Uncategorized

የሐዊ ማስታወሻዎች The Diaries of Haawii (ክፍል ሶስት)

ሰኔ 7 ጠዋት 12፡30

የአዲስ አበባ ስታዲየምን በሚያህለው ሳሎናችን ውስጥ ሁላችንም አሮጌውን የዳዲን የጥናት ጠረጴዛ ከበን ተቀምጠናል። ከፊት ለፈታችን በቁጥራችን ልክ ደረታቸውን ገልጠው የተቀመጡ መፅሐፍ ቅዱሶች ይታያሉ። ባለ አበባ አቃፊው አምፖል የሚያመነጨው ብርሐን  ቤቱ ውስጥ ይደንሳል። ዳዲ ፊቱን ቅጭም አድርጎ፣ የንባብ መነፅሩን  የአፍንጫው ጠርዝ ላይ አስደግፎ በፊቱ ፊት ለፊቱ  የተቀመጠውን ግዙፉን አሮጌ መፅሐፍ ቅዱሱን እያነበበ ያብራራል።  ቤቢእና አይኖቹ ግን ግብግብ ገጥመዋል። እንደምንም አንደርድሮ ሲከፍታቸው እንቅልፍ ያረገዙ አይኖቹ ተመልሰው ይከደኑበታል፤ አይኖቹን የከደነው የእንቅልፍ ማዕበል ሽቅብ ወደ አናቱ ወጥቶ ወደ ፊት በኩል ድፍት ያደርገውና ወደ ጎን አዘንብሎ እኔ ላይ መጥቶ ዘፍ ይላል። እግሩን ስረግጠው ብንን ብሎ አይኖቹን ለመክፈት የፍጨረጨራል። ትንሽ ይቆይ በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ  ማሚ ይነጋደድ እና እላይዋ ላይ ዘፍ ይላል። ማሚ ገፋ ስታደርገው ይነቃል። ብቻ ምን አለፋችሁ ልክ እንደ ፔንዱለም በእኔና በማሚ መካከል ይወዛወዛል። ሰራተኛችን ፅጌ  ቤቢን እየተመለከተች አፏን በመዳፏ ሸፍና ትስቃለች። ዳዲ ከሮሜ 12፡1-3 አንብቦ ማብራራት ከጀመረ ቆይቷል። ማሚ  በክንዷ ጠረጴዛውን ተደግፋ አገጯን በመዳፏ አደግፋ አይኖቿ ዳዲ ላይ ትክል አደርጋ ታዳምጠዋለች። ግን አይኖቿን ትክል አድርጋ ጠረጴዛውን ክንዷን የእጆቿ መዳፎች አገጯ ላይ አሳርፋ በትኩረት ታዳምጠዋለች። ዛሬ ብቻ እንዳይመስላችሁ  ላለፉት ዘመናት ሁሉ እንዲሁ ነች። አለመስልቸቷ ይገርመኛል! አይ ማሚ ኬክ! ከዳዲ በላይ የምትወደው እና የምታከብረው ሰው የለም። እኔም አልፎ አልፎ  ሐሳቤ ቢወሰድም አዳምጠዋለሁ።  ቤቢ ግን እንደሌለ  ከዳዲ በስተቀር ሁላችንም እናውቀዋለን።

ዳዲ ለመጨረሻ ጊዜ በሚመስል ሁኔታ ጉሮሮውን አፀዳዳና  ደስ በሚል ጎርናና ድምፅ “እሺ ሁላችንም የሰማነው በህይወታችን እንዲፈፀም እንፀልያለን” አለ።  በእንቅልፍ ውስጥ የነበረው ቤቢ ይህንን ድምፅ መልአክ ሹክ ይበለው ሰይጣን ሳይታወቅ ከሁላችንም ቀድሞ ወደ ሶፋው ጋር ለመሄድ ሲንደረደር፤ የምንጣፉ ጠርዝ አደናቅፎት ወደ ላይ ጎነ…

ማሚ “ቀስ!”

ዳዲ “ምን ያደናብርሃል!”

ፅጌ “በለው!”

እኔ  “በየሱስ ስም!”

 ብንልም ቤቢ ግን መሬት ላይ ወርዶ በደረቱ ተዘረጋ።

 በእንቅልፍ ልቡ በሚመስል ሁኔታ ከወደቀበት ተነስቶ ሶፋ ስር ተንበረከከ። እኔም እሱን ከእሱ አጠገብ ሶፋው ስር ተንበርክኬ ፣በግንባሬ የሶፋው ጠርዝ ላይ ደገፍ ብዬ መፀለዬን ጀመርኩ ። ዳዲ ግን አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ቀኑን ሙሉ ሳይንበረከክ ቢፀልይ እንደማይደክመው አውቃለሁ። ማሚም በተለመደው ሁኔታ ምንጣፉ ላይ በግንባሯ ተደፍታ ፀሎቱ ቀጠለ። (አይ ማሚዬ ስታሳዝን!) ስለራሳችን ፣ስለቤተክርስቲያን፣ ስለቤተሰባችን፣ ስለ ሃገራችን ፣ ስለፖለቲካ መሪዎች  በዳዲ መሪነት ፀለይን ። ድንገት ግን ጆሮዬን ጣል ሳደርግ ቤቢ በለበሰው ጋቢ ተሸፋፍኖ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ሲያንኮራፋ ይሰማል። (አቤት ዳዲ ቢሰማው ጉዱ ፈላ !) ጎኑን በክንዴ መታ አደረግኩት ነቅነቅ አለና “ምንድን ነው? ምንድን ነው?” ብሎ ተመልሶ ተሸፋፈነ። ዳዲ እና ማሚ ድምፃቸውን ከፍ አድረገው ባይፀልዩ ኖሮ ሊሰማ እንደሚችል ገመትኩ፤ በተጨማሪም የዳዲን ቁጣ አስቤ ክው አልኩ። በእንብርክኬ እየተንፏቀቅኩ ጠጋ ብዬ በደንብ ሳቀምሰው ነቃ ። በእንቅልፍ ልቡ ጮክ ብሎ “አሜን! አሜን!” አለ። ይህንን ስናደርግ ምናልባት ከሰራተኛችን በስተቀር የሚያውቅ የለም።

ዳዲ ፀሎት ስንጨርስ እንደሚያደርገው “ ገነት .. ስለ ቤተክርስቲያን ትፀልያለች… ሃዊ ደግሞ ስለአዲሱ  የቤተክርስቲያን ህንፃ ግንባታ… ቤቢ ስለቤተሰባችን …”ሲል ድንጋጤዬ ጨመረ ። ዳዲ ይሄንን ሲል ቤቢ እያንኮራፋ ነበር። የምችለውን ሁሉ ሞከርኩ በእግሬ ረገጥኩት ፣ አነቃነቅኩት፣ ፀጉሩን ነጨሁት ወይ ፍንክች ። ማሚ ጨረሰች ። እኔም በግማሽ ልቤ ጨረስኩ። ዳዲ “ እሺ አሁን ከቤቢ ጋር  ሰለዚህ ቤተሰብ እንፀልያለን…” ሲል ባለ በሌለ ጉልበቴ የካኒቴራውን አንገትጌ ይዤ ጎትቼ ቀና አደረግኩት እንደምንም እየተንገዳገደ በእግሩ ቆመና ተነሳና “ ጌታ ሆይ የሃገራችንን ሁኔታ የምታውቀው ነው….” ሲል የፅጌ ሳቅ በቤቱ ውስጥ ፈነዳ ። እኔም ሳቄን ለቀቅኩት። ማሚ እሳት እንደነካው ላስቲክ ጭምትርትር ስትል ይታየኛል። ዳዲ እንደዛ ቀን ተናዶ አይቼው አላውቅም ። እንደምንም አመስግኖ ከጨረሰ በ¹ላ ሁላችንንም አስወጥቶ ቤቢን ለሰላሳ ደቂቃ ያህል ተቆጣው።

እኔም ትምህርት ቤት ረፍዶብኝ ስለነበር ወደ ክፍሌ ገባሁና ልብሴን ቀያይሬ ቻው ብያቸው ወጣሁ ። ወደ ጓሮ ሄጄ ‘ኩል’ እና ‘ሊፒሰቲክ’ ተቀባሁ ልክ እንደ ኪኪ ፀጉሬን አስየዤ ፤ከውስጥ የለበስኩትን አጭር ቀሚስ እንዳያሳይ ረጅም ካፖርቴን ጥብቅ አድርጌ ቆለፍኩ። በራችንን ገና እንደወጣሁ አንድ ሊስትሮ “አቤት ውበት ..እንዳትበሪ !” ሌላኛው “ወዴት ነው ባክሽ?” “ አልረፈደም እንዴ ወይስ ልትቀጭው ነው?” ወ.ዘ.ተ። አቤት ወንዶች ሲያናድዱ ቆንጆ አይተው የሚያውቁ አይመስሉም።….ማሚ ወይም ዳዲ እንደዚህ ሆኜ ቢያገኙኝ ሊከሰት የሚችለውን ነገር አሰብኩና ቀዝቃዛ ላብ በጀርባዬ ሲንቆረቆር ታወቀኝ…. “ታዲያ ፋራ ሆኜ ሄጄ የጓደኞቼ መሳቂያ እንድሆን ነው የሚፈልጉት ?….መፅሐፍ ቅዱስ አትልበሱ ይላል እንዴ?”

በአንድ ልቤ ለምንድን ነው ተናግሬ የማላርፈው አንድ ቀን መያዜ እንደሆነ አይቀር ብዬ አስበኩ። ነገር ግን ዳዲ አንድ ቀን ጥብቅ ያለ ሱሪ አድርጌ አይቶኝ “ገነት ለመሆኑ እንደዚህ አይነት ልብ ስትለብስ ዝም ትያታለሽ?” ብሎ ማሚ ላይ የጮሀባት ትዝ አለኝ። ድንገት ተማሪዎች ሰፊ ቀሚስ ሰለምትለብስ “ዘርፌ” እያሉ የሚቀልዱባት ምስኪኗ ሰናይት ትዝ አለችኝ። ብቻ አእምሮዬ ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌለው ሃሳብ ተንጫጫ ሃሳብ ተንጫጫ… ሃሳቤን እንዲያረጋጋልኝ “እወድሃለሁ” የሚለውን መዝሙር እያንጎራጎርኩ በረርኩ…ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት።

ይቀጥላል …

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s