Uncategorized

የሐዊ ማስታወሻዎች (The Dairies of Hawwii) :

ክፍል አምስት

ሐሙስ ዕለት

“ይሄ እግዚአብሔር ግን   ለምንድን ነው ህይወታችንን የሚያቀሉ ነገሮችን ሁሉ የሚከለክለን?” አለች ኪኪ ፈርጠም ብላ።  ጠላታችሁ ክው ይበል ክው ነው ያልኩት። ምናልባት ፊቴ ላይም አመድ  ሳይነዛብኝ የቀረ አይመስለኝም። ኪኪም እኔ የተናገርኩት ያህል ነው የደነገጠችው።

“ይውልሽ ሐዊዬ እስቲ አስቢው ይሄንን ፈተና እንዴት ነው ሳልኮርጅ መስራት የምችለው? እንደምታውቂው ሚ/ር ዩኖ እንደሆኑ አይወዱኝም?” አለችኝ እነዛን የሚያማማሩ ጥርሶቿን ብልጭ አድርጋ።

“ኪኪ…ይሄማ ሐጢያት ነው። እግዚአብሔር አይወደውም?” አልኳት ዓይን አይኗን በርህራሄ እየተመለከትኳት።

ጭል ጭል የሚሉ ዓይኖቿን የምትችለውን ያህል ከፍታ

 “እንዴ …ታዲያ ደስ የሚለው እኛ በፈተናችን ስንወድቅ ነው እንዴ?”

ግራ በመጋባት ጭንቅላቴን ከግራ ወደ ቀኝ አወዛወዝኩት።

ኪኪ ቀጠለች።

“እምልሽ እስቲ አስቢው … ባለፈው አዲሱን የቴዲን ዘፈን ስሚው ብልሽ ¹ጢያት ነው አልሽኝ ? ያቺ ቀልቃላ ልጅ ስትገላምጠኝ ሄጄ ልክ ልኳን ልንገራት ስልሽ … ¹ጢያት ነው አልሽኝ?.. አሁንስ ¹ጢያት የማይሆነው ነገር ምንድን ነው?”

“እህ?”

ኪኪ ቀጠለች ። “እሰቲ አስቢው በ‘በፍሪ ቶክ ፔሬድ’ ዘፈን ሲያስጠናን አልዘፍንም ብለሽ ምን ያህል የምትዘልቂው?”

የምትናገረው ነገር እውነት የለውም ብዬ ለማሰብ ያደረግኩት ሙከራ፤ ቋንቋ ትምህርት ቤት ከገባሁ በ¹ላ ያጋጠሙኝን አሳፈሪ ሁኔታዎች ወደ  አዕምሮዬ አመጣው።

ቀኑ ሰኞ ይመስለኛል። ሰኞ መቼም አይመቸኝም። ምናለበት ፈረንጆች 13 ቁጥር እንደሚሰርዙ ሰኞ ከ‘ካላንደራችን’ ላይ ቢሰረዝ። ሚ/ር ዩኖ ወደ ክፍል እንደገቡ ያለወትሯቸው ዘፈን አስጠናለሁ ማለት ጀመሩ። ተማሪዎቹ ከዳር እሰከዳር በጭብጨባ ክፍሉን አናወጡት።

“ምኑ ነው የሚያስጨበጭበው ! እነዚህ ተማሪዎች ዘፈን ሐጢያት መሆኑን አያውቁም እንዴ!” ስል ለራሴ ተናገርኩ። አስተማሪው “ዌቪንግ ዘ ፈላግ” የሚለውን አዲሱን የዓለም ዋንጫ ዘፈን ከፈቱ። ከጥቂት ተማሪዎች በስተቀር ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ከካሴቱ እኩል ‘ዘፈኑ’። አንድ ሶስቴ ደጋግመው ካሰሙን በ¹ላ ተማሪዎቹን ሲያጤኑ ቆዩና ጥቂት ተማሪዎችን መርጠው ተነሱ አሉን እና ዘፈኑን ከፈቱት። እኔ ከመቀመጫዬ አልተነሳሁም። ሌሎቹ ተማሪዎች ከመቀመጫቸው ተነስተው የሚችሉትን ያህል ሞከሩ።

ሚ/ር ዩኖ ፀጉራቸውን ከቾክ የተሰሩ በሚመስሉ እጆቻቸው እየፎከቱ ተጠጉኝ እና “ተነሺ !” አሉኝ በእንግሊዘኛ፤ ከመቀመጫዬ እንደምንም እየታሸሁ ተነሳሁ።  ቴፑን ተከፈተ ሙዚቃው መጫወት ጀመረ።

 “አብረሽው ዝፈኚ አለኝ” 

“ይቅርታ አልዘፍንም!” አልኩት ።

ተማሪዎች ሁሉ ፊታቸውን አዙረው ሲመለከቱኝ ግንባሬ ላይ ላብ ችፍፍ ሲል ታወቀኝ።

“ለምን?” ብሎ ጠየቀኝ።

“ክርስቲያን ስለሆንኩ አልዘፍንም አልኩት።” ተማሪዎች በሙሉ የሳቅ ልምምድ በሚመስል ሁኔታ በተለያየ ድምፅ ሳቁ። ግንባሬ ላይ ያቀረዘዙት የላብ ዘለላዎች በፊቴ ቁል ቁል ተንከባለሉ።

“ክርስትና ዘፈን ይከለክላል እንዴ?” ብለው ተማሪዎችን ገረመሟቸው። ከክፍላችን ተማሪዎች መካከል በመንቀልቀሉ የሚታወቅ ሸካራ ድምፅ ያለው ልጅ ሳይፈቀድለት መናገር ጀመረ።

“ለምሳሌ እኔ ክርስቲያን ነኝ። ግን ዘፈን እዘፍናለሁ?” አለ።

ሚ/ር ዩኖ ትንሽ የስላቅ ሳቅ ከሳቁ በ¹ላ “ለሐዊ አጨብጭቡላት!!” ሲሉ ተማሪዎች ጭብጨባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈቀደላቸው በሚመስል ሁኔታ ለሶስት ደቂቃ  ያህል ያለማቋረጥ አጨበጨቡ።  ከዚያም በመቀጠል ከድምፀ ሸካረው ልጅ ጀምሮ እያንዳንዳቸው ሳቁ። ኪኪ ዴክሱ ስር ስትደበቅ ነበር ችግር እንዳለ ያወቅኩት። ለካ ሚ/ር ዩኖ ሲያሽሟጥጡኝ  ነበር። መቀመጫዬ ላይ በቁሜ ዘፍ ብዬ ወደ ቅኩበት።

ኪኪ ከገባሁበት የሐሳብ ባህር ውስጥ ስወጣ አሁንም ትኩር ብላ መልስ በሚናፍቅ መልኩ ትኩር ብላ እየተመለከተችኝ ነበር።

“ኪኪዬ “ አልኳት  ዓይን አይኗን እየተመለከትኩ።

“ኪኪዬ አላውቅም! በቃ አላውቅም! ታውቂያለሽ አሁን እግዚአብሔር ግራ እያጋባኝ መምጣቱን ልክድሽ አልፈልግም። ክርስትናዬ ከመላዕክት ጋር ብቻ ካለሆነ በስተቀር ከሰዎች ጋር የሚያኖረኝ አልመስልሽ አለኝ ነው! ደሞ ሳሰበው …”

የጭንቀት ደመና ሲከበኝ ተሰማኝ እና ተስፋ ቆረጥኩ። ምን አይነት እንቆቅልሽ ነው ባካችሁ? ቆይ እስቲ ማንን ነው የማማክረው …አባዬን አባዬን ምን ብዬ ነው የመማክረው ..ዘፈን ሐጢያት ነው ብዬ ነው የምጠይቀው ? ሆሆ እንዲህ ብለው  ምን  ይለኝ ይሆን?

በሚያስፈሩ ዓይኖቹ አይኖቼን ትኩር ብሎ እያየኝ በአግራሞት ግንባሩን ቋጥሮ “ምን አልሽ ዘፈን  እረ ጌታ ይገስፅሽ! ሰይጣን ነው እንዲህ አይነት ሐሳብ በልብሽ ውስጥ የሚዘራው መጽሃፍ ቅዱስ ምን ይላል መሰለሽ…”

ወይም ደግሞ “አንቺ ደፋር… እግዚአብሔርን ነው ‘ምን አይነት ነው’ የምትይው!”

“ለመሆኑ ከነማን ጋር ነው የምትውይው?”

ለማሚስ ብነግራት፤

ፈገግ ብላ አይን አይኔን እየተመለከተች አንገቴን በዕጆቿ ይዛ። “እንደዚህ አይባልም! እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው!” ስትለኝ አሰብኩ። ። ግን ምንም መልስ ሊሆነኝ የሚችል ነገር ልትሰጠኝ እንደማትችል አውቃለሁ።

ቆይ ቆይ እግዚአብሔርንስ ቀጥታ ብጠይቀው? ማለቴ “ እግዚአብሔር ሆይ ለምንድን ነው በዚህ ምድር ላይ ፈጥረህ የምታሰቃየኝ ብለውስ?”  ወይም ደግሞ “እግዚአብሔርዬ እባክህ ለዚህ እንቆቅልሼ ….መ/ር ዩኖን ፀጥ በሚያደርግ መልክ መልሰ እንድሰጣቸው አስተምረኝ።” እግዚአብሔር ግን ጥያቄዬን በቀጥታ ጠይቀው መልሶልኝ ያውቃል ? አያውቅም ሁል ጊዜ የሚጠይቁት ማሚ እና ዳዲ ናቸው።

ኪኪ ይህንን ሁሉ ሳውጠነጥን  ምንም ሳትተነፍስ አይን አይኔን ትመለከተኛለች።

አቤት ጭንቀት? ፀጥታው ያስፈራል። አዕምሮዬ  በሐሳብ እንደ ሰርዲን ተጠቅጥቆ ተሞልቷል። ለቁጥር የታከቱ ሐሳቦች በአዕምሮዬ ውስጥ ተደማጭነትን ለማግኘት ተንጫጩ። ኪኪዬ ጭንቀቴን አይታ ነው መሰለኝ ። “ሐዊ ፕሊስ ዶን ዎሪ!” ብላ እንደሞት የከበበኝ ፀጥታ ሰበረችው።

Advertisements

3 thoughts on “የሐዊ ማስታወሻዎች (The Dairies of Hawwii) :

  1. what can I say…..you are getting better and better,your characters are becoming as real as people,Hawe can make you feel things when you read her diaries….I love it but your stories are very short work on that.
    blessings!!!!!

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s