ምን ይወራል ? News

ክርስትና እና ሳይንስ (Christianity and Science) ፡ በሞሎኩላር ማይክሮ ባዮሎጂሰቷ በወ/ት ሶፋኒት አበበ አይን

በሰንበት ቡድን (Sunday Group)  አዘጋጅነት ሰኔ 26 ቀን 2002 ዓ.ም ደቀ መዝሙርነት እና የክርስቲያን   አዕምሮ (Discipleship and the Christian Mind) በሚል ርዕስ የተካሄደውን ልዩ ሴሚናር እና የእኔን  አስተውሎት ባለፈው ሳምንት ማስቃኘቴ ይታወሳል። በአቶ ነብዬ ዓለሙ ፅሁፍ  ዙሪያ ላቀረብኩት ሐተታ ብዙ የ“ትንንሽ ሐሳቦች” አንባቢዎች ለሰጣችሁኝ ገንቢ  አስተያየት አመሰግናለሁ። በተለይ የግል አስተውሎቴን በተመለከተ አንዳንድ ወዳጆቼ ትንሽ እንደተቀየሙኝም መገንዘብ ችያለሁ። እነዚህ ወዳጆቼ ሐሳባቸውን በፅሁፍ ለትንንሽ ሃሳቦች ቢሰዱ አደባባይ እናውለው እና ለውይይታችን እና ለሙግታችን መንስዔ ይሆን ነበር።

ዕስቲ ለማንኛውም  የሞሎኩላር ማይክሮ  ባዮሎጂ ባለሙያ የሆነችውን የወ/ት ሶፋነት አበበን ክርስትና እና ሳይንስ (Christianity and Science) የሚል ወረቀት እና የእኔን ምልከታ ላቅርብላችሁ። ምናልባት በመጨረሻው ክፍል የአዘጋጆቹን  እና ተሳታፊዎች ጋር የማደርገውን ውይይት  አንደ መደምደሚያ  አቅጣጫ አመላካች ሐሳብ አቀርበዋለሁ።

ክርስቲያናዊ አዕምሮን ለማሳደግ ዕንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች

1. አንዳንድ ሰዎች ዕንደ ወ/ት ሶፋኒት አገላለጥ ክርስቲያን ሲሆኑ “አዕምራቸውን አስቀምጠው” የመጡ ይመስላቸዋል። ስለዚህ ለክርስቲያናዊ አዕምሮ ዕድገት ትኩረት አይሰጡም።

2.  “እንደ ህፃን ያለ ዕምነት እና  እንደ ህፃን ያለ አስተሳሰብን” ይደባልቃሉ። ነገር ግን እንደ ህፃን ያለ እምነት እንጂ እንደ ህፃን ያለ አመለካከት እንድናዳብር አልተጠራንም ።

3.  መንፈሳዊ ጉዳዮችን ጥያቄ ስንቀበል መንፈሳዊ የሆንን ይመስለናል። ይሄ ጉዳይ ምክንያታዊነትንን እና ማሰብን የሚያበረታታ አይደለም።

4. “አዕምሮዬን ስጠቀም እስታለሁ።” የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ስንመለከት ግን የቤተ ክርስቲያን አባቶች በአመክንዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ በአመክንዮ ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን እንመለከታለን። (በዚህም ጣልቃ “የጥያቄውን ምንጭ ማሰስም” ልማድ ሊኖረን ይገባል ስትል ታበረታታናለች።)

5. “ባለ አዕምሮ ነን ባዮች ፀረ- እምነት አመለካከት ስላላቸው።” እናስባለን እንመራመራለን የሚሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን መኖር ይክዳሉ ስለዚህ እኛም አዕምሯችንን ብንጠቀም እግዚአብሄርን እንክዳለን የሚል ፍራቻ።

የክርስትና እና ሳይንስ “ቅያሜ”

ወ/ት ሶፋኒት ሳይንስ ይህንን ፍጥረታዊውን ዓለም ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ማጥናት የስራው ድርሻ ሲሆን የእግዚአብሔር መኖር እና አለመኖር ጉዳይ ግን የሳይንስ ጉዳይ እንዳልሆነ አስምረውበታል።   የክርስትና እና የሳይንስ “ ቅያሜ” መነሻ የሆነው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ኮፐርኒከስ የተባለ መነኩሴ ሳይንቲስት (በመጨረሻም ጋሊሊዮ) ያነሱት  በመሬት እና በፀሐይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ንትርክ ነበር። እነዚህ ሰዎች በእርግጥ አማኞች ቢሆኑም ፤ እሷ ዕንደገለጠችው ውዝግቡ ሳይሆን ከጀርባው “ልዩ” ተልዕኮ ያላቸው ሰዎች የራሳቸውን አጀንዳ ለማራመድ ተጠቀሙበት።  በዚህም የተነሳ ሳይንስና ሐይማኖት  ቅያሜያቸው ተጀመረ።

ይህንን ጉዳይ የሚያፋፍሙ  በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የታተሙ አምስት ያህል መፅሓፍት ሲሆኑ ከዕነዚህም መካከል The History of the conflict of Religion and Science (19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ የተፃፈ) The History of the warfare of science and Theology የመሳሰሉ መፅሐፍት ይገኙበታል። ለዚህም ምላሽ በሚሆን ሁኔታ በክርስትና ውስጥ ‘መሰረታዊነት’ (Fundamentalism) የሚል ንቅናቄ እንደ ተጀመረ እና የሳይንስ እና የክርስትና አለመግባባት እንደተባባሰ ትናገራለች። ( ከሳይንሳዊነት አልፎ ወደ “ዕምነትነት” እተጠጋ ያለውን  እነ ሪቻርድ ዶውኪንሰ እና ሳም ሀሪስ እና ሌሎች የሚያረምዱት ‘ሳይንሳዊ ቁሳዊነት’ (Scientific Materialism) ልብ ይሏል!)

በመቋጫውም

ወ/ት ሶፋኒት ስለ ሳይንስ እና ክርስትና ያላቸውን ግንኙነት መወያየት የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉት አብራርታ ከነዚህም መካከል የሚከተሉትን ጎላ አደርጋ አስቀምጣቸዋለች።

1. “የተፈጠረው ፍጥረት ወደ ፈጣሪው ያመለክታል።” (መዝ 19፡1-2)

2. ሳይንስ እና ክርስትና ባላቸው ግንኙነት ዙሪያ “ውይይት እና ክርክር”  ያስፈልጋል።

3.የተለያዩ “ህብረቶች” ተፈጥረው “ዕምነታችንን በሕይወታችን ውስጥ ለመግለጥ” ጥረት ማደረግ ይገባናል።

4. የንባብ ቡድኖች (Book Club) ሊኖረን ይገባል።

የእኔ አስተውሎት

1. እኔ ግን አዕምሮን ላለመጠቀም ዕንቅፋት ይሆናሉ ብላ የሰነዘረቻቸው ምክንያቶች ሚዛን ደፍተውብኛል። ሶፋኒት ዕንዳለችው አንዳንድ ሰዎች ልክ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ “አዕምሯቸውን አሰቀምጠው”  መምጣት ያለባቸው ይመስላቸዋል። ለዚህም ይመስለኛል አንዳንድ ጊዜ ግራ የሚያጋቡ መንፈሳዊ ልምምዶች ሲታዩ ወይም ትንቢቶች ሲሰጡ፣ ወይም የስህተት ትምህርት ሲሰበክ አጥርተው የማያስቡት ወይም ደፈር ብለው የማይናገሩት። ምናልባትም ሐሳብ ብሰነዝር “ደረቅ”(ወይም ‘መንፈስ የሌለበት!’ ይሄ ቃል በራሱ መንፈሳዊነት አዕምሮን ካለመጠቀም ጋር ተዛምዶ ያለው መሆኑን እንደሚያሳይ ልብ ይሏል!) እባል እና መድረክ እከለከላለሁ ወይም ሌሎችን አሰናክላለሁ ወ.ዘ.ተ የሚል ስጋት ይመስለኛል።  ከዚህ በተለየ ደግሞ ስንመለከተው የምናምነውን ነገር ከተማርነው ከተሰበክነው በዘለለ ስለማናውቀው እነዚህ ሰዎች ሞግተው  “ያዋርዱናል” የሚል ስጋትም ይጠፋል ብላችሁ ነው።( አንድ ወዳጄ ተምረናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን አድምተው ሳያነቡ አንብበናል ይሉና በትዕቢት ይሞላሉ፤ የእኔም ጥሪ ይህንን ትምክህት ማፍረስ ነው ይለኝ ነበር። ምን ላይ ደርሶ ይሆን?)

2. ልክ ወ/ት ሶፋኒት “ስንጠይቅም የምንስት ይመስለናል” ብላ ነበር። በዚህም እስማማለሁ!  ዕሰቲ ላብራራው! በጭፍን ካላመንን በስተቀር እንዲያው ጥቂት ከጠየቅን “የእግዚአብሔርን አለመኖር” እናረጋግጥና ጉዳችን ይፈላል ብለን ስለምናስብ፤ እንዲያው ተመራምረን ከሐዲያን ከመሆን ሳንመራመር “በጭፍን”  አምነን መቀመጡ ይሻለናል።(Intellectual snobbery የሚሉት ይሆን!) ጎበዝ እንዲህ ከሆነ እኮ በአንድ ገዜ የሚመጣው ፍልስፍና አጥቦ ሊወስደን ነው!

3. ስለ “ሕብረቶች” እና ስለ “የንባብ ቡድኖች” ያነሳቻቸው ሐሳቦች ማርከውኛል። (ለዚህ ሐሳብ ደግሞ ድንቅ ምሳሌ የሚሆነን ይህንን መርሐ ግብር ያሰናደው የሰንበት ቡድን (Sunday Group) ነው። ዕነሆ አድራሻቸው http://blog.ethiosundaygroup.com/)  የእኔም ጩሀት የዚህም የ“ትንንሽ ሐሳቦች” ዋና ዓላማ በወቅታዊ በሐገር ውስጥ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚወያይ እና ክርስቲያናዊ አስተውሎትን የሚያቀብለን በኢትዮጵያ ውስጥ ክርስቶስን ዕንዴት መከተል እንደምንችል የሚያመላክተን  የወንጌላውያን አማኞች ቤተሰብ መፍጠር ነው።)

4. ለእኔ ግን አሁንም በወ/ት ሶፋኒት  ሆነ በሌሎች ሰዎች ሲመለስ የማላየው ጥያቄ “የስልጣን ጉዳይ” ነው። ወዳጆቼ ሳይንስ እና ክርስትና አንዳንድ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁለቱም ባለስልጣን ሆነው ይቀርቡልናል (አንዱ ‘በጥናት’ ተረጋግጧል ሲለን ሌላው ‘መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል’ ይለናል።) ክልላቸውን የማናውቅ ከሆነ ዕንዴት ነው? በየዕለት ህይወታችን የሚያጋጥሙንን ሳይንሳዊ እውነቶች እና መፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች አጣጥመን የምንጓዘው?

(ሐሳባችሁን በፅሁፍም ሆነ በስልክ ብታቀብሉኝ ደስታዬ ዕልፍ ነው! ምስጋና ለቴዲ፣ለሚኪ፣በአጠቃላይ ለሰንበት ቡድን አባላት እና ለ“ትንንሽ ሐሳቦች” ቤተሰቦች። ለትንንሽ ሐሳቦቼ ጊዜያችሁን ስለ ቆነጠራችሁልኝ። ዕሱ ይባርካችሁ! በመጨረሻው ክፍል  የክርስቲያን አዕምሮ እና ፍልስፍና (Philosophy and the Christian Mind)  አቶ ተድላ ገብረየሱስ (በሴይንት ሉዊስ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና የፒ.ኤች.ዲ ተማሪ) ባነሳቸው ሐሳቦች ዙሪያ እናወራለን።)

Advertisements

3 thoughts on “ክርስትና እና ሳይንስ (Christianity and Science) ፡ በሞሎኩላር ማይክሮ ባዮሎጂሰቷ በወ/ት ሶፋኒት አበበ አይን

 1. Hi Admin:

  I apologize for using English, as my laptop does not have Amharic editing software.

  Yours is an amazing blog and it’s encouraging to see Amharic blogs. Good job! I was also present in this seminar and would like to say a few things:

  Your observation no. 4: the question of ‘boundary’ and ‘authority’ was discussed – though not deeply – and it was said that Science has its boundaries so does Theology/Bible. The Bible is not a science text book and when it comes to attesting scientific ideas/facts, we better stick to science. One of the reasons why the infamous ‘Galileo-Catholic Church affair/controversy’ happened was that the Church thought the Bible could serve as an astronomy text book. Science does have its limits as well. Science has no say on the existence of God and things nonmaterial- that’s the task of theology or philosophy.

  Having said that, though, there are overlaps when it comes to the orgin of life and the universe. Both the Bible and Science present us with ‘truths’ on this things; these ideas are parallel, contrasting and conflicting. This is one of the reasons why the proper use of the mind as a Christian matters; a Christian needs to understand the claims of science; whether these claims conflict with his/her faith and if they do, how to tackle these conflicts, etc…….This is because Science has become the de facto source of ‘Truth’ in the increasingly secularised world and (I would say) most of us are in one way another have been affected……

 2. Hi Abinet:

  I’ve just discovered this blog almost by chance! Good to see such a neat blog in Amharic. Sorry for sharing this in English–hope you understand.

  I’ll try to read this blog whenever I can. If I’ve something to say I’d like to share as well.

  Cheers,

  Tedla

  1. Ted,
   I would be happy if you would send me your ideas so that I might share them with my friends out there.

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s