መጣጥፍ Articles

‘ኮመዲ’ ቲያትር ለማየት የወሰንኩባቸው ሰባት መጥፎ ምክንያቶች ፡

ይሄ  የ’ኔ ድፍረት ነው። ማለቴ “ይሄ ነገር ሊያስነሳው የሚችለውን ትችት ትቋቋመዋለህ ወይ?” ያሉኝ ወዳጆች ነበሩ ? ለእነሱም ጥያቄ መልሴ ታዲያስ! እንዴታ! ነው። ምክንያቱም እነዚህ አስተውሎቶቼ  በየቲያትር ቤቶቻችን ያየ¹ቸውን ኮመዲ ቲያትሮችን ብቻ  በተጨማሪም ሙያዊ ትንተና መስጠትም አልችልም። ምክንያቱም የቲያትር ባለሙያ አይደለሁም! ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱሳዊ/ስነምግባራዊ / ማህበራዊ ሂስ (social critic) ለመስጠት የምችል ይመስለኛል።  ከተግባባን  ሰባት መጥፎ ምክንያቶቼን እነሆ፡

1.    ስድብ፣ ዘለፋ፣ ማንጓጠጥ፣ የቀልድ ዋነኛ ግብዓት መሆናቸው።

ወዳጆቼ እንዲያው ዘንደሮ እንዴት ቀልድ ተወዷል መሰላችሁ። ለዚህ ምስክር የሚሆነን አዲስ አበባችን ውስጥ ‘ኮመዲ’ ነን ብለው ራሳቸውን የሚገልጡ ቲያትሮቻችንን መታደም ነው። ቀልድ ቢወድድ ወይ ቢጠፋ አይደል እንዴ “ስድብ ፣ዝለፋ፣ ማንጓጠጥ” የቀልድ ግብዓቶች፤ የ“አእምሮ ዝግመት” ፣ የአካል ጉዳት፣ አረጋውያን  “ያለ አግባብ” የቀልዱ ማጀቢያ እና መሽከርከሪያ የሆኑት። በ “ኮመዲዎቻችን” ውስጥ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሙልጭ ተደርገው ሲዘለፉ ማየት የተለመደ ነው። ሁላችንም ምንም ጥያቄ ሳናቀርብ ይህንን “የሳቅ  ጎርፍ” መቀላቀላችን ለ’ኔ ገርሞኛል? እንዲያው እዚያ መድረክ ላይ የሚብጠለጠሉት ሰዎች  የእኔ እናት ፣አባት እህት ወንድም ቢሆኑ እንዲህ በሳቅ እነፈራፈር ይሆን ? አይመሰለኝም ! “ባልእንጀራህን እንደራስህ ውደድ” ስል እሟገታለሁ።

2.   ‘ገንዘብ’ ስለከፈልኩበት።

እናንተዬ ገንዘብ ግን ያሳሳል! ምናልባት እኔ ብቻ ሳልሆን ገንዘብ ከእግዚአብሔር በአደራ የተሰጠን እንደሆነ ለምታመኑ ሰዎች ሁሉ ገንዘብ  የከፈላችሁበት ነገር ያንገበግባች¹ል ብዬ አስባለሁ። ጊዜው ጥንቅር ይበል የከፈልንበትን ያህል ግልጋሎት እንፈልጋለን። ለእኔ ግን ቲያትር  እንዳይ ከወሰንኩባቸው ምክንያቶች ዋነኛው  ገንዘብ መክፈሌ ነው። ጥቂት ወዳጆቼም በእኔ ሐሳብ ይስማማሉ። እንዲያው ምንም አይነት ቲያትር ይሁን በጠፋ ገንዘብ የከፈልኩትን ያህል ሳላይ አልወጣም።  ስለዚህ በስድብ  የደመቀ፣ በማንጓጠጥ የታጨቀ፣ ይሁን ቲያትር የማየው ስለከፈልኩበት ነው። በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ለምን ገንዘብ አባክናለሁ የሚል ሐሳብ ወደ ልቤ እየመጣ ብርድ ብርድ ቢለኝም!

3.   የ”ሞባይል” ስልክ  ጩሀት – ለቲያትር ድምቀት ።

          የሞባይል ጉዳይ ግን ግራ የሚያጋባ ሆኗል! አንዳንዴ የምንተነፈሰውን አየር የሆነብን ይመስለኛል። ቲያትር ቤት ውስጥ እንኳን ስንገባ አናጠፋውም። ይሄ ደግሞ ለቲያትር ቤቱ ከፍተኛ ድምቀት ይሰጠዋል። ከተለያዩ የሐይማኖት ቡድኖች (ኦርቶዶክስ፣ወንጌላውያን .. ) መዝሙራት ጀምሮ  አስከ ትኩስ ሰሞነኛ  የሐገር ውስጥ እና የሐገር ውጭ ዘፈኖች ከህፃን ልጅ ለቅሶ እስከ አዋቂዎች ቀረርቶ በምንታደማቸው ቲያትሮች መካከል ብቅ እያሉ በሳቅ እንድናውካካ ወይም በተቃዎሞ እንድናጉረመርም ያደርጉናል። ታዲያ የ “ሞባይል ስልኮች” ለቲያትር ቤቱ መስህብ ሰጥተውታል አትሉኝም። ድንቄም!

4.   ምን ማድረግ እንደሌለብኝ ስለሚያስተምረኝ።

          አንዳንድ ጊዜ ከ“ስድብ” ውጪ መልካም ነገር እንዳይወጣቸው የተገዘቱ በሚመስሉት ‘ኮመዲ’ ቲያትሮቻችን ውስጥ ፍልቅ ፍልቅ የሚሉ ድንቅ ትምህርቶች አጋጥመውኛል። ለምሳሌ ዋሽቶ ማስታረቅ ፣ዋሽቶ ማስማማት፣ ዋሽቶ ማስደሰት፣ ዋሽቶ ሁሉን ነገር ማደረግ አይነተኛ ትምህርቶች ናቸው ። “ቲያትር የገሐዱ አለም ነፀብራቅ ነው።” ሲባል እሰማ ነበር። እናንተዬ ይሄ ገሐዱ ዓለም የሚባለው ነገር ግን አልገባ አለኝ’ኮ? የገሐዱ ዓለም የሚባለው የሚሽከረከረው በውሽት ምህዋር ላይ ብቻ ነው  እንዴ?  (እኔ እኮ (በጌታ) መልካም ገፅታም ያለው ይመስለኝ ነበር?)

5.   “ነጠላነቴን” ለማማረር።

ይሄ ዓለም ግን ነጠላነትን እንደተጠየፈ እሰከመቼ ይሆን የምንዘልቅው? ካፍቴሪያ ብንገባ ለአንድ ሰው የተዘጋጀ መቀመጫ የለም! ምግብ ቤት ብንገባም እንደዚያው ! ሰው ባይኖራቸው እንኳን በወንበር ተከበን መቀመጥ የውዴት ግዴታችን ነው? ቲያትር ቤት ስንገባም ለአንድ ሰው የተዘጋጀ መቀመጫ ይኑር እነጂ፤ ብቻን መግባት ነውር  ነው የሚመስለው። ሰው ቢቻለው ፍቅረኛውን ሸጎጥ አድርጎ ካልቻለም  ወንድ ከወንድ ፣ሴት ከሴት ተጣምረው ነው የሚገቡት። እስቲ በዚህ መ¹ል ብቻውን የተቀመጠ እንደ እኔ አይነቱ ሰው ? ለምን ሰዎች ተጣምረው ይመጣሉ? እኔስ ለምንድን ነው ያልተጣመርኩት? ሳይጣመሩ መኖር አይቻለም ወይ? ለዚህ ይሆን እንዴ “ህብረት” የሚያስፈለገን እያልኩ ለማማረር እችላለሁ? ታዲያ “ኮመዲ” ቲያትሮች በማስታወቂያቸው ባይማርኩኝ ፤ እኔም መማረኬ ይሄን እድል ሰጠቶኛል አትሉኝም?

6.   ለትችት ያለኝ ፍቅር

እንዲያው ወገኖቼ የፊልሞቻችንን ነገር አታንሱት (“ቀን ይፍጀው!”) ቲያትሮቻችንን ግን እንዲያው “ሃይ!” የሚላቸው አያስፈልግም ትላላችሁ። ማለቴ እንዲያው ይሄ ነገራችሁ እኮ ለትውልድ ለሐገር ሚያበረክተው አስተዋጽኦ አናሳ ነው ምነምን የሚላቸው ማለቴ ነው። ባለሙያም ፣ ብስል ፀሓፊ፣ … ምናልባት “ፈጠራ” አይገደብም? እንባል ይሆናል ቢሆንም ግን ከሐገራዊ ፋይዳው አንፃር ቢፈተሽ እንዲያው ምን ያህል በበጀን። (እባካችሁ እሰቲ በጥበባዊ ስራዎቻችን ላይ “ማህበራዊ ፋይዳን ያጠቀሰ ሂስ ልትሰጡ የታጠቃችሁ የመፅሓፍ ቅዱስ (ስነመለኮት) ተማሪዎች፣ የማሕበራዊ ሳይንስ ባለሙያ የሆናችሁ ክርስቲአኖች መፅሓፍ ቅዱስን ማዕከል ያደረገ ትንተናና ምሪት ስጡን?) ታዲያ እኮ ይሄን ሁሉ ለማድረግ በስፍራው መገኘት ወሳኝ ነው፡፤ ለዚህም ነው እንዲያው አቅም በፈቀደ (ገንዘብ ማለቴ ነው!)  ቲያትር ቤት እየገቡ “ኮመዲዎቻችንን መኮምኮም” አይገባህም ትሉኛላችሁ። (እንዲያውም ያለየሁት አንድ ኮመዲ አለ ሰሞኑን አይቼ አፈስላች¹ለሁ!) የዚህ ሐሳብ ውላጅ ቢሆንም ለብቻው ለይቼ አንዱን ሐሳብ ላስጩሀው እስቲ…

7.   “ትውልድ ቀራጮቻችን” ሐላፊነታቸውን እየተወጡ  አለመሆኑ።

የሰው ልጅ በተደጋጋሚ የሚሰማው እና የሚያየው ነገር በአመለካከቱ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆን የስነልቦና ሊቃውንት የሚስማሙበት ሐቅ ነው። “ሰው በልቡ እንዲሚያስበው እንዲያው ነው።” ታዲያ ሐሳባችን እውነት የሆነውን ሁሉ፣ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ትክክል የሆነውን ሁሉ፣መልካም የሆነውን ሁሉ፣በጎ ቢሆን ወይም ምስጋና እነዲዚህ ያሉትን ነገር ማሰብ አለበት። ከዚህ በተቃራኒ ግን ውሸት የሆነውን ሁሉ ውርደት የተሞላበትን ሁሉ የተሳሳተውን ሁሉ ፣መጥፎ የሆነውን እና ፣ክፋት እና መሬት የተሞላበትን ነገር የምናሳብ ከሆነ አለቀልን ማለት ነው።

ታዲያ በዚህ መነፅር “ኮመዲ” ቲያትሮቻንን ስንገመግማቸው ። ከሚዛን የጎደሉ ይመስለኛል የሚስብኳቸው መልካም ነገሮች እንዳሉ ባይካድም እንዲያው በቁጥር አንድ ላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች ግን ሚዛን ደፍተው ታይተውኛል። ስለዚህ ይህንን ቲያትር የሚታደሙ ልጆች/ወጣቶችም ሆነ አዋቂዎች አለጥንቃቄ /ያለማጣራት የሚያስገቧቸው  ሐሳቦች  በውስጣቸው አደገው ምን እንደሚያፈሩ የምናየው ይሆናል። “ምን እንደምትዘራ ተጠንቀቅ የምታጭደው እሱን ነውና!”  ታዲያ “ትውልደ ቀራጮቻችን” ፀሐፊ ተውኔት ፣አዘጋጅ፣ ተዋናይ፣ የባህል ቢሮ…(የሚመለከተው ሁሉ) እነዚህ ጥበባዊ ስራዎች ያላቸውን ጉልበት ተረድተው እንዲአው መድረክ ላይ ከመዋላቸው በፊት አንድ ሁለት ሶስት አራት ጊዜ ቢታሰብባቸው።

እንዲያው በጥቅሉ  ሰዎችን ቲያትር እንዲያቆሙ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች እኔን ግን ይበልጥ ወደ ቲያትር ቤቶች ስበውኛል። እንዲያው ወገኖቼ ቲያትር ቤት ባለገባ እንዴት ገዳም ውስጥ እሆን ነበር። ቲያትር ቤት ደርሽ በጨለማ ውስጥ ተቀምጬ መድረክ ላይ ባለው ብርሃን ላይ ሳፈጥ ህበረተሰቡን በአስተሳሰብ የሚቀረፁ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ስጋ ለብሶ አየዋለሁ። ስለዚህ ይነስም ይብዛም፣ ይክፋም ይነስም፣ ቲያትር ቤት መግባት በተለይ  እምነታቸውን በህይወታቸው ለመተርጎም ለሚፍጨረጨሩ እንደ እኔ አይነት ሰዎች አይበጅም ትላላችሁ።

ክብሩ ይስፋ ለመድሃኔዓለም!

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s