሶ ስለመጣበት ክፍለ ሀገር እንደሚሄድ ነግሯት፣ ለሱ የሚያስፈልጉትን ሽማግሌዎች እንድታዘጋጅና እሱ እንደላከ አስመስላ እንድትልክ ተስማምተው ራሷ አዘጋጅታ መላኳን አረጋግጣለች፡፡ ይክደኛል የሚል እምነት ስላልነበራት መታለሏንም ገልጻለች፡፡

“እኔ ደፍሬ መገናኘት ከፈለኩኝ ለምን ይሸሻል? ለምን ግንባር ለግንባር አንገናኝም?” በማለት የምትጠይቀው ሲሳይ፤ ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ ሁሉም ነገር ሊታወቅ ይችል እንደነበር ትናገራለች፡፡

በፍቅር በነበሩበት ሰዓት የሁለቱን አንድነት የሚገልጽ የጋራ ፎቶ እንደሌላቸው የምትገልፀው ሲሳይ፣ የታምሩ አንድ ፎቶ እንዳላት፣ አብረው የተነሱትን ላሳጥብ ብሎ ወስዶ ተቃጥሏል እንዳላት አስታውሳለች፡፡

የሁለታችሁን ፍቅር የሚያረጋግጥ ምን ማስተማመኛ ነገር ይገኛል? በሚል ለቀረበላት ጥያቄ፣ “ድሮም ስነሳ እታመናለሁ ብዬ አይደለም፤ ሁሉንም ነገር በማድረጌ ጥፋቱ የኔ ነው፡፡ ተጎድቻሁ፣ ተከፍቻለሁ፤ ግን ጩኸቴን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይስማልኝ፤ እህቶቼ በኔ የደረሰው እንዳይደርስባቸው ጥንቃቄ ያድርጉ፤” ብላለች፡፡

(ቀሪውን እዚህ ይመልከቱ ሙሽራው ያልተገኘበት የሠርግ ዝግጅት እያነጋገረ ነው)

እያንዳንዳችን ከፖሊስ ፕሮግራም ፣ከሪፖርተር ጋዜጣ እና ከ“መንደራችን ሰዎች” መልስ እየጠበቅን ነው። ወዳጆቼ እናንተ ምን ትላላችሁ?

Advertisements

3 thoughts on ““ሙሽሮቹ ቀሩ” ፦ “የፖሊስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም” ፣የእኛ መንደር ሰዎች እና ሪፖርተር ጋዜጣ

  1. hi, i am soory for here, but if thery have a relasen ship how they dont have almost one pucter, i am sham of them, in my way some thing is secrat there r/s ship, it is long time there r/s ship how it happen some thing behand thm, no one now with out them.
    i dont want to say nothing but, it is not good for other gays, b/c it is like they said revang. i want to say for here strong.

    tq
    bybykass

  2. Sisay ledersbesh hazen kelbe betam azenalhu. E/r anchin yekasesh. esun gen atekseshew. yale yelele nbertshen shetshe shgut gezetesh akerkariwun beyewu zemnun hulu be Gari endihed wyenem ye alga kuragna adergiw. alebelziya gen anch rasesh yematrbi set nesh malet neaw. ye set wend hugnebet. batekalye”be Hiwot(betena) endinor atfkejilet.” kezi yebase men endayemtabesh? betetaseri muya tmresh enji yemtwchiw. egersh tekorto atwech. lemangnawum destawun kurechibet!!!!!!!!!!!!!!……

  3. I know tamiru for more than 20years in kollfe he is not maried ones even I know he was married more than three times thats why he hide the truth any body who wants the truth and know him aske him his marriage in kefetegna 25 kebele 07 it is before 15 or more years he is hidding his head under cherches who serves God do not .

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s