ምን ይወራል ? News

‘ደቀመዝሙርነት እና ክርስቲያናዊ አዕምሮ’ (Discipleship and the Christian Mind) የተሰኘውን ሴሚናር (ክፍል አንድ)

(እኔ እንደታዘብኩት)

ዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 19 ቀን 2002 ዓ.ም  ልክ ዕንደ ሰሞኑ በጉም ተጀቡና ነበር የመጣችው። ቁልቁል ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ ላይ የአፍሪካ ሕብረትን ዋና ፅሕፈት ቤት እንዳለፉ፤ ከቀይ ሸክላ የተሰሩ  ሶስት ጉልላቶች ያሉት ህንፃ ልክ ድልድዩን ዕንደ ተሻገሩ ይገኛሉ። ይህ ህንፃ የኢንተርናሽናል ወንጌላውያን ቤተክርስቲያን (International Evangelical Church) ህንፃ ነው። በዚህ ግቢ ውስጥ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን የስነ መለኮት ኮሌጅ (Evangelical Theological College) ይገኛል። ይህ ትምህርት ቤት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ  ስነመለኮትን የተማሩ ሰዎችን ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያናት አበርክቷል። የ“ሰንበት ቡድን”ን (Sunday Group) ያቋቋሙት ከዚህ ትምህርት ቤት አብራክ የወጡ ተማሪዎች ናቸው።

የሰንበት ቡድን አባላት “ደቀ መዝሙርነት እና የክርስቲያን አዕምሮ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት 60 አካባቢ ተሳታፊዎች የነበሩት መርሐ ግብር የተከፈተው የማቴቴስ መፅሔት ዋና አዘጋጅ የሆነው አቶ

ሚኪያስ በላይ  መርሐ ግብሩን በማስተዋወቅ ነበር። በመቀጠልም የተጋበዘው የሰንበት ቡድኑ አስተባባሪ የሰንበት ቡድኑን ዓላማ ሲገልጥ “የተለወጠ/የታደሰ ክርስቲያናዊ አዕምሮን” ማስፋፋት እንደሆነ  ገልጦ ወቅታዊውን የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያናትን “ማሰብ ጠል” እና “ ፀረ-አዕምሮ” ሲል ነበር የገለጣቸው። ይህንንም ለመፍታት የ“ሰንበት ቡድን”  አመክንዮን (Reasoning &Logic) መሰረት ያደረገ ፤ ክርስቲያናዊ ዕሴቶችን ማዕከል ያደረገ ውይይት በሳምንት አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ለአስር ዓመታት ያህል ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ገልጦ። በተጨማሪም ህብረተሰቡን ዘልቆ ለመግባት የድረ ገፅ (Web Page) አገልግሎት የጀመሩ መሆናቸውን ገልጧል።

ደቀ መዝሙርነት እና ክርስቲያናዊ አዕምሮ

የመጀመሪያውን የመወያያ ወረቀት ያቀረቡት በማቴቴስ መፅሔት ላይ  በመፅሐፍት ዙሪያ በሚያቀርበው ቅኝት የሚታወቀው  አቶ ነብዩ ዓለሙ ነው። የወረቀቱንም ዓላማ ሲገልጥ “ ደቀ መዝሙርነትን  እና ክርስቲያናዊ አዕምሮን ከመፅሐፍ ቅዱስ እና ከኢትዮጵያ ሁኔታ አንፃር” ማስቃኘት እንደሆነ ገልጧል። የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያናት ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ሸሽታለች ያላቸውን ሁለት ምክንያቶችን አሰቀምጧል። እንደ አቶ ነብዩ ከሆነ የመጀመሪያው “ባህላችን” እንደሆነ “አጥብቆ የጠየቀ የእናቱን ሞት ይረዳል”፣ “አትመራመር”(የሐዊ ማሰታወሻዎች ክፍል አምስት ልብ ያሏል)፣ “እሱ ያውቃል” የሚሉት አባባሎቻችንን በማስረጃነት ጠቅሷል። በሁለተኛም ደረጃ ለልምምድ ብዙ ትኩረት መስጠት ሌላኛው ምክንያት እንደሆነ እና “ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በስሜት የምትመራበት ዘመን ላይ ነው(ናት)።” ሲል ይከሳል።

አቶ ነብዩ በሁለተኛ ደረጃ ያነሳው ሐሳብ “‘ምን ያክል ሰዎች አዕምሯቸውን ይጠቀማሉ?’ የሚል ሲሆን ፤ይህንንም ለማወቅ በየመፅሐፍት መሸጫ ሱቆች ሄደው መደበኛ ያልሆነ ጥናት ማድረግ ነበር። በዚህ ኢ – መደበኛ ጥናቱም በክርስቲያን ቤተ መፅሐፍት ውስጥ  በዋነኛነት የሚሸጡት “በፍቅር” ዙሪያ የሚያተኩሩ  እና  “እንዴት ሃብታም መሆን ይቻላል? ” የመሳሰሉ  መፅሐፍት ናቸው ብሏል። እንዲሁም ክርስቲያናዊ ባለሆኑ የመፅሐፍት መሸጫ ሱቆች ባደረጋቸው ጥናቶችም ያገው ተመሳሳይ ውጤት እንደሆነ ገልጦ፤ ይሄ ምን ያህል ክርስቲያኖች አዕምሯቸውን እንደማይጠቀሙ ማስረጃ ሊሆን ይችላል ብሏል። በዚሁም የወረቀታቸውን መግቢያ የደመደሙ ሲሆን ።

የፅሁፉን ፅንሰ ሐሳብም ሲያስተዋውቅ

 “የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት (ማለትም ክርስቲያኖች) አዕምሮአቸውን ተገቢ በሆነ መልኩ ቢጠቀሙ ክርስቲያናዊ ጥሪያቸውን የበለጠ በመግጽ የደቀ መዝሙርነት ጥሪያቸውን ይወጣሉ ከዚህም በተጨማሪ በሚኖሩበት በማኅበረሰብ የተሻለን/የላቀን ለውጥ (ተጽእኖ) ማምጣት ይችላሉ የሚለውን ማሳየት ነው።”

ሲሉ ገልጠዋል።  ደቀመዝሙር ማለት መምህርን መቅዳት የሱን ትምህርት ማስፋፋት ሁለንተናን (አዕምሮንም ጭምር!) የሚያሳትፍ እንደሆነ ተናግረዋል። የማርቆስ ወንጌልንም በመጠቀም “የክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆን ማለት ክርስቶስን መረዳት”(ምዕ.1-8) እና “መኖር” እንደሆነ ተናግረዋል። የክርስቲያን አዕምሮንም ደግሞ የገለፁት በሚከተለው መልኩ ነበር። ክርስቲያናዊ አዕምሮን ማዳበር ማለት ክርስቲያናዊ “ንፅረተ ዓለምን” ማዳበር እንደሆነ አበክረው ገልጠዋል። ይህም ማለት ከክርስትና አንፃር ዲሞክራሲ ፣ፖለቲካ ፣ ሳይንስ እና ሌሎች ጉዳዮች ምን ማለት እንደሆኑ መመርመር ነው ብለዋል። ለዚህም ሮሜ 12፡1-2 በማስረጃነት አቅርበዋል።

በአዕምሮ መታደስ ማለት ሒደታዊ (Progressive) እንደሆነ እና ዓለምን (Analyze) መመርመርን የሚጠይቅ ነው ብለዋል። ይህንንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ፍቃድ መለየት እንደምንችል ተናግረዋል። በተጨማሪም የማቴዎስ ወንጌል 22፡34 በመጠቀምም  ኢየሱስ “አዕምሮ” የሚለውን ቃል እንደተጠቀመ እና ይሄም ክፍል (ሁለንተናዊነት ውስጥ) መካተት አለበት ብለዋል። በመቀጠልም ቤተ ክርስቲያን በዘመናት መካከል ለሚነሱባት ጥያቄዎች በተለያየ መልኩ ምላሽ ስትሰጥ ቆይታለች። ለማያምኑ ሰዎች የመከራከሪያ ነጥቧን ግልፅ ባለ ሁኔታ ስለእምነት ስትሟገት ቆይታለች ብለዋል።

 አቶ ነብዬ በመጨረሻም የሚከተሉትን የማጠቃለያ ሐሳቦችን ሰንዝሯል።

1. ትንቢትን ከእግዚአብሔር ቃል አኳያ መፈተሽ፤ ከአመክንዮ ጋር የሚቃረን ቢሆንም እንኳን ስነምግባር እና ትንቢት  በአመክንዮ መፈተሽ ያስፈልጋል ።

2. እያመዛዘንን (Critically) ማሰብ ያስፈልገናል::

የእኔ ጥቅል አስተውሎት

1. “ዐውድ ተኮርነት” – የሰላ አስተሳሰብ አመክንዬ ዓለም አቀፋዊ ገፅታ ቢኖራቸውም እንደ የበቀሉበት አውድ ግን መገለጫቸው ሲለዋወጥ ትኩረታቸው ሰዋዥቅ አይተናል። ክርስቲያናዊ ፍልስፍና እያበበ በሚገኝበት በዚህ ዘመን እንኳን አሜሪካ የሚገኙ ኮሌጅ ውስጥ መምህራን እና አዋቂዎች የእውነት ምንጭ “ምክንያት”(Reason) ብቻ ነው ወደሚል ፅንፍ እየተመሙ ነው። በዚህ ዕምነታቸውም ላይ የተመስረተው የሚያመርቷቸው መፅሐፍት ከእነሱ ወዳጆች ባሻገር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተነባቢነት ያላቸው እንዳልሆነ ከአንደበታቸው ይሰማል። በመሆኑም ለክርስቲያናዊ አዕምሮ ትኩረት መስጠቱ የሚያሰጨበጭብ ሆኖ ፤ ተነባቢነታችን እና ተፅዕኗችን ግን “እሁድ ጠዋት መፅሓፍ ቅዱሱን ይዞ ከሚመጣው ክርስቲያን” ጀምሮ ያማከል ቢሆን ጥሩ ነው።

2. “‘የሚያስብ’ እና ‘የማያስብ’ ክርስቲያን”

ከላይ ካልኩት ሐሳብ ጋር በተያያዘ “ማሰብ ጠል” “ፀረ -አዕምሮ” የሚሉት ቃላት  ቡደንተኝነትን እንዳያሰፍኑ እሰጋለሁ። ይህም ደግሞ ጥቂት “የሚያስቡ ክርስቲያኖች” የማሰብ ስራቸውን ሲያጧጥፉት ፤ ብዙሐኑ “የማያስቡ የምንላቸው ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚያ ጋር እንዳይቃረኑ እሰጋለሁ።

3. “የአዕምሮ ምጥቀት እና የልብ ሙቀት” ይሄንን እንደ ፀሎት ልታዩት ትችላላችሁ ፡፡ እባካችሁ ሚዛን እንጠብቅ አእምሮችንን እናበልጥገው። ልባችን ግን በመንፈሳዊነት እና ከጌታ ጋር ባለን ህብረት የሞቀ ይሁን። እንዲህ አይነት ክርስቲያኖችን  ማፍራት ላይ ትኩረት ቢሰጥ እንዴት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይበጃት ነበር? አሁን ግን የምናያው “የሚያስበው”  ‘መንፈሳዊ’ እና በ‘አመክንዬ የማይፈተሽ’ ነገርን ሁሉ በጥርጣሬ ይመለከታል። “የማያስበው” ደግሞ እያንዳንዱ “የሚያስቡ” የሚላቸውን ሰዎች ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ማየት አይፈልግም። ምክንያዩም ደረቅ ናቸው! (ስነ መለኮት የተማረ እና የተቆላ ገብስ አንድ ናቸው! ሁለቱም አይበቅሉም” )

4. “መፅሐፍ ቅዱስ አጠቃቀማችን” በዚህች አጭር የህይወት ዘመኔ መፅሐፍ ቅዱስ ለስነ አመራር ተማሪዎች የስነ አመራር መፅሐፍ፣ ለስፖርት መምህራን የስፖርት መፅሐፍ፣ ለማህበረስብ እድገት ተማሪዎች የማህበረሰብ እድገት መፅሐፍ፣ ለፋይናንስ ተማሪዎች የፋይናስ መፅሐፍ፣ለትምህርት ቤት መምህራን ደግሞ የማስተማር መረሆችን የያዘ መፅሐፍ ሲሆን ታዝቤያለሁ። እንዲያው ወዳጄ ነብዩም ደግሞ የበለጠ ካልተጠነቀቀ እንደ ሮሜ 12፡1-3 እና ማቴ 22፡34 ያሉ ምንባቦችን  ስለ “አስተሳሰብን መጠቀም” የሚያወሩ ክፍሎች እንዳያደርጓቸው ሰግቻለሁ። ምን ትላላችሁ?

5.(በመጨረሻም) ነብዩ ያቀረበው ወረቀት ያነሳቸው ሐሳቦች ድንቅ ቢሆኑም ፤ በበለጠ ጥልቀት መታየት የሚችሉ ይመስለኛል። ለምሳሌ በመፅሐፍት መደብሮች ባደረገው መደበኛ ያልሆነ “ዳሰሳ” ላይ ተመስርቶ ክርስቲያኖች የሚያነቡት የፍቅር እና የ “ሀው ቱ” መፅሐፍትን ነው፤ ስለዚህ “እንደማያስቡ” ማሰረጃ ሊሆን ይችላል ማለቱ ሰቅጣጭ ድምዳሜ ነው። “የሚያስብ ክርስቲያን ምን አይነት መፅሐፍ ነው ማንበብ ያለበት?” “በእርግጥ እነዚህ መፅሐፍትስ ቀርበውለታል ወይ?” የሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያስነሳል። (ወዳጆቼ ምን ትላላችሁ?) ሁለተኛ ፤ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያኖች እንዳያስቡ እንቅፋት ሆነዋል ተብለው ከተጠቀሱት “ባህል” እና “ማሰብን አለማበረታት” ባሻገር ሌሎች ምክንያቶች ይኖሩ ይሆን?

(አቶ ነብዩ አለሙ በስነ መለኮት የመጀመሪያ ዲግሪ ከኢቫንጀሊካል ቲዮሎጀካል ኮሌጅ (Evangelical Theological College) ፤ በስነመለኮት ሁለተኛ ዲግሪ ከኢቲዮጵያን ግራጁዌት ስኩል ኦፍ ቲዮሎጂ (Ethiopian Graduate School of Theology) ፣ በስነ ቋንቋ ሁለተኛ ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ አግኝተዋል። በአሁን ሰዓት በተለያዩ የስነ መለኮት ትምህርት ቤቶች በመምህርነት የሚያገልግል ሲሆን ፤ በማቴቴስ መፅሔት ላይ የመፅሐፍት ቅኝት በማቅረብ ይታወቃል።)   

በቀጣይ ብሎግ (ክፍል ሁለት)

(ክርስትና እና ሳይንስ(Christianity and Science) ፡ በሶፋኒት አበበ የሞሎኩዩላር ማይከሮ ባዮሎጂ የ ፒ.ኤች.ዲ ተማሪ)

ክብሩ ይስፋ ለመድሃኔ ዓለም!!!

Advertisements

5 thoughts on “‘ደቀመዝሙርነት እና ክርስቲያናዊ አዕምሮ’ (Discipleship and the Christian Mind) የተሰኘውን ሴሚናር (ክፍል አንድ)

    1. Teddy,
      Thanks bro for poiniting that out!(My apologies) We will be dealing with that on our “over makiyato” session soooon. God bless bro!

  1. it is good! but the page is not enough I hope I well get on matitas . Neb how to run your sun day meeting ?can send you Web?bless u!!!!!!!!!! pleas this is not the last.

    1. Thank you bro for dropping by.Probably you might get the full coverage on Mathethes and please check sudnay group web site @http://www.ethiosundaygroup.com.This will not be the last we will have one more series on the issue of “Discipleship and Mind”. Showers of Blessings!

  2. I just addresse my thanks for sundaygroup members your guide line is based on the word of God and trying to indicate solutions to the current Chruch problems,this is addressed in Nebyu’s presentation, and in your intial thoughts the last ten years must be exposed in the needy ways of ethiopian churches.My advice is do not give up ,we christian always prays to you to be more effective,be honest,be stick to the scriptures and share every thin in Christ Love. yours Sime Tadesse and Zic Nuru

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s