መጣጥፍ Articles

120 ‘ጅምላ ጨራሽ’ አስተሳሰቦች ፦ 120. “ሁሉም አንድ ናቸው!”

 

ሰሞኑን የምሰማቸው ወሬዎች ትንሽ ግር አሰኝተውኛል።

አንዳንዶቹን ‘ጅምላ ጨራሽ’ ብዬ ጠርቻቸዋለሁ። እነዚህ ሐሳቦቻችን የሚነሱት በውስጣችን ሸሽገን ከያዝናቸው “ጥቅል ድምዳሜዎች ነው። የአትዮጵያ ህዝብ ብለን ይጀምሩና አበበ ብለው  ያቆማሉ።የኢትዮጵያ ሕዝብ ስራ አይወድም አበበ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ስለዚህ አበበ ስራ አይወድም። እነዚህ ሐሳቦች ዘር ቀለም ስልጣኔ  አይለዩም። እነዚህን “ጅምላ ጨራሽ አስተሳሰቦች”  በእኔ እና በወዳጆቼ ባህሪ ውስጥ አይቻለሁ። በእነዚህ አስተሳሰቦች ላይ ተመስረተው ሰዎች ዱላ ሲማዘዙ፣ ፍቅር በእንጩጭ ሲቀጭ፣ ቤተክርስቲያን ስትታመስ፣ ቤተሰብ ሲፈርስ ወ.ዘ.ተ አይቻለሁ። (እናተም እንደዚያው!) እነዚህ አስተሳሰቦች ጭፍንነትን በማራመድ ህይወታችንን ተገቢ ባለሆነ አቅጣጫን የሚመሩ ናቸው። እኔ የሚከተሉትን አግኝቻለሁ እናንተ ብትጨመሩልኝ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ይሆናል።

ስለ “ጴንጤ”፡

‘ጴንጤዎች’ ሐቀኞች ናቸው፤

አብነት ‘ጴንጤ’ ነው፤

ስለዚህ አብነት ሐቀኛ ነው።

(ወይ ጉድ ! አብነት ሃቀኛ የሆነው እኮ ጴንጤ ስለሆነ ነው። ጉድ የሚፈላው ሆኜ ሳልገኝ ነው! “ሁሉ አጭበርባሪ!

ስለ ሴቶች፡

(“ባቢሎን በሳሎን” በሚለው ቲያትር ውስጥ እንዳየሁት!)

ሴቶች የሚንቃቸውን ወንድ ይወዳሉ፤

ወርቄ ሴት ነች፤

ስለዚህ ብትንቃት ትወድሃለች።  

ሴቶች የሚያስቀናቸውን ወንድ ይወዳሉ፤

ትዝታ ሴት ናት፤

ስለዚህ ብተስቀናት ትወድሃለች።( ሴተኛ አዳሪ አምጥተህ አስቀናት!)

ስለ ወንዶችን፡

(በ”ባቢሎን በሳሎን” ቲያትር ውስጥ እንዳየሁት!)

ወንዶች ፊት ሲያዩ አይቻሉም፤

አብነት ወንድ ነው፤

ስለዚህ ፊት አታሳይው። (ስለዚህ አንዱን በገንዘብ ገዝተሽ አስቀኝው!)

ስለ አበሻ ፡

አበሻ ቀጠሮ አያከብርም፤

አላምረው አበሻ ነው

ስለዚህ ቀጠሮ አያከብርም።

አበሻ ስራ አይወድም፤

አብነት አበሻ ነው ፤

ስለዚህ ስራ አይወድም።

ስለ ትዳር፡

ወንዶች ሁሉ ከገቡ በ¹ላ አይነከባከቡም፤

አላምረው ወንድ ነው፤

ስለዚህ ብታገቢው አይንከባከብሽም።

የሚዘገንነው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ሰዎች በዚህ ላይ ተመስርተው ሕይወታቸውን ሲመሩ። በእንደዚህ አይነት መረጃዎች ላይ ተመስርተው እርምጃ ሲወስዱ ስታዩ… “ኡ ኡ ኡ ኡ” ብለህ ጩህ ነው የሚያስኘኝ ! ለምን አትሉኝም? ምን መሰላችሁ?

‘ጴንጤዎች’ ሐቀኞች ናቸው ብለው አሰቀድመው የሚያስቡ ሰዎች ‘አጭበርባሪ ጴንጤ’ ገጥሟቸው ሲታለሉ። ‘ጴንጤዎች’ እንደዛ ናቸው ብለው ሲደመድሙ! ሴቶች ወንድ የሚንቃቸውን ይወዳሉ የሚል “ደካማ” አስተሳሰብ ያለቸው ወንዶች ፤ የሚወዷትን ፍቅረኛቸውን ሲያጡ!። ወንዶች ፊት ሲያዩ አይቻሉም የሚሉ ሴቶች ደግሞ ፤ ጓደኛ ፈልገው ጓደኛ አጥተው ስናይ እረ አለቅን እኮ ጎበዝ እንላለን። አበሻ ቀጠሮ አያከብርም ብለው ስንት ጓደኝነት ያፈረሱ፣ የስራ ዕድል የተዘጋባቸው፤ አበሻ ስራ አይወድም ብለው የሐገሬን አርሶ አደር አይተው ኩምሽሽ ያሉ ወ.ዘ.ተ ተዘርዝረው አያልቁም። እንዲያው እናተዬ እንዲያው ይሄ ሰውዬ ቢያገባኝ እኮ አይንከባከበኝም ብላችሁ፤ የእጮኝነት ጊዜያችሁን ያስረዘማችሁ ትኖሩ? አላውቅም ብሰማ ግን ደስ ይለኛል!

ታዲያ ምን እናድርግ? “ሁሉ”ን እንመርምራት። ስንናገር ምን እየተናገርን እንደሆነ እናስብ! “ለመናገር የዘገየን!” እንሁና ጎበዝ ሴቶች (ሁሉ)፣ ወንዶች (ሁሉ)፣ ባሎች (ሁሉ)፣ ሚስቶች(ሁሉ)፣አበሻ (ሁሉ) ሁሉ… ሁሉ… የምትባል ቃል ያለባትን አሰተሳሰባችንን መፈተሽ አለብን። እንዴት ሁሉ አንድ ሊሆኑ ይችላሉ? “ሁሉንም” ሰዎች (ወንዶች፣ ሴቶች፣ባሎች ፣ሚስቶች፣ አበሾች)  እኮ አናውቃቸውም! ስለዚህ እሷ ልዩ ልትሆን ትችላለች! ዕሱም ዕኮ ልዩ ሊሆን ይችላል! ብለን ብንመረምርስ ?

ዕኔ “ሁሉን” አላወቅ እናንተ ደግሞ ዕስቲ መፍትሔ የምትሉትን ስደዱልኝ እና እንወያይበት!

ይርዳና!

Advertisements

One thought on “120 ‘ጅምላ ጨራሽ’ አስተሳሰቦች ፦ 120. “ሁሉም አንድ ናቸው!”

  1. ከላይ የተጠቀሱት እውነት ናቸው አንዳንድ ጊዜ እኛ እራሳችን ሆነን ተገኝተናል ወይ? ሌላውን ሰአት አያከብርም ብለን ከመውቀሳችን በፊት እኛ ሆነን መገኘት ያለብን ይመስለኛል ከዛ ሌላውን ማስተማር እንችላለን ጴንጤ ነኝ ያለ ሁሉ አይደለም ሁሉንም በጅምላ ባይጠራ መልካም ነው እላለሁ ሌላው ከፍሬው ያስታውቃልና
    ስለ ጋብቻ የተነሳው ነገር አለ አንዷ ወይ አንዱ ያለፈበትን እኔ ላላልፍበት እችላለሁ እረጅም ጊዜም ወስደን ስለተጠናንም አይሆንም እራሳችን እንደምንፈልጋቸው ባህሪዎች እራሳችንን አዘጋጅተናል ወይስ ካንድ ወገን ብቻ ነው የምንጠብቀው ሌላው ብዙ ጊዜ አበሻ አበሻ እንላለን እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ እግዚአብሔር ለሌላው አለምና ላበሻው የሰጠው ጭንቅላት የተለያየ ነው እንዴ? እኔ እንደሚመስለኝ በአይምሮ መለወጥ ነው ያለብን ቀጥሉበት በጣም አሪፍ ነው!!!!!!!!!!!

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s