“በሠርግዎ ቀን ጌታን ያምልኩ!” ግን በዲጄ …

እናንተዬ ሰርግዎን በዲጂ የሚለው ነገር  ወንጌላውያን ሰፈርም እንደገባ ለመሆኑ ሰማችሁ? ትላንት ቁልቁል ቡልጋሪያን ሰቋርጥ  ነበር ከላይ የጠቀስኩትን ማስታወቂያ ያየሁት። እንዲያው ለመሆኑ በእኛ መንደር ያለውን  “ሠርግዎን በዲጄ” እንዴት ያዩታል? የምለውን ከማለቴ በፊት የእናንተን መስማት ፈልጌ ነው። ጠብቃለሁ?

እባክዎ ሪፖርተር ጋዜጣ ስለዚሁ ጉዳይ የፃፈውን ይመልከቱ…

“ቀለል ያለ የጋብቻ ሞዴል፦ በብር 15000.00 ብቻ!”

ወገኖቼ ለካ ሙሽራ ለመሆን መመከር በራሱ ኢንቬስተር መሆን መሞከር ኖሯልና? ማለቴ ሁለት ሰዎች በጌታ ምሪት መጋባትን ያህል ወኔ የሚጠይቅ ውሳኔ ወስነው። ለመጋባት ሲያቅዱ …ከፊታቸው ድቅን የሚለው ወጪው ነው።  እንዲያው  እስቲ ቀለል የክርስቲያን ሰርግ አሥቡ። በቃ አለ አይደል ፦

ስቱዲዮ ሄዶ ፎቶ መነሳት ፤ ቤተ ክርስቲያን ተገናኝቶ ቀለበት ማድረግ

አይነት ሰርግ። ስንት እንደሚያስወጣ ታውቃላችሁ ቢያንስ በትንሹ 15000.00 ብር ። ቀለበት 5000.00 ፣ቬሎ 1000.00፣መኪና 1000.00፣ ሱፍ 1500 ብር …ገስት ሐውስ 1400.00 ብር …’ፍሸና’ 1500.00፣  እና እኔ እውቀት ከማጣት የዘለልኳቸውን ነገሮች ደምሩበት!

አጀብ! 15000.00 የኢትዮጵያ ብር…

“ላጤዎች” እንደኔ ማለት ነው! ወይ ገንዘብ አጠራቅሙ! ወይም ደግሞ ሌላ ሞዴል ፈልጉ። እኔ ግን ብፈልግ ፣ብንፈልግ አጥቼ በዚሁ ሞዴል ልሞክረው ወይ እያልኩ ነው። ቅዱሳን ምን ትላላችሁ?

ወደ “ጨዋታው ሜዳ” ተመለስናል

ወዳጆቼ ለጊዜው  አዳዲስ  ፅሁፎችን  ብሎግ ማድረግ አቁሜ ነበር።  አሁን ግን አዲስ እና በሰል ያሉ ጽሁፎችን ይዤ ለመምጣት እየተሰናዳሁ ነው ። እናንተዬ የምታነቡትን ፣ የምታስቡትን ..የሚያጋጥማችሁን ነገር ለመተናፈስ “ቦታ ማጣት” እንዴት ይጨንቃል?  አሁን ግን “ብው” ብዬ ሳልፈነዳ ተመልሻለሁ።

ክብሩ ይሰፋ’አ!