ምን ይወራል ? News

ሰሞንኛው የ“እስራኤል ቀን” ስብሰባ እና የ’ኔ ሶስት ጥያቄዎች?

 

ዕለት ማክሰኞ ማለዳ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የተገኘሁት ቀደም ብዬ ነበር። በዚህ ስፍራ ላይ እንድገኝ ያደረገኝ ጉዳይ ግን በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያናት ህብረት (ሕብረቱ)  በኩል የተላለፈውን ከ ሰኔ 14 -18 ቀን 2002 ዓ.ም የሚቆይ የስብሰባ “ጥሪ”  አክብሬ ነበር። በግምት ከአንድ ሺህ ሰው በላይ የታደመበትን ስብሰባ አሐዱ ብለው ያስጀመሩት የሕብረቱ ሰብሳቢ የሆኑት ቄስ አለሙ ሼጣ ነበሩ። እሳቸውም ሁላችንም ለእስራኤል እንድንፀልይ በመጠየቅ የፕሮግራሙን መከፈት አበሰሩን ። በመቀጠልም ዶ/ር ሄኖክ አድሃኖም እና ፓ/ር ቶም ሄስ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተሰብሳቢዎችን በማስተዋወቅ መርሐ ግብሩን በፀሎት አስጀመሩ። በዚህ ሁኔታ ስበሰባው ቀጠለ። የስብሰባው ሂደት እየገፋ በሄደ ቁጥር፤ ማዕከሉም “ብሄራዊቷ እስራኤል” (National Israel) እየሆነች በሄደች ቁጥር ግን ሶስት ጥያቄዎች  በአዕምሮዬ ውስጥ ተፈጠሩ። እነዚህ ጥያቄዎቼም ፦ የስብሰባው መጥሪያ፣ ስነ-መለኮታዊ መሰረቱ እና ግቡን የተመለከቱ ነበሩ።

ጥያቄ አንድ የስብሰባው “ጥሪ” ፦ ለስብሰባው ጥሪ የተላለፉት ሁለት አይነት መጥሪያዎች ነበሩ። አንደኛው በቀጥታ በህብረቱ የተበተነው መጥሪያ ሲሆን ፤ ይሄ መጥሪያ “4ኛው የመላው አፍሪካ ሐገራት ስብሰባ  ከሰኔ 14-18 ቀን 2002 ዓ.ም” የሚል በፖስታው ላይ ሰፍሯል (ርዕሱን ልብ ይሏል)። ይኸው መጥሪያ ዝርዝሩን በማንበብ ከሚገኘው መረጃ ያለፈ ስብሰባውን ዓላማ በማያሻማ ሁኔታ ግልጽ አድርጎ የሚያስቀምጥ  አይደለም። ሁለተኛው ደግሞ ለእስራኤል ለመፀለይ ሸክም ካላቸው ወዳጆቼ የተሰጠኝ መጥሪያ ሲሆን እሱ  ከሕብረቱ መጥሪያ  ግማሽ ገፅ ነው። ፖስታው ላይ የተፃፈው ነገር ግን ግልፅ ነው። እንዲህ ይላል፦ “4ኛው የመላው አፍሪካ ሐገራት ስብሰባ (አፍሪካ እስራኤል ቀን) 18 ቀን 2002ዓ.ም” ( የቅንፍ ማብራሪያውን ልብ ይሏል) ። የመጀመሪያውን መጥሪያ ሳነበው ምንም “ልዩ” የሆነ አጀንዳ ያለው አልመሰለኝም። የተለመደው የሕብረቱ ስብሰባ ነው የመሰለኝ ፤ ሁለተኛውን ግን ሳነበው በእርግጥ የስብሰባችን ማዕከል ለእስራኤል ስለሚደረገው ፀሎት ሪፖርት ለመስማት፣ ወይም ለማቀድ ነው ስለመሰለኝ ክፋቱ አልታየኝም ነበር። ግን  አንድ አይነት የሆኑ መጥሪያዎች በፖስታቸው ላይ የተለያየ መልዕክት ማንገብ ለምን አስፈለጋቸው?

ጥያቄ ሁለት ስነ-መለኮታዊ መሰረቱ።  መጋቢ ቶም ሄስ በዚያኑ ዕለት ባቀረቡት ስብከት ላይ አሁንም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳላጠፈ፤ አሁንም “ብሄራዊት እስራኤል” የእግዚአብሄር የቃልኪዳን ህዝብ እንደሆነች መፅሐፍ ቅዱስም 700 አካባቢ ጥቅሶችን በመጠቀም ይህን እንደሚያብራራ ገልጠው ጥቂቶቹንም ቆነጠሩልን። እንዲያውም  “የሚባርኩህን እባርካለሁ ፤የሚረግሙህን እረግማለሁ” (ዘፍ 12፡1-3) የሚለው  ቃል ለ“ብሄራዊት እስራኤል” የተገባ ኪዳን ነው። እስካሁንም የፀና ነው! ሲሉ ከተናጋሪዎች አንዱ አሰረገጡ። ገና ከስብሰባው መጀመሪያ ለሌሎች የአፍሪካ ሐገራት የሚደረገውም ፀሎት ከዚህ አቅጣጫ እንደሚሆን ግልጡን ተነገረን። በእርግጥ  የአብርሐምን ቃል ኪዳን ለ“ብሄራዊቷ እስራኤል”  እንደሚሰራ  መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል እንዴ?

 “የአብርሐም ቃልኪዳን ወራሽ እስራኤል ወይስ ቤተክርስቲያን?” ለዚህ ጉዳይ የሚሰጠው መልስ እጅግ በጣም አከራካሪ ነው። የአከራካሪነቱ መንስኤዎች ደግሞ የተለያዩ የመፅሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይህ አስተምህሮ የሚመሰረትበቸው የአዲስ ኪዳን ምንባባት በተለይም በሮሜ 9-11 እና ሌሎች የእስራኤል እና የቤተክርስቲያን ማንነት በሚያብራሩ ምንባባት ላይ  ያላቸው የአተረጋጓም እና የአረዳድ ችግር ነው። በግርድፉ ሶስት አመለካከቶች አሉ። የሪፎርምድ የስነ መለኮት ሊቃውንትም አመለካከት ሚላርድ ጄ ኤሪክሰን በግርድፉ ያንፀባርቃሉ። እሳቸውም እንዲህ ይላሉ

        “መንፈሳዊቷ እስራኤል (ቤተክርስቲያን) ለብሄራዊቷ እስራኤል የተገባውን ኪዳን በመፈፀም  የብሄራዊቷን እስራኤል ሰፍራ ወስዳለች።… ቤተክርስቲያን አዲሲቷ እስረኤል ነች። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የብሉይ ኪዳኗ እስረኤል የያዘቸውን ስፍራ ይዛለች።ጌታ በመቀበል እና ቤተክርስቲያንን በመቀላለቀል ላይ የተመሰረተ ቢሆንም እንኳን እስራዔል እንደ ሓገር ወደፊት የእግዚአብሄር ጉብኝት ይደርሳታል።”[i]

 ይላሉ። ይህንን አባባል በከፊል የሚቀበሉት ደግሞ ታዋቂው  “የእግዚአብሔሯ እስራኤል” (The Israel Of God) የሚል መፅሐፍ የፃፉት  አቶ ሮበርትሰን ናቸው ፦ “የመዳቀል ፅነሰ ሐሳብ ለአይሁድ በጥቅሉ እና ለአይሁድ ምርጦች ወደ ፊት አንድ ጉብኝት ይደረግላቸዋል ማለት አይደለም።… እስራኤል ሁሉ የሚለውም ፅንሰ ሐሳብ በአሁኑ ዘመን በሚደረገው የወንጌል አገልግሎት ጌታን ተቀብለው የዳኑትን ሰዎች ብቻ ነው።”[ii] ሲሉ ይከራከራሉ። በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ሮበርትሰን አንድ ምሁር ለዶክተሬት ዲግሪ መመረቂያቸው የፃፉትን ጽሁፍ እንዲህ ሲሉ ይጠቅሳሉ፦ “ ሰዎች በጣም የሚስማሙበት ሐሳብ ተቃራኒው ቢሆንም፤ አዲስ ኪዳን የእስራኤልን በምድሪቷ ላይ እንደ ፖለቲካዊ ሐገር መመስረትን በተመለከተ በሚያስገርም ሁኔታ መልስ አይሰጥም።”[iii]  እነዚህ ምሁራን የአብርሐም ኪዳን ወራሽ ቤተክርስቲያን እንጂ “ብሔራዊቷ” እስራኤል እንዳልሆነች ይስማማሉ።

  በአሁኑ ሰዓት “የብሔራዊቷን እስራኤል” የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች ወራሽነት የሚደግፈው ስነ መኮታዊ አመለካከት ዲስፕነሴሽናሊዝም የምንለው ነው። የዚህ ሐሳብ አራማጆች በተለይ “ትውፊታዊ” የሚባሉት ያላቸው አመለካከት በሚከተለው መልኩ በግርድፉ ሊገለጥ ይችላል። “ብሉይ ኪዳን ምድራዊው የእግዚአብሄር መንግስት የዚህ ዘመን ሕዝቦች በሆኑት በእስራኤላውያን አማካኝነት በክርስቶስ የሺህ ዓመት አገዛዝ ውስጥ ይፈፀማል። ሰማያዊ የሆነችው ቤተክርስቲያን ግን የተለየ ፍፃሜ አላት።”[iv] ይሄ አመለካከት እስራኤል እና ቤተክርስቲያን የተለያዩ ናቸው እግዚአብሄር ለብሉይ ኪዳን ሰዎች የገባላቸውን ቃል የሚፈፅመው በ“ብሄራዊት እስራኤል” አማካኝነት ነው ይላል። ስለዚህ ይህንን አመለካከት የሚያራምዱ ሰዎች ለ“ብሄራዊቷ እስራኤል” እንፀልይ እሷ ብንነካ ፤ የእግዚአብሄርን የአይኑን ብሌን መንካት ነው ይሉናል። ስለእነዚህ አመለካከቶች በብዙሃኑ ዘንድ ያለው መረዳት ምን ይመስላል?

 ታዊቂው የብሉይ ኪዳን ስነመለኮት ሊቅ ብሩስ ዎኪ “የተከለሰው የዲስፔንሽናሊስቶች አመለካከት እስራኤል ወደ ፍልስጤም ምድር  መመለሷ የኪዳኑ መፈፀም መሆኑን የሚያሳይ ምንባብ ከአዲስ ኪዳን ውስጥ ከአንድ ቦታ እንኳን ካሳዩኝ እቀላቀላቸዋለሁ።”[v] ሲሉ እሰራኤል እና  ቤተክርስቲያን የተለያዩ ናቸው የሚለውን ሐሳብ ያጣጥሉታል። ወጣት አንተነህ የስነመለኮት ዲግሪውን ከአፍሪካ ናዛሪን ዩኒቨርስቲ ላይ ሰርቷል ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገር “ስለ እስራኤል ሕዝብ መዳን መፀለይ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ።” ነገር ግን  እግዚአብሄር ለእስረኤል የተለየ እቅድ አለው በሚለው ሐሳብ ላይ እንደማይሰማማ  እና መፅሐፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆነ ይናገርና “ለምንድን ነው ግን ለፍልስጤም መዳን የማንፀልየው?” ሲል  ጠይቃል። በዚሁ ስበሰባ ላይ ተካፋይ የነበረው ስሙ እንዳልጠቅስ የተማፀነኝ የስነመለኮት ተማሪ የሆነ ወጣት ደግሞ “ ስብሰባው ላይ በነበርኩባቸው ጊዜያት እንዳየሁት እስራኤል እና ቤተክርስቲያን የተለያዩ ናቸው የሚለው መረዳት የተንፀባረቀ ይመስለኛል። ብሄራዊቷ እስራኤል የእግዚአብሄር ምርጥ ነች የሚለው ሐሳብ ከመድረኩ ተደጋግሞ ሲወረወር በአንዳንድ ተሰበሳቢዎች ላይ ቅሬታ መፍጠሩን ገልጿል።” የዲስፔነሲስናሊስቶችን አመለካከት የምትደግፈው ደግሞ እህት ተዘራ ወርቅ በአግራሞት እንዲህ ስትል ትጠይቃለች፤ “ ብሉይ ኪዳን ላይቁልጭ ብሉ የተቀመጠውን ሐሳብ እንዴት አድርገን ነው የምንክደው? ለእስራኤል መዳን እንዲሁም ለተገባላት ኪዳን መመለስ መፀለይ ሐላፊነታችን ነው።” ታዲያ የሄን አይነት የተለያየ መረዳት ባለበት ሁኔታ ስነ መሎከታዊ መሰረቱን ሳያጠሩ “ለእስራኤል እንፀልይ” ማለት ምን ማለት ይሆን?

 ጥያቄ ሶስት  የስብሰባው ግብ። አንድ ወዳጄ እንደጠቆመኝ ከተካፈዮች አንዱ ኮትዲቮር እስራኤል ላይ ክስን ባስነሳች ጊዜ መከፋፈል እና ጦርነት እንደደረሰባት እስራኤልን መባረክ በጀመረች ጊዜ ደግሞ  በሐገሪቷ ውስጥ ማዕድናት እንደተገኙ እና ወደ ብልፅግና እንደተሻገረች ተነገሩ።  ከዚህ ምስክርነት እና በስብሰባው ላይ ከተነሱት “ፂዮናዊነት ዘረኝነት አይደለም” ብሎ የተባበሩት መንግስታት ወስኗል እና የአፍሪካ ህብረት እንዲወስን ፀልዩ። በዚህም ምክንያት “ብሔራዊቷን እስራኤል”ን ስለነካን ጌታ “ረግሞናልና” ንስሐ እየገባን እንፀልይ። በተጨማሪም የእስራኤል ዋና ከተማ ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመለስ የአፍሪካ ሐገራትም ኤምባሲዎቻቸውን ወደ እንዲመልሱ እንፀልይ የሚሉት ነገሮች ጎልተው መውጣታቸው የስበሰባውን አጀንዳ እንድጠራጠር አድርጎኛል። የስብሰባው ዓላማ  “ፖለቲካዊ ድጋፍን ማሰባሰብ” ነው? ወይስ ደግሞ የእግዚአብሄር የማዳን እቅድ በ“ብሄራዊቷ እስራኤል” ውስጥ እንዲፈፀም መጠየቅ ነው?  ይህን አይነት ፀሎት በእስራኤል ፍልስጤም ግንኙነት ላይስ ያለው ሚና ምንድን ነው? የሙስሊም ክርስቲያን ግንኙት ላይስ ያለው ፋይዳ ምን ይሆንየአቢያተ ክርስቲያናት ህብረትስ በዚህ ውስጥ መሳተፉ ወንጌልን ለሙስሊሙ ማሕበረሰብ ለማድረስ በምናደርገው ጥረትስ ላይ ምን አንድምታ ይኖረው።

እነዚህ የእኔ የግል ጥያቄዋች መልስ አላገኙም።  እስቲ መልስ ያላችሁ ሰዎች ጀባ በሉኝ!!


[i] Blaising Craig A. and Book Darrel L. (eds.) Dispensationalism: Israel and the Church. (Grand Rapids ,Michigan : Zondorvan Publishing House,1992) p.219

[ii] ዝኒ ከማሁ ፤ገፅ 357

[iii] ዝኒ ከማሁ፤ገፅ357.

[iv] ዝኒ ከማሁ፤ገፅ357

[v] ዝኒ ከማሁ፤ገፅ 357

ዋቢ መፅሐፍት

Robertson O. Palmer, The Iserael of God: Yesterday,Today and Tommorow (New Jersy: P&R Publishing,2000)

Advertisements

One thought on “ሰሞንኛው የ“እስራኤል ቀን” ስብሰባ እና የ’ኔ ሶስት ጥያቄዎች?

  1. What a wonderful reflection. It is possible to understand the love people have for nation Israel based on a literal translation of the bible, but you raised a good question. Who represents the nation Israel? Do we have ethnically ‘clean’ Israel now?! (Remember their scattering all over the world before they tried to found the Israel state).
    The main question I think is why the Lord chose Israel. The Old Testament speaks that they were chosen to be kingdom of priests. They were to point people to Yahweh as the only God. Now, what does the New Testament teach about them? This is controversial. However, trying to support nation Israel at the expense of Palestinians (and any other nation for that matter) is unbiblical. God does not show favoritism. The Church is to witness about the Lord to all, including those who do not know the Lord in the nation Israel. God has no favorites! Let us not be decieved into believing that mere physical birth qualifies one for salvation. Repentance is good, but let’s us repent about our bad attitude towards all nations, including Muslims!
    It is very sad to hear that the Ethiopian Evangelical Churches Fellowship promoted such a one-sided interpretation of the bible. Who gave Israel the right to abuse other nations? Most of all, let us not base our doctrine on controversial passages.

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s