መጣጥፍ Articles

ስጋ በል ፍቅር

(አንድ ወዳጄ እንደተረከው)

በሳምንቱ ውስጥ ከሚገኙ ቀናት መካከል በአንዱ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስናወጋ መሸት ይልብኝ እና ታክሲ ይዤ ወደ ቤት መሄድ ጀመርኩ። በግምት ሰላሳ ሜትር ያህል ከተጓዝን በ¹ላ አንዲት ወጣት እጇን ዘርግታ ታክሲውን ታስቆመዋለች። እሷ ግን ውጪ ቆማ ከአንድ ወጣት ጋር መጨቀጨቋን ትቀጥላለች።የታክሲው ተሳፋሪዎች እኔን ጨምሮ ወደ ሶስት ሰዓት እየተቃረበ መሆኑን እያሰብን ጮህንበት። የታክሲው ረዳት ከታክሲው  ውስጥ አንገቱን አውጥቶ ወደ ውጪ ትዕግስት በማጣት  “የምትመጪ ከሆነ ነይ አለበለዛ ልንሄድ ነው?”  ሲል አምባረቀባት። ልጅት ከወጣቱ እጅ ተስፈንጥራ መጥታ ከአጠገቤ ተቀመጠች ። ትኩር ብዬ ስመለከታት መረበሽ እና መቅበጥበጥ ይታይባታል። በእጆቿ የያዘቻቸውን  ጥቂት ሳንቲሞች መዳፏ ላይ ታሻሻቸዋለች። ትኩር ብዬ ተመለከትኳት ። ውስጤ ሳንቲም እንደሌላት ጠረጠርኩ። የተጣጠፉ ብሮች ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ ፤ ፈገግ ብዬ እየተመለከትኳት “ ብከፍልልሽ ቅር ይልሻል?” አልኳት ትንሽ ተግደርድራ እሺ አለችኝ። ደፈር አልኩና ሌሎች ጥያቄዎችንም ጠየቅኳት።

“ በሰላም ነው ?”

“ባክህ… ካላደርሽ ነው የሚለኝ ?” ደነገጥኩ ።

 “ምን ያህል ጊዜ ትተቃዋወላችሁ ?” አልኳት። ዕድሜዋን ለመገመት እየሞከርኩ በግምት ከ17 ዓመት አይበልጣትም ረጅም አይኖቿ ጎላ ጎላ ያሉ ድምጿ  ጎርነን ያለ ወጣት። ፈገግ ብላ “ ስድስት ቀንም አይሞላንም አብረን ዛሬም አብረን ነው የዋልነው… አብረን ካላደርን አለኝ ዕኔ ደግሞ እቤት “ሃርድ” ነው ።” አለችኝ። ወደ መውረጃችን ስንቃረብ “የዕከሌ ሰፈር ትራንሰፖርት የት ነው የማገኘው አለችኝ?” ሰዓቴን ተመለከትኩ ከምሽቱ 2፡48 ደቂቃ “ልሸኝሽ?” አልኳት እና ልመካክራት ሞከርኩ። የተባለው ሰፈር ትራንስፖርት የሚያዝበት ቦታ ስደርስ ፤ ጥቂት ብሮች አስጨበጥኳት እና ታክሲ ውስጥ እየተቻኮለች ስትገባ ትኩር ብዬ ተመለከትኳት።

ያም ብቻ ሳይሆን ፤ ቦይ ፍሬንድ ተብዬውም ምን አይነት ሰው ነው? አብረን ካላደርን ብሎ ይህችን የምታክል ልጅ ፣የማታውቀው ሰፈር በምሽት ያለምንም ሳንቲም ጥሏት የሚሰወረው ? ምናልባት ይሄም የፍቅር መገለጫ  ይሆን እንዴ? ወይስ ደግሞ የዘንድሮ ፍቅር “እንሰሳዊ” እና አካላዊ ብቻ ሆነ? ፍቅር ማለት ከጊዜያዊ የወሲብ ጥማትን ከማርካት ባሻገር ያለውን ለዛ  አጣ? አላውቅም እናንተ የምትሉትን በሉት እኔ ግን “ስጋ በል ፍቅር” ብዬዋለሁ።

Advertisements

ምን ሐሳብ አለዎት?

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s