ምን ይወራል ? News

ተድላ ገብረ የሱስ ፦ ፍልስፍና እና ድህነት ፤ ፍልስፍና እና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ዕጣ፤ ፍልስፍና እና ኦሾ

ተድላ ልክ እንደ ሌሎቹ ፈላስፋዎች ውስብስብ አይደለም። ሁልጊዜ ከፊቱ ላይ ፈገግታ አይለየውም። ምናልባትም  እሰከዛሬ ከማውቃቸው ጥያቄ ከማይፈሩ ሰዎች መካከል ዋነኛው ነው ብል ማጋነን አይሆንም። ግልጽ እሰከ ሆነ ድረስ ማንኛውንም ጥያቄ ለመመለስ ይሞክራል ካለወቀውም ፈገግ ብሎ “አላውቀውም!” ይላል ። ሙሉ ስሙ ተድላ ገበረ የሱስ ወልደ ዮሐንስ  ይባላል። በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ውስጥ መጠነኛ ታዋቂነት አለው። በተለይም የስንበት ቡድንን በመሳሰሉ የክርስቲያን ወጣቶች ሕብረት  እንዲሁም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አልፎ አለፎ በሚያቀርባቸው ፅሁፎች ይታወቃል። ተድላ በአሁን ሰዓት በሴንት ሉዊስ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ትምህርቱን  እየተከታተለ ይገኛል። ዕስቲ ተድላ ለሪፖተር ጋዜጣ ፍልስፍናና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ የሰጠውን አሰተያየት እንቃኘው።

 

ፍልስፍና እና  ድህነት

“ድህነት ባለበት አገር ውስጥ ፍልስፍናን መማር፣ ፍልስፍናን እንደ ሙያ አድርጎ መከተል ቅንጦት ነው የሚሉ አሉ፡፡ የተመቻቸው ሰዎች ብቻ የሚገቡበት አድርገው የሚመለከቱት አሉ፡፡ እኔ ግን አላምንበትም፡፡ ፍልስፍና ሰው ከመሆን የተነሣ፣ ሰው በሰውነቱ ሊያነሣቸው የሚችላቸው ጥያቄዎች ይኖሩታል፡፡ እኔ ማን ነኝ? በእዚህ ዓለም ውስጥ ምንድን ነው የምሠራው? ከየት መጣሁ? ወዴት ነው የምሔደው? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንኛውም ሰው ሊያነሣ፣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ እንዲሁም ድሆች እንዲህ ያለውን ጥያቄ የበለጠ የሚያነሡት ይመስለኛል፡፡ ሁሉም ነገር የተሟላለት ሰው ከሚጠይቀው ይልቅ ብዙ ነገሮች ያልተሟሉለቱ ሰው ለምን አልተሟሉልኝም ከሚል ጥያቄ፣ የሕይወትን ትርጉም ለማወቅ የበለጠ ተፈላሳፊ የመሆንና ወደፍልስፍናውም የመግባት ሰፊ እድል ያለው ይመስለኛል፡፡ ብዙ ሰዎች ለኢትዮጵያዊ ፍልስፍና አይሆንም፡፡ አስፈላጊም አይደለም የሚሉት ነገር ሐሰት ነው ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም እንደ ብዙው ኢትዮጵያዊ ደሀ ሆኜ ኖሬአለሁና፡፡ ደሀ መሆኔ የፍልስፍናን ፍላጎቴን ከልክሎ አያውቅም፡፡ የበለጠ እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡ ለምን ደሀ ሆንን? የሚለው የኢኮኖሚስቶች ወይም የታሪክ አጥኚዎች ጥየቃ ብቻ አይደለም፡፡ በመሠረታዊነት ድህነት የፍልስፍናም ጥያቄ ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ፍልስፍናን የመሥራት ችሎታ ያላቸውና አካባቢውም የበለጠ የሚገፋፋቸው ይመስለኛል፡፡ ይችላልም ብዬ አምናለሁ፡፡ እኔንም ገፋፍቶኛልና፡፡” (አፅንዖት የእኔ)

በዕርግጥ  “ድህነት” ያፈላስፈል በሚለው ሐሳብ መስማማት የሚያስቸግር አይመስለኝም። ነገር ግን በግርደፉ ስንመለከተው ለዕኛ ድህነታችን ቁጭ አድርጎ ሲያፈላስፈን አላይም። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ጥያቄውን በአፋጣኝ መመልስ የሚችሉ መፍትሔዎችን እንፈልጋለን። ወይም ይሄማ “የአርባ ቀን ዕድሌ ነው!” ብለን ተሰብስበን እንቀመጣለን። (በዕርግጥ መልስን ፈልጎ ለማግኘትስ “የዳቦ ሩጫችን” ያስችለናል!) ይሄ ከላይ ያነሳሁት ሐሳብ በራሱ ፍልስፍና ነው! ግን መደባኛ (አካዳሚያዊ ) አይደለም? ግን ወንድም ተድላ ድህነቴ ለመደበኛ ፍለስፍና መርቶኛል ብትለኝ ሊዋጥልኝ አይችልም?

 

ፍልስፍና እና ኦሾ

“ስለዚህ ነገር በግል ከሚያውቁኝ ሰዎች ጋር አውርቻለሁ፡፡ ጽሑፎቹን አላነበብኩም፡፡ ሆኖም አንዳንድ በየገበያው ያሉ መጻሕፍት ለአብነት የኦሾ መጽሐፍ የፍልስፍና ይዘት አለው ወይ ቢባል አዎን ባይ ነኝ፡፡ የፍልስፍና ይዘት አላቸው፡፡ የምናምናቸው ነገሮች የፍልስፍና ቅኝት ስላላቸው ለአብነት ኦሾ ፈጣሪ አለወይ ለሚለው ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ ይኖረዋል፡፡ አለ ወይም የለም ብሎ ቢል ይህ ፈላስፎች ሁሌም ሲያነሡ ሲጥሉት የኖረ ጉዳይ ነው፡፡ እሱ የጻፋቸው ነገሮች የፍልስፍና ምልከታ አላቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ የሚታየውንም ሆነ የማይታየውን ዓለም በተመለከተ ሰዎች የራሳቸው አመለካከት አላቸው፡፡ የኦሾም ሆነ ሌሎች መጻሕፍት የፍልስፍና ይዘት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ጥሩ ናቸው ወይ? ለሕዝቡ የሚጠቅሙ ናቸው ወይ? ከባህላችን ጋርስ ምን ያህል ይሄዳሉ?  ከብዙ ሰዎች እምነቶች ጋርስ ይስማማሉ ወይ? ለሚለው ጥያቄ ማለት የምፈልገው አለኝ፡፡ እዚህ አገር ከመጣሁ በኋላ ሰዎች ከሚሉትና እኔም በጥቂቱ ለማንበብ ከሞከርኩት ከባህላችንና ብዙ ሰዎች ከሚያምኑት ጋር የሚጋጩ ነገሮች አይቻለሁ፡፡ የሂንዱ ይዝምና ቡድሂዝም እምነቶችን በእኛ አገር ካለው የክርስትናና እስልምና ጋር በሚጋጭ ዓይነት መልኩ ነው ጽሑፎቹ የሚቀርቡት ይባላል፡፡ ብዙ ሰዎች ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡ እምነታቸውን የጣሉም አሉ ይባላል፡፡ አሁን ደግሞ የኦሾን እምነት የሚከተሉ እንዳሉም ይነገራል፡፡ ሰው የፈለገውን ማመን ይችላል፡፡ መብቱም ነው፡፡ ነገር ግን የምናነበው ነገር እውነት ነው ወይ ብለው ቢመዝኑና ቢገመግሙ መልካም ነው፡፡ እውነቱንና ሐሰቱን ለመለየት አመክንዮ ያስፈልጋል፡፡ ቁጭ ብለው በማሰብ ምክንያቱን ማወቅ አለባቸው፡፡ የሰማነውን ነገር ሁሉ እውነት ነው ብለን ካመንን ምስኪኖች እንሆናለን፡፡ ትክክለኛም መሆን አለብን፡፡ ስለዚህ ሰዎች ለሚያምኑትና ሕይወታቸውን ለሚመለከት ጉዳይ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ ጊዜ ወስደው ቢመለከቱ አንዳንዶቹ የተሳሳቱ ሆነው ሊያገኟቸው ይችላሉ፡፡ ሰዎችን በአሉታዊ ተጽዕኖ ከትክክለኛው የሕይወት መስመር የሚያስወጡ ከሆነ ትክክለኛ ስለመሆናቸው ያጠራጥራል፡፡ የኦሾን መጽሐፍ አንብበው መርዝ የጠጡ  ወጣቶች እንዳሉ ሰምቻለሁ፡፡ መርዝ የሚያስጠጣ ፍልስፍና ጥሩ ፍልስፍና ነው ብዬ አላስብም፡፡ እነዚህ ነገሮች በጥንቃቄ ካለማሰብ የሚመጡ ነገሮች ናቸው፡፡ ፍልስፍና መርዝ የሚያስጠጣበት ምክንያት አይታየኝም፡፡ ለዚህ የተጋለጥነው በትምህርት ሥርዓታችን አመክንዮን ወይም ፍልስፍናን በደንብ ካለመስጠታችን ሊሆን ይችላል፡፡”

በርከት ያሉ “ዘመነኛ”  ወጣቶች ዖሾን ልክ እንደ ነብይ ነው የሚያዩት! ዕሱ ግን  “የገንፎ ውስጥ ስንጥር” ሆኖባቸዋል። ምክንያቱም ከሐይማኖት ከባህል ዕስራት ነፃ አውጥቶ በነፃነት ሽቅብ ያጎነናል ያስባሉ፤ ዖሾም በአንዳንድ ፅሁፎች ተመሳሳይ ቃል ይገባል። በመጨረሻ ግን ብዙዎቹ ዖሾን ያነበቡ ወጣቶች ብዙ ጊዜ  ሁሉን መቀበል ተስኗቸው ይታያሉ። አማለይ በሆኑ ቃለቶቹ ያደርሰኛል ብለው ያሰቡት ቦታ ላይ ሳያድርሳቸው ሜደ ላይ በትኗቸው ይቀራል። ለዚህ ይሆን እንዴ መርዝ የሚጠጡት! (አይ ዖሾ!) ለዚህ ሁሉ ግን መንስኤው የዖሾ ሃሳቡን መግለጥ ሳይሆን የእነዚህ ወጣቶች ያለመርመር መቀበል። “ምርቱን ከግርዱ” አለመለየት ይመስለኛል

ፍልስፍና እና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ዕጣ

 ሰዎች ያነባሉ፡፡ ከበፊቱ የበለጠ ግልጽነት አለ፡፡ ነገር ግን ትልቁ ችግር ብዙ የተማሩ ሰዎች አይጽፉም፡፡ በእኛ ሰዎች የተጻፉ ነገሮችን የማንበብ ዕድል ብዙም የለም፡፡ የእኛ ሰው ለምን አይጽፍም ብዙ ማብራሪያ ሊኖረው ይችላል፡፡ ለእኔ ግን የሚመስለኝ በልማዳችን ከመጻፍ ይልቅ ማውራት ይቀለናል፡፡ ወሬውን መስማት ራሳችንን ከምናደርገው ጥናት የበለጠ ቦታ ያለው ነው፡፡ ሁሉም ነው ማለቴም አይደለም፡፡ ለማንበብ ፍላጎት ያለው ሰው አእምሮውን የሚያሳድጉ ነገሮችን፣ በጥንቃቄ አሁን ካቆምንበት ቦታ ወደፊት ሊያስኬዱ የሚችሉ መጻሕፍት ቢጻፉ ብዙ ሰዎች ይጠቀማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ፍልስፍና የበለጠ ሊሠራበትና ሰውም የሚቀበል ስለመሆኑ ከራሴ አንዳንድ ተሞክሮዎች አይቻለሁ፡፡ ስለዚህ የሚጽፉ ሰዎች መበረታታት አለባቸው፡፡ መቼ እንደሚወጣ ባላውቅም የአቅሜን እየጻፍኩ ነው፡፡

“ሰዎች ያነባሉ።”  እኔ እንጃ!  የስፖርት ጋዜጣ አንባቢዎች ቁጥር እያሻቀበ እንደሆነ አያለሁ! በፍቅር እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ጋዜጦችንም የሚያነቡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። በመፅሐፍት ረገድ ካየነው ግን  “ማዝናናትን” ዓላማ ካደረጉ ፅሁፎች በስተቀር ብዙ መፅሐፍትን ሲነበቡ አላየሁም። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) ከበፊቱ የበለጠ ግልጥነት አለ። እዚህም ጉዳይ ላይ ከላይ የጠቀስኩት አይነት አመለካከት ነው ያለኝ። “መፃፍን” በተመለከተ ግን እንዲያውም ከዚህ በላይ ብጮህ ደስ ይለኛል። ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ስናወራ እንታያለን ነገር ግን እነዚህን ጉዳዮች በወረቀት አስፍሮ ለህዝብ በማቅረብ በኩል ግን ይቀረናል። ለዚህ መንስኤው  የትምህርት ቤት ቆይታችን ይመስለኛል። ብዙዎቻችን የምንበረታታው የተፃፈን እንደንገለብጥ ነው እንጂ ራሳችን እንድንፅፍ አይደለም። ተድላ እንዴት ግልፅ እንዳለው አላውቅም እንጂ  እንደ እኔ አስተያየት “ግልፅነት” ላይ ለመድረስ ብዙ ይቀረናል። በተለይ ፊደል ቆጥረናል የምንል ሰዎች ሓሳባችን በፅሁፍ አኑረን ለትውልድ ልናሳልፍ ይገባል። የፃፉትንም ደግሞ ገዝተን በማንበብ እናበረታታ!

ለማንኛውም  ዕሰቲ እናንተም የምትሉትን አጫውቱኝ !

ተድላ እና ሪፖርተር ጋዜጣ ያደረጉትን ወግ ግን ተጋበዙልኝ ? (ይህንን ይጫኑ)

Advertisements

6 thoughts on “ተድላ ገብረ የሱስ ፦ ፍልስፍና እና ድህነት ፤ ፍልስፍና እና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ዕጣ፤ ፍልስፍና እና ኦሾ

 1. Hi Abinet:

  First, I want to thank you so much for your kinds words about me. You’re very kind.

  Second a few thoughts about some of the things expressed in the Interview (by the way, I was told that there is a sequel to this interview, which is part of one longer interview I gave, that is coming out this Sunday]:

  About how the interview got transcribed: I gave the interview mostly in guramayle (mixing some English words with Amharic. Then I gave the person who interviewed me the right to edit the interview, weed out the English words, and also try his best to express what I tried to communicate in his own words. This creates some problem and there are a few thoughts in the published interviewed that I was not sure if they would correctly communicated what I meant to say. No blame game here. This is inevitable when two people with different backgrounds try to work together. I’m pleased generally at the way my interviewer tried to do–translating my thoughts in good, readable Amharic. The credit goes to him.

  Having said the above I can add a few thoughts on your comments:

  Being poor might not immediately motivate some people to become academic philosophers. I did not say in the interview that being poor was the only reason or the main reason for my being in academic philosophy. I only suggested the idea of as a motivating factor.

  One who is struck with some fundamental existential questions as a poor person could end up being a professional philosopher if that person found himself in the right circumstances that positively contribute to the pursuit of philosophy professionally. My case has more to do with finding myself asking most fundamental questions about existence and the meaning of life in this universe that led me to more fundamental questions in philosophy. The question of truth is one example that kept me moving in the direction of philosophy right after the fundamental metaphysical questions that are familiar to philosophers. I think this is enough for now.

  I’ll return to say a few things about other comments you’ve made.

  Cheers,

  Tedla

 2. P.S. I forgot to add this thought in my previous comment: You’re right that poverty when it’s deep like in our society does not provide an opportunity for philosophizing with a long term solution to pressing experiences of poverty. That is obvious and it’s from this obvious point that many seem to infer that being poor is never compatible with taking a longer period of time to examine long-term solutions to poverty in general. That I think is a bad inference. A person who is economically poor, who can barely survive like his fellow poor people, can still be determined to go for a much longer and extended philosophical pursuit in order to understand the root causes of poverty in one’s community and how to address such pressing issues of poverty both short-term and long-term. I’m not working on the philosophical analysis about poverty but then I’ve also taken a long-standing interest in the sense of trying to understand why poverty, the kind of poverty for which our society is well know for a long time, is with us and what to do about it. My main concern, however, is about poverty of ideas that I think are fundamental causes for poverty in its various manifestations, economic and otherwise.

 3. More comments:

  As for what I said in the interview about Osho and his influence in our society I think I can add this for now: After I gave this interview I had opportunities to read some of Osho’s writings and have had chances to speak on the subject to a couple of audiences. After my experience with the audience and based on many requests to address Osho’s works I committed myself to writing a book-long response to Osho, which will, hopefully, come out sometime next year this time or so.

 4. More comments:

  As for what I said about reading in our culture: What I said should be taken in context in the following sense: I was comparing, even it was not clear from the interview, the public consumption of books, esp., books translated into Amharic including Osho’s, and my observation of this compared to what I knew was the case in our society, not that many years back, shows some sign of reading culture on the rise. But this need not be interpreted as only reading good books, speaking of good books some might want to exclude books such as on self-help or motivational, etc. If pressed, I’d say reading some books is better than not reading anything at all. Probably, this habit being developed even reading self-help books could be a stepping-stone for a better reading habit for better books later on. That is a good thing overall, as I think. But that does not mean that ours is a reading culture–we are not there yet.

  I spoke about “openness” in the following sense: People in our society were not open to read books like Osho’s, esp., books that are critical of religious beliefs. But that seems to be changing and this change could be taken as a sign that people are being more open to reading books that once were considered taboo. Open-mindedness if it’s a consequence of openness is a virtue and I was trying to say something about this.

 5. Hi Abinet:

  This is just to say a few things about why I wrote my comments in English: First, I don’t know how to use Amharic to type here. Second, even if I do have some basic knowledge, my Amharic is not good enough to communicate my thoughts–as I think.

  Otherwise, I appreciate the fact that there is an Amharic blog to which I can contribute something whenever I can if my doing so in English is okay.

 6. Note:

  The sequel to the last interview did not come out today. I was told that it would. Probably it’ll come out in another issue. I’ve no further info at the moment.

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s