ምን ይወራል ? News

ሶፋኒት አበበ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ፦ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ፣ሳይንስ ፣ ራዕይ

በማይከሮ ባዮሎጂ የዶክተሬት ዲግሪዋን እየሰራች የምትገኘው ወጣት ሶፋኒት አበበ  በዚሁ ብሎግ  ላይ ባለፈው ሳምንት ክርስትና እና ሳይንስ (Christianity and Science) በተመለከተ የሰንበት ቡድን (Sunday Group) ላዘጋጀው ሴሚናር ያቀረበችውን  ወረቀት በተመለከተ የዕኔን ምልከታ  አቅርቤላችሁ ነበር ። ይህች ክርስቲያን (“ወንጌላውያን”) ወጣት ጁላይ 27 2010 ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያደረገችውን ቃለ ምልልስ ቀንጨብ አድርጌ አቅርቤላች¹ለሁ።

ስለራሷ

ወጣት ሶፋኒት አበበ ዛሬ፣ ሐምሌ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. 26ኛ ዓመቷን ትይዛለች፡፡ ዓመት ከመንፈቅ ሲሞላት ደግሞ የዶክትሬት ዲግሪዋን ታጠናቅቃለች፤ በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ፣ ዌልስ ዩኒቨርሲቲ ከምትማረው የማይክሮባዮሎጂ ትምህርት በተጓዳኝ በረዳት መምህርትነት ስትሠራ ቆይታ፣ በአሁኑ ወቅት በመምህርትነት እየሠራች መሆኗን አጫውታናለች፡፡ተወልዳ ያደገችው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን፣ ለከፍተኛ ትምህርት እስክትበቃ ድረስ የትምህርት ገበታን የተቋደሰችው በናዝሬት ትምህርት ቤት ነበር፡፡
በውጭ አገር ለሰባት ዓመታት ያሳለፈችው ሶፋኒት፣ ከመነሻው የከፍተኛ ትምህርትን ደጅ የረገጠችው በውጭ አገር ነው፡፡ የመጀመርያ ዲግሪዋን በባዮኬሚካል ኢንጂነሪንግ፣ የሁለተኛ ዲግሪዋን ደግሞ በባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ ሁለቱንም በጀርመን አገር ተከታትላለች፡፡ እዚህ አዲስ አበባ ለእረፍት በመጣችበት ወቅት በአንድ ሴሚናር ላይ አገኘናትና ከወጣትነት ጋር በተያያዘ ጉዳዮችና በሌሎችም ላይ እንድናወጋ ፈቀደችልን፡፡  

 ስለ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች  

ለሰባት ዓመታት በትምህርት በቆየችባቸው የውጭ አገራት አንዳንድ ያጋጠሟት ጉዳዮች ካሉ በሚል ጠይቀናት ነበር፡፡ በውጭ ቆይታዋ በተለይ በጀርመኗ ፍራንክፈርት ከተማ፣ በጊስን ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪዋን በመማር ላይ ሳለች ያጋጠማትን አወጋችን፡፡

“ያሳዝናል፤ ያናድዳልም፤ ነጠላ ስለለበሱ አበሾች ናቸው ብዬ ሳዋራቸው ሊያዋሩኝ ፍላጐት አልነበራቸውም፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ በዘርና በመሳሰሉት የተከፋፈሉ ናቸው”.፡፡” ወጣቶች ሆነው በዚህ ዓይነት ሁኔታ መገኘታቸው፣ “በሰፊ አእምሮ ነገሮችን ከመመልከት ይልቅ በቆየ አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ክፍፍል አለ፤” ስትልም የገጠማት ጉዳይ አሳዛኝነቱን አስረድታለች፡፡

እንደ ሶፋኒት ምልከታ፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወጣት “ዝምተኛ፣ የማይጠይቅ፣ ወደ ራሱ፣ ወደ ውስጡ የሚመለከት ነው፤” በዚህም “ከተሠራበትና ከተሣለበት” ወጣትነት መውጣት ሲከብደው፣ ልዩነትን ለማሳየትም ሆነ ለመግለጽ ሲቸገር ይታያል፡፡
በራሷ መርሕ እንደምታምነው፣ “ሰዎች የተፈጠሩት በዓላማ ነው፡፡ ሰዎች ከፈጣሪ ያገኙትን ለሌሎች ለመግለጽና የተፈጠሩባትንም ዓለም ተንከባክበው ፈጣሪን ለማክበር የተፈጠሩ ናቸው፡፡”

ሳይንስ እና …

ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ ከሳይንስ ጋር የተቆራኙ ሰዎች ራሳቸውን ኅብረተሰባቸውን፣ ባህላቸውንና ሌሎችንም ጉዳዮች ለምን? እንዴት እያሉ መጠየቅን አመጡ፤ ሁሉንም ነገር በሚለኩበትም እይታ ላይ ሳይንስ ተጽዕኖ ፈጥሯል የምትለው ሶፋኒት፣ ከዚያ አንፃር እኔም እንደ ግለሰብ የምቀበላቸውን ነገሮች ለምን ብዬ እንድጠይቅ፣ ጥቅማቸውና አስፈላጊነታቸው ምንድን ነው? እያልኩ መጠየቅ እንዲኖርብኝ አድርጓል ስትል አክላለች፡፡

“አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ ወይም በልማድ የያዝኳቸውን ነገሮች፣ መጣል ያለባቸውን እንድጥል፣ ያልያዝኳቸውንም እንድይዝ ረድቶኛል፤”
አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከራሳቸው ኅብረተሰብ አይወጡም፤ በራሳቸው ክልል ታጥረዋል የሚል ትዝብቷን ከውጭው ዓለም ወጣቶች ጋር አመሳክራ አጫውታናለች፡፡ እዚያው በውጭ አገር ተወልደው ላደጉት ጉዳዩ የተለየ ቢሆንም፣ ከኢትዮጵያ ሔደው በውጭ ለሚኖሩ ወጣቶች ሁኔታዎች የሚከብዱበትና የሚምታቱበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ 

እንደ ሶፋኒት ምልከታ፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወጣት “ዝምተኛ፣ የማይጠይቅ፣ ወደ ራሱ፣ ወደ ውስጡ የሚመለከት ነው፤” በዚህም “ከተሠራበትና ከተሣለበት” ወጣትነት መውጣት ሲከብደው፣ ልዩነትን ለማሳየትም ሆነ ለመግለጽ ሲቸገር ይታያል፡፡
በራሷ መርሕ እንደምታምነው፣ “ሰዎች የተፈጠሩት በዓላማ ነው፡፡ ሰዎች ከፈጣሪ ያገኙትን ለሌሎች ለመግለጽና የተፈጠሩባትንም ዓለም ተንከባክበው ፈጣሪን ለማክበር የተፈጠሩ ናቸው፡፡”

ራዕይ

የዶክትሬት ዲግሪዋን ካጠናቀቀች በኋላ ምን ለመሥራት እንዳሰበች ጠይቀናታል፡፡ ወደ አገሯ በመመለስ፣ የሥራ ዕድል ካገኘች ለማስተማርና ከእሷ በዕድሜ ያነሱትንም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የማማከር ሥራ ለመሥራትና ከእምነቷ ጋር በተያያዘም እንቅስቃሴ ለማድረግ ሐሳብ እንዳላት አጫውታናለች፡፡

ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከሪፖርተር ያንብቡ

Advertisements

One thought on “ሶፋኒት አበበ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ፦ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ፣ሳይንስ ፣ ራዕይ

  1. nice to entertain people like Sofanit on your blog. It will motivate and encourage many Christians to engage in academic. Keep on moving.

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s